ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, July 3, 2020

በሕወሓት እና በግብፅ መንደር ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ የሚመራው የለውጥ ኃይል በእዚህ ሳምንት በከፍተኛ ደረጃ ወደፊት ተስፈንጥሯል ማለት ይቻላል።ዓርብ ሰኔ 26፣2012 ዓም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፀጥታ እና የፍትህ አካላት ያሉበትን ኮሚቴ ሰብስበው ባደረጉት ውይይት ላይ ሰሞኑን እየተደረገ ያለው ጥፋት ቀደም ብሎ በደህንነት መስርያቤት ተመስርቶ የነበረው የ''ኢኤንኤን'' ቴሌቭዥን ከሁለት ዓመት በፊት የሚያሳየውን የስፖርት ጨዋታ አቁሞ በኦሮሞ እና አማራ መሃል ጠብ እንዳለ ለማስመሰል የነዛው ፕሮፓጋንዳ ቅጥያ ነው ያሉ ሲሆን፣ አንድ ጊዜ ዓቢይ ታፈነ ሌላ ጊዜ ታከል ታፈነ እያሉ የሚያወሩ ከንቱ ምኞታቸውን ነው የሚነግሩን ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብልፅግና ፓርቲን እና አሁን ያለውን አመራር አስመልክተው ሲናገሩ ባለፉት ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ አሁን ያለነው የብልፅግና አመራር የእዚህን ያህል የጋራ አመለካከት ኖሮን አያውቅም ያሉ ሲሆን መስከረም 30 መንግስት የለም ሲሉ የነበሩ ለመስከረም 30 ያቀዱትን አሁን ለማፍጠን የተገደዱበት ምክንያት ባለን መረጃ መሰረት ባንዳዎቹ ከግድቡ ጋር በተያያዘ አጉራሾቻቸው ለእኛ አሁን ካልሆነ ምን ይሰራልናል ስላሏቸው  የእነርሱን ፍላጎት ለማርካት ያደረጉት መሆኑን አብራርተዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ በሰሞኑ የመንግስት ጠንካራ እርምጃዎች ሳብያ በህወሓት መንደር እና በካይሮ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል።በተለይ በአዲስ አበባ በትናንትናው ዕለት ዓርብ ሰኔ 26/2012 ዓም ፖሊስ የጀዋር መሐመድን እና የበቀለ ገርባን ቤት ጨምሮ ሌሎች ስፍራዎች ባደረገው ፍተሻ ከፍተኛ ሰነዶች እንደያዘ ነው የተሰማው።በእዚህ መሰረት ከድርጊቱ ጋር  አላቸው የተባሉ መረጃዎች ከህወሓት ጋር እና ከአንዳንድ የግብፅ ንግድ ድርጅቶች ጋር መያያዛቸው ያልተጠበቁ መረጃዎች መንግስት እጅ እንዲወድቁ ማድረጉ ተሰምቷል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በዓርብ ዕለት ማብራርያቸው ላይም ቀድሞ አሸባሪ ይል የነበረው ነው ዛሬ አሸባሪ ሲለው ከነበረው ጋር የገጠመው በማለት የጠቀሱት ይህንኑ የሚስጥር ዕቅድ በተመለከተ ጥቆማ የሚሰጥ ነው።ሃጫሉን በቁሙ ሲያራክሱት የነበሩት ናቸው ዛሬ ለእርሱ የሚቆረቆሩ መስለው ከእኛ በላይ ያዘኑ መስለው የቀረቡት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሁን ሀሳባቸው ሁሉ ጨንግፏል ብለዋል።

ግብፅ የዓባይን ድርድር አስመልክታ ይዛው የነበረው ስልት በሰሞኑ የመንግስት የውስጥ በጥባጮችን በድንገት በመቆጣጠሩ እና ሌላው ቀርቶ ያሏቸውን የውስጥ ደጋፊዎች ለማግኘት እንዳይችሉ የኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ መዘጋት ለካይሮ የስልት መቃወስ ገጥሟታል። በመሆኑም የመረጃ መስመራቸው ሁሉ ጎርፍ እንደበላው አፈር በፍጥነት እንደተሸረሸረባቸው ነው የሚሰማው። በተመሳሳይ መንገድ በህወሓት መንደርም የሆነው ይሄው ነው።ህወሓት ዛሬ  ቢጨንቃት ምሽት ላይ መያዣ መጨበጫ የጠፋው መግለጫ አውጥታለች። መግለጫው በራሱ የሚያሳየው ጉዳይ ቢኖር ግራ የተጋባ ሰው ቃላትን ሰብስቦ በአንድ ጆንያ ያጨቀው  እንጂ መሰረታዊ የመግለጫው መልዕክት በራሱ መግለጫውን ላወጣው አካልም ግልጥ አይደለም።
አሁን መንግስት ትኩረቱ በህወሓት ቀንደኛ ተጠያቂ ባለስልጣናት ላይ አነጣጥሯል።የመቀሌ ሕዝብም ከምሽት ጀምሮ እንቅስቃሴው ቀንሷል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወታደራዊ ደንብ ልብስ ለብሰው መግለጫ መስጠታቸው በራሱ ለህወሓት መልዕክት ማስተላለፋቸው መሆኑን የተረዳው የመቀሌ ሕዝብ ቁጥሩ ቀላል እንዳልሆነ የሚናገሩ አሉ። 

በመጨረሻም ሕዝቡ ህወሓት ሰልችታዋለች።ህወሓት ተወግዳ በነፃነት ከጎንደር እስከ ሞያሌ፣ ከአስመራ እስከ ምፅዋ ተንቀሳቅሶ እና ነግዶ የሚኖርበት ሕይወት ናፍቆታል።ስለሆነም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነፃ እንዲያወጣው በጉጉት እየጠበቀ ነው።በእርግጥ በውጭ ሀገር ያሉ እንደ መቀሌ እና አዲግራት ሕዝብ ውሃ ያልጠማቸው በማኅበራዊ ሚድያ ህዝቡ ከህወሓት ጋር እንደሆነ ጧት ማታ እያወሩ ነው።እነርሱ ይዘውት የወጡትን የህዝቡን ዳቦ መብያ ገንዘብ እየተምነሸነሹ በሕዝቡ ላብ እና ደም የሚቀልዱ ናቸው።ለሁሉም ግን ኢንተርኔት ከመቀሌ ነፃ መሆን በፊት ላይከፈት ይችላል።   

የደቡብ ኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ስለ ዓባይ ያዜሙት ድንቅ ኢትዮጵያዊ ዜማ ቪድዮ ይመልከቱ 

No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...