Victims of the 22-July terrorist attacks in Norway
በኡቶያ ደሴት ጥቃት ህይወታቸውን ያጡት ፎቶዎች
ጉዳያችን ዜና
በእዚህ ስብሰባ ላይ ከ600 ያላነሱ ወጣቶች የሚሰበሰቡበት ሲሆን በእዚህ ጥቃት 77 ወጣቶች በግፍ ተገድለዋል ።ከእነኝህ ውስጥ 69 ወዲያው በደሴቱ ላይ ሕይወታቸው ሲያልፍ ከእንኝህ ውስጥ 33ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነበር።
ዛሬ ሐምሌ 22/2020 ዓም እኤአ የሰማዕታቱን ዝክር ለመዘከር የኖርዌይ ብሔራዊ ቴሌቭዥን በቀጥታ ለሕዝብ እያስተላለፈ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሰራተኛ ፓርቲ ሊቀመንበር እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በደሴቷ ወጣቶቹ በሞቱበት ቦታ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡ ሲሆን ፣የሰማዕታቱ ወጣቶቹ ስም በየተራ እየተጠራ እንዲታወሱ ተደርጎ ነበር።ከእዚህ በተጨማሪ ንግግሮችም ተደርገዋል።ከንግግራቸው በኃላ የኖርዌይ ቴሌቭዥን ያናገራቸው የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር አርና ሱልበርግ ሲናገሩ ''ይህ ክስተት የዲሞክራሲ እና የምርጫ አስፈላጊነት ምን ያህል ዋጋ ያለው መሆኑንም ለማስተማር እንጠቀምበታለን'' ብለዋል።
የኦቶያ ደሴት እኤአ በ1893 ዓም በቀኝ አክራሪ ፖለቲከኛ የንስ ብራትሊ የተገዛ ንብረትነት ከቆየ በኃላ በ1933 ዓም የኖርዌይ ሰራተኛ ማኅበር ኮንፈድሬሽን ገዝቶት የሰራተኛ ማኅበሩ ንብረት መሆን ችሏል።
ወንጀለኞች ሁል ጊዜ የሚወክሉት እራሳቸውን እና የተበላሸ አእምሮአቸውን እንጂ የወጡበትን ማኅበረሰብ ፈፅሞ ሊወክሉ አይችሉም።በቭሪክም የኖርዌይን ማኅበረሰብ አይወክልም።የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ወንጀሉን የፈፀመው በቭሪክ እድሜ ልክ ተፈርዶበት በእስር ቤት ሲሆን፣በድንገቱ ልጆቻቸውን እና ወዳጆቻቸውን ያጡ ብዙ ኖርወያውያን ግን ዕለቱን በተሰበረ መንፈስ ያስቡታል።ድርጊቱ የሰውን ዘር በሙሉ የሚያሳዝን አረመኔያዊ ድርጊት ነው።
በኢትዮጵያም ሰሞኑንም ሆነ ቀደም ብለው በአክራሪ ብሔርተኞች እና ፅንፈኛ የሙስሊም እንቅስቃሴ በሻሸመኔም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ህይወታቸው ለተቀጠፈ ሁሉ የመታሰቢያ መርሃግብር ማዘጋጀት ያስፈልጋል።ክፉ ድርጊት መዘከሩ ያለፈውን ለማሰብ ብቻ አይደለም ለነገውም እንዳይደገም ለማስተማር ጭምርም ነው።ለሰማዕታቱ ዕረፍተ ነፍስ ይስጥልን።
No comments:
Post a Comment