Monday, July 13, 2020

በኖርዌይ፣ ኦስሎ እና በዙርያዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ የቀረበ ጥሪ - ለትውልድ የምትቆይ ኢትዮጵያን ለማቆየት ሁለት ሰዓታትን ለኢትዮጵያ ከመመስከር ያነሰ አይደለም።

ኢትዮጵያ ዛሬ በስሜት ከቤቱ የሚናደድ፣የሚቆጭ እና እንዲህ ቢሆን እያለ የሚያወራ ሰው አይረባትም።ወቅቱ ቢያንስ ለሀገር በአደባባይ የመመስከር እና የጋራ ድምፅን የማሰምያ ጊዜም ነው።ወቅቱ በዓለም አደባባይ ''ኢትዮጵያ ትውደም'' (ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ) እያሉ የሚሞላቀቁ 'የጉድ ትውልዶች' የታዩበትም ጊዜ ነው። 
በእዚህ ጊዜ ከቤተሰብ ጋር ወጥቶ ለኢትዮጵያ አለመመስከር ትልቅ ስህተት ነው።በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ ጋር በከተማዎች ይመላለሳሉ።ከእዚህ ጊዜያቸው ውስጥ ሁለት ሰዓታት ለኢትዮጵያ እንዲመሰክሩ ለመጪው ረቡዕ ጁላይ 15/2020 ከ 14 እስከ 16 ሰዓት ባለው ጊዜው ውስጥ ኦስሎ የሚገኘው የኖርዌይ ፓርላማ Karl Johans gate 22 / 0026 Oslo በመገኘት ለኢትዮጵያ ድምፅ እንዲሆኑ ይጠየቃሉ።






No comments:

ወቅታዊው እና መጪው የኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ምጣኔሃብታዊ እና ማኅበራዊ ሁኔታ በሶስት ርዕሶች ማጠቃለል ይቻላል።

  ፎቶ ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2017 ዓም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ መትከል ብሔራዊ ዘመቻ ሲከፍቱ። ========= ጉዳያችን ምጥን ======== በእዚህ ጽሑፍ ስር ሶስት ምጥን ርዕሶች ያገኛሉ። እነርሱም  አ...