ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, July 8, 2020

ጆሮ ጠገብ ያልሆኑ ኢትዮጵያን የተመለከቱ ዜናዎች

ሐምሌ 2/2012 ዓም (ጁላይ 9/2020)
================
ኢትዮጵያ የዓባይን ግድብ ውሃ መሙላት በሚስጥር  ጀምራለች ተባለ።

ኢትዮጵያ በሚስጥር የአባይ ግድብን መሙላት ጀምራለች ሲል ''ግብፅ እንዲፐንዳንትን'' ጠቅሶ ''ኢነርጂ ሚክስ ዶት ኮም'' ገልጧል።እንደ ድረ ገፁ ዘገባ የሱዳን እና የግብፅ ምንጮች እንደገለጡት ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት መጀመሯ ተሰምቷል ብሏል።በሌላ በኩል የግብፅ የውሃ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውሃውን እየሞላች እንደሆነ ተከታታይ መረጃዎች እንደደረሱት ነው ድረ ገፁ የዘገበው።ሆኖም የመስርያቤቱ ቃል አቀባይ መሐመድ አልሰባይ የግብፅ እንዲፐንዳንት ዘገባ አልተረጋገጠም ብለዋል።ይህ በእንዲህ እያለ የካይሮ ዩንቨርስቲ አንድ መምህር ግድቡ እየተሞላ እንደሆነ የሚያሳይ የሳተላይት ፎቶዎች ማሳየታቸውን ዘገባው ያትታል።''ኢነርጂ ሚክስ ዶት ኮም'' በናይጄርያ የነዳጅ እና ሌሎች የኃይል ምንጮች ላይ የሚዘግብ ድረ ገፅ ነው።

ሩስያ ለዓባይ ግድብ ድርድር ቴክኒካል እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኗን ገልጠች 

የሩስያ ዜና አገልግሎት ''ታስ'' ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 1/2012 ዓም እንደዘገበው ሩስያ ለዓባይ ግድብ ድርድር ቴክኒካል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጠዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርጌ ላቭሮቭ ይህንን ያሉት ከዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣የግብፅ እና የደቡብ አፍሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በቪድዮ ከተነጋገሩ በኃላ መሆኑን ታስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሜሪካም ለተደራዳሪዎቹ አገልግሎት መስጠቷን አገራቸው በበጎ እንደምታየው ገልጠው፣ሩስያም አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት እንደምትችል ተደራዳሪዎች ሊያውቁት ይገባል ካሉ በኃላ ሩስያ የግድቡ ጉዳይ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት በቀረበ ጊዜ የሁሉንም ወገኖች የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ስምምነት መደረስ እንደሚገባ መግለጧን አስታውሰዋል።

ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ለሳውዲው  የዜና ቻናል ''አል-አረብያ'' ጋር ቃለ መጠይቅ አደረጉ።
''በግድቡ ምክንያት ግብፅ እና ሱዳን ፈፅሞ ውሃ አይጠሙም'' አቶ ገዱ አንዳርጋቸው 

አቶ ገድ በእዚህ መግለጫቸው ሱዳን እና ግብፅ ፈፅሞ በግድቡ ሳብያ ጭንቀት ውስጥ ሊገቡ አይገባም ካሉ በኃላ የግብፅ የተጋነነ እና ትክክል ያልሆነ ጥያቄ መታረም እንዳለበት እና ለችግሩ መፍትሄው መነጋገር ብቻ መሆኑን ገልጠዋል።ይላል የአል-አረብያ'' የእንግሊዝኛ ድረ ገፅ።ድረ ገፁ ሌላውን የቃለ መጠይቅ ይዘት ምንም ሳያቀርብ ወደ ግድቡ ታሪክ ገብቷል።ይሄው ድረ-ገፅ የአቶ አንዳርጋቸውን ፎቶ ያወጣበት ሁኔታ ደረጃውን ያልጠበቀ እና በራሱ ከሚድያ ስነምግባር የራቀ ነው።ቻናሉ የቃለ መጠይቁን ይዘት በገፁ ላይ ይዞ ላይወጣ ቃለ መጠይቅ ያደረገው መረጃ ለማግኘት ነው ወይ? ያስብላል።ድረ ገፁ የአቶ ገዱ ፎቶ በሸራተን ሆቴል ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መግለጫ ሲሰጡ (ከፋይሌ) ብሎ የለጠፈው ፎቶ ከስር ተመልከቱት። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱን አስታወቀ 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮቪድ -19 በኃላ ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱትን አስታወቀ።አየር መንገዱ ወደ ዱባይ በረራውን ረቡዕ ሐምሌ 1/2012  የጀመረ ሲሆን ወደ ጅቡቲም በመጪው ሳምንት በረራው እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል።አየር መንገዱ አገሮች የአየር ማረፍያቸውን መክፈት መቀጠላቸውን ተከትሎ አገልግሎቱን እንደሚቀጥል ገልጦ፣በረራው በሚደረግባቸው አገሮች ያለውን የጤና መስፈርት እና ዓለም አቀፍ ደረጃ የጠበቁ መስፈርቶችን ተከትሎ አገልግሎቱን እንደሚሰጥ እና ደንበኞች ይህንኑ የተመለከተ መረጃ ከአየር መንገዱ ድረ ገፅ ላይ መመልከት እንደሚችሉ አሳስቧል።

=============
  
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
Gudayachn Multimedia, Kommunikasjon og Konsultent 


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...