ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, July 26, 2020

በኦስሎ፣ኖርዌይ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የበጎ አድራጎት ክፍል ሰሞኑን በኦሮምያ ክልል በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦ/ ተ/ ቤ/ ክርስቲያን ምእመናንን ሕይወት እና ንብረት ላይ ለደረሰው ጥፋት ከምእመናን ገንዘብ ማሰባሰብ ጀምሯል።ኢትዮጵያውያን እጃቸውን እንዲዘረጉ ተጠይቀዋል።


በእዚህ ስር እርዳታ ሊያደርጉ የሚችሉባቸው አማራጮች ማለትም   
>> እርዳታ የሚያደርጉበት ጎፈንድ-ሚ አካውንት ሊንክ ፣
>> እርዳታ የሚያደርጉበት የቪፕስ ቁጥር፣
>> የቤተ ክርስቲያኗ የባንክ ቁጥር  እና 
>> ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ለምእመናን ያስተላለፉት ትምህርታዊ ጥሪ ቪድዮ ያገኛሉ።

ሰሞኑን በተለይ ኦርቶዶክሳውያንን ላይ ያነጣጠረ፣ በኦሮምያ ክልል በተለይ በአርሲ፣በባሌ እና በሻሸመኔ በሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ሕይወት እና ንብረት ላይ በብሄር እና የፅንፍ ጥላቻ በተነሳሱ የጥፋት ኃይሎች አማካይነት በደረሰ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ እና የንብረት መውደም እስካሁን በስም የተለዩ 52 ምእመናን (ስማቸው እየተለየ ያሉ ስላሉ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል) በአሰቃቂ ሁኔታ በእነኝሁ አረመኔያዊ ድርጊት ፈፃሚዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣የጣልያን እና ፈረንሳይ አካባቢ ሊቀጳጳስ እና የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እና የበላይ ጠባቂ ዛሬ ሐምሌ 19/2012 ዓም በቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤልን ዓመታዊ በዓል (ሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል) ለማክበር ለተሰበሰቡ ምእመናን አስታውቀዋል።ብፁዕነታቸው በእዚሁ መልዕክታቸው በተመሳሳይ መንገድ በሀገረ ስብከታቸው በጣልያን እና በአካባቢው በሚገኙ ምእመናን እስካሁን 70 ሺህ ኢሮ መሰብሰቡን እና በእዚህ ሳምንትም ምእመናን ማዋጣታቸውን መቀጠላቸውን ገልጠዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በጎ አድራጎት ክፍል በእዚህ ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ ለጀመረው የገንዘብ ማሰባሰብ መርሃግብር ምእመናን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና በስካንድንቭያን አገሮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ሊቀ ጳጳስ የላኩትን መልእክት ጨምረው  መልእክት አስተላልፈዋል። 

 የተከፈተውን ጎፈንድ-ሚ ሊንክ፣የቪፕስ ቁጥር እና የቤተክርስቲያኑ የባንክ ቁጥር  ከስር ያገኛሉ የበኩልዎን አስተዋፅኦ ያድርጉ።
 

2) የቪፕስ ቁጥር = 616461 

3) የቤተ ክርስቲያኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር = 1203 19 01535

አቡነ ሕርያቆስ ዛሬ  ሐምሌ 19/2012 ዓም ለምእመናን ያስተላለፉት ትምህርታዊ ጥሪ ቪድዮ 






 

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...