ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, July 4, 2020

አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች በሰላማዊው ሕዝብ ባደረሱት ጥቃት የ166 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን መንግስት ገለጠ።ከአስመራ ሲገባ በአቦይ ስብሐት የምሳ ግብዣ የተደረገለት ኦነግ ሸኔ በዓማራ ክልል ላይ የሞከረው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።

በእዚህ ፅሁፍ ስር-   
  • በሐረር የተፈፀመ አንድ የግፍ ጥቃት የከተማው አምቡላንስ ባለመምጣቱ ከፈረንሳይ በተደወለ ስልክ ህይወቱ የተረፈበትን ታሪክ እና 
  • ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ በኦሮምያ የንፁሃንን ደም የሚያፈሱትን የመከረችበት ቪድዮ ያገኛሉ።

ባሳለፍነው ሳምንት መጀመርያ ላይ በተወዳጁ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ በግፍ ከተፈፀመው ግድያ ተከትሎ በኦፌኮ አባላት በጀዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ እንዲሁም በኦኤምኤን ቅስቀሳ በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮምያ ክልል እና በአዲስ አበባ የፀጥታ ችግር መፈጠሩ እና በመቀጠልም ጀዋር እና በቀለ ገርባን፣1084 ሰዎች መታሰራቸው እና እስካሁን የ166 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን ኮማንደር ግርማ ገላን የኦሮምያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሰጡት ቃል ገልጠዋል።እንደ ኮማንደሩ ገልጣ 10ሩ ሰላማዊ ሰዎች በአዲስ አበባ የሞቱ ሲሆን፣145ቱ ደግሞ በተለያዩ የኦሮምያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ የፅንፈኞች ጥቃት ሳብያ ህይወታቸውን ያጡ መሆናቸው እና 11 ከፀጥታ ኃይሉ ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጧል።

በሰሞኑ ክስተት በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት በርካታ መረጃዎች ስላልወጡ እንጂ በሐረር፣ዝዋይ፣ሻሸመኔ፣ሞጆ፣ምዕራብ ሸዋ እና አርሲ  ውስጥ ምንም ዓይነት ፖለቲካ የማያውቁ ከሁለት ትውልድ በላይ የኖሩበት ከተማ በግፍ የተገደሉት ቁጥር ብዙ እንደሆነ ነው የሚነገረው ። ለምሳሌ የእዚሁ ዜና አዘጋጅ በሐረር የተፈፀመው ግፍ እንደምሳሌ ያቀርባል።በእዚህ በያዝነው ሳምንት ውስጥ በሐረር አራተኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ኮንደሚንየም በግል ስራው የሚተዳደረው የቤተሰብ ኃላፊ ላይ የደረሰው ግፍ ጉዳዩን በሚገባ ከሚያውቀው ሰው ሰምቷል።ግለሰቡ በእዚሁ በሐረር ከተማ አራተኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያለው ኮንደሚንየም ነዋሪ ነው ።ግለሰቡ ከአዲስ አበባ ሊጠይቁት የመጡትን ዘመዶቹ ጋር ቤቱ ተቀምጦ እያወራ ነበር። ባለፈው ሮብ በድንገት ሁለተኛ ፎቅ የሚገኘው ቤቱ መስኮቱን ሰብረው እቤት ውስጥ ያሉትን ሰዎች ከባለቤቱ ጨምሮ በግፍ ይቀጠቅጧቸዋል።በመሃል ስልክ ወደ አምቡላንስ እና ወደ ፖሊስ  ቢደውሉ፣ የሚደርስ የለም።በመሃል ፈረንሳይ ሀገር የምትኖር እህቱ ደውላ አደጋ ላይ መሆናቸውን ሰምታ አዲስ አበባ እና ሌላ ቦታ የሚኖሩ ለምታውቃቸው ደውላ በብዙ ስልክ አምቡላንስ እንደደረሰለት ሰምተናል።አሁን ባለው ሁኔታ አንዳንድ የኦሮምያ ፖሊስ አባላት እና ኃላፊዎች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እያዩ እንዳላዩ የሚያዩ እንዳሉ እየተነገረ በመሆኑ የእዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈፅሙትን መንግስት ተከታትሎ ለሕግ ማቅረብ አለበት። 

ይህ በእንዲህ እያለ ከሁለት ዓመት በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በአቦይ ስብሐት የምሳ ግብዣ የተደረገለት የኦነግ ሸኔ ቡድን ወደ ዓማራ ክልል በባቲ ከተማ በመግባት በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ሊፈፅም የነበረው ጥቃት በመከላከያ እና በዓማራ ክልል ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የዓማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 27/2012 ዓም ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ገልጠዋል። በእዚሁ መግለጫቸው ላይ አቶ ተመስገን እንዳብራሩት የሽብር ቡድኑ የአዲስ አበባው ጥፋት ቅጣይ መሆኑን እና የቡድኑ መሪ ጨምሮ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን እና የቀረዑት ከሙሉ ትጥቃቸው ጋር መያዛቸውን ነው የገለጡት።በመጨረሻም አቶ ተመስገን መንግስት በቀጣይ የሸረሪት ድሩ ላይ ብቻ ሳይሆን በሸረሪቱ ላይ አትኩሮ እንደሚሰራ  ነው የገለጡት።

በመጨረሻም ሰሞኑን በውጭ የሚኖሩ የህወሓት፣ኦነግ ሸኔ እና የጀዋር ደጋፊዎች በአንድነት የተለያዩ የማኅበራዊ ሚድያ ገፆች እየከፈቱ የተለያዩ የጥላቻ ቪድዮዎች እየለቀቁ ሲሆን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ለመንግሥታቱ የጥላቻ ንግግሮች የሚዘሩትን እየጠቆሙ እንደሆነ ነው የተነገረው።ጉዳዩን በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችም በቀጥታ ላሉበት መንግስት የጥላቻ ንግግር የሚዘሩትን ከመጥፎ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማመልከት ይገባቸዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም አዲስ አበባ ያሉትን ኤምባሲዎች በጉዳዩ ዙርያ ቢያነጋግር እና ጉዳዩን ቢከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ በዘረኝነት የጥላቻ ንግግር የሚያልቀውን ሕዝብ ለመታደግ እንደሚጠቅም ማሰብ ተገቢ ነው።

ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ በኦሮምያ የንፁሃንን ደም የሚያፈሱትን የመከረችበት ቪድዮ 

 


No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...