ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, June 30, 2018

ሰበር ዜና በጋምቤላ ክልል ሜጢ ከተማ እና ዙርያዋ በአማራ ተወላጆች ላይ እልቂት ሊፈፀም ነው መንግስት እንዲደርስ እየተጣሩ ነው (ጉዳያችን ልዩ ዜና Gudayachn Exclusive News)



ጋምቤላ ክልል
ጉዳያችን ልዩ ዜና (Gudayachn Exclusive Breaking News) 
ሰኔ 23፣2010 ዓም (ጁን 30፣2018 ዓም)

  • አሁን ያንዣበበው የሞት አደጋ እንዲቀረፍ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ለሚጠይቀው ሕዝብ መንግስት በሰዓታት ውስጥ እንዲደርስለት ተማፅኖ እየቀረበ ነው።
  • በአካባቢው ያሉ በኢንቨስተርነት የቡና እርሻዎችን የተቆጣጠሩ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች በአማራ እና መዥንገር መሃል ጠብ በመዝራት ነዋሪዎች እየከሰሷቸው ነው።
  • ለልዩ ልዩ ሥራ የሄዱ የትግራይ ተወላጆች በኢንቬስተር ስም ወደ ስፍራው የመጡ የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች ከተግባራቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል።
  • የቀድሞ ታጋዮች ከአማራ ተወላጆች ተደብቀው የመዥንገር ተወላጆችን ጠርተው ያደረጉት ምስጢራዊ ስብሰባ ተደርሶበታል።

ሰላማዊው ክልል እንዴት ታመሰ?

የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከሃያ ሰባት አመታት በፊት ሰላማዊ ብቻ ሳይሆን ደርግ በ1977 ዓም በሀገራችን በተከሰተው ድርቅ ሳብያ ከወሎ እና ትግራይ ሰፋሪዎች በማምጣት ያሰፍርበት የነበረ ቦታ ነው።ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ግን አካባቢው በጎሳ ፖለቲካ ሆን ተብሎ እንዲታመስ በህወሓት እና ኢህአዴግ ተፈርዶበታል።ጉዳዩ መልኩን ቀይሮ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ግጭት መነሻ እንዲሆን ያደረገው አንዱ እና አይነተኛ ምክንያት የቡና አምራች አካባቢዎችን ለመቆጣጠር የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች መሬት በመውሰድ እና በመንጠቅ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የኖሩ የአማራ ተወላጆችን ለዘመናት አብረው ከኖሩት ከመጀንገር እና ሸኮ ብሔር ጋር ግጭት እንዲፈጠር ሆን ተብለው መሰራታቸው ይታወሳል።በእዚህም ሳብያ እስከ አለፈው ዓመት ድረስ ሶስት ያህል አሰቃቂ ግጭቶች ተፈጥረዋል።በሁሉም ግጭቶች ላይ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ የህወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት በባህላዊ መልክ የታረቀውን ማኅበረሰብ ሁሉ መልሰው ወደግጭት እንደመሩት ከቦታው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ለጉዳያችን ከታማኝ ምንጭ የደረሳት ዛሬ ያኮበኮበው የሞት አደጋ

ሰሞኑን  በእሊባቦር፣ሜጢ ከተማ በኢንቨስተርነት ስም የመጡ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች (ባብዛኛው ነዋሪውን የአማራ የቡና እርሻ ከመዠንገር ጋር እያጋጩ የነጠቁት ናቸው) ሚስጥራዊ ስብሰባ ከመዥንገር ጋር መደረጉ የተሰማው ስብሰባው እንዳለቀ ነበር።ቀደም ብሎ እነኝሁ ኢንቨስተር ተብዬ የቀድሞ ታጋዮች በቦቴ ነዳጅ ጫኝ መኪና ውስጥ እየደበቁ  ክላሽ እንዲታጠቅ ያደረጉት የመዥንገር ተወላጅ ስብሰባው ላይ የተነገረው ''አማራ ሊወረው እንደሆነ፣በያዘው መሳርያ እንዲፈጀው'' የሚል ማሳሰብያ እንደነበር ከስብሰባው የወጡ መረጃዎች ለአማራ ተወላጆች ይደርሳል።ይሄንኑ እኩይ ተግባር ከአማራው ጋር አብረው በጉርብትና እና ተባብረው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችም በሃዘን ይሰማሉ።ጉዳይ የአማራ ተወላጆች ጋር እንደደረሰ በሁሉም በኩል የትጥቅ ዝግጅት ተደረገ።ልብ በሉ በእዚህ ሁሉ መሃል በግጭቱ የሚያተርፉ የመሰላቸው በኢንቨስተርነት የመጡ የቀድሞ ታጋይ የህወሓት አባላት ናቸው።

ከእዚህ በፊት በቦታው ላይ በርካታ የአማራ የቡና እርሻ ባለይዞታዎችን ምንም  በማያውቁት ጉዳይ ግንቦት 7 ወዘተ እያሉ እስከ ቂልንጦ ድረስ ያሳሰሯቸው ግለሰቦች የቡና እርሻቸውን ተነጥቀው ባዶ እጃቸውን እንደቀሩ ዜናው ያብራራል።ሰሞኑን ይህ ውጥረት ከመፈጠሩ በፊት የተከሰተው ጉዳይ ቢኖር እነኝህ በግፍ የታሰሩ የአማራ እና በግጭት አሉበት ተብለው የታሰሩ የመዥንገር ብሔር ተወላጆች በዶ/ር አብይ የምህረት አዋጅ ብዙዎች እየተፈቱ ግፍ ወደ ተሰራባቸው አካባቢዎች መመለሳቸው ነበር።የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ይህንን ግጭት ያቀናበሩትም ከሰሩት ግፍ ስጋት እና የለውጥ ሂደቱን እንዲያደናቅፉ ከተሰጣቸው መመርያ አንፃር እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ወደ ስብሰባው ጉዳይ እንመለስ እና በእዚህ ሳምንት የተደረገው ምስጢራዊ ስብሰባ በኢንቨስተር ስም ባሉት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች እና በመዥንገር መሃል የተደረገው ሚስጥር ከወጣ በኃላ እና በቦቴ እየተደበቀ ለመዥንገር መሳርያ ከታደለ በኃላ ዛሬ ቅዳሜ ጦርነቱ ሊከፈት ቀጠሮ ተይዞ እያለ የመከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ኃይል ቀድሞ ሜጢ ከተማ ገቡ።ዛሬ የነበረው የቅዳሜ ገበያም ሳይደረግ ህዝቡ እንደጠፋጠጠ እንደሚገኝ እና ሌሊትም ውጥረቱ እንዳለ ለጉዳያችን ከታማኝ ምንጭ የደረሰው ልዩ ዜና ያብራራል።

መፍትሄው

ከላይ በጥቂቱ ለመግለጥ እንደተሞከረው የአካባቢው ግጭት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መልክ ከመያዝ አልፎ በሰሞኑ በሀገራችን ያለው የለውጥ ማዕበል ያላስደሰታቸው ወገኖች ደም እንደ ጎርፍ የሚፈስበት አንዱ የጥፋት ግንባር ለማድረግ አሰፍስፈዋል።ስለሆነም መግስት የሚከተሉትን ተግባራት በአፋጣኝ መውሰድ አለበት። እነርሱም : -
1ኛ) የደረሰው የመከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ኃይል ቶሎ ለቆ እንዳይሄድ እና ለረጅም ጊዜ በከተማዋ እና በአካባቢው እንዲቆይ እንዲደረግ፣
2ኛ) በአካባቢው ግጭት የሚፈጥሩት በኢንቨስተር ስም የመጡ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች እና በስልጣን ላይ ያሉ የአካባቢው ባለስልጣናት  ውስጥ በግጭቱ ላይ እጃቸው ያለበት በቶሎ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እና
3ኛ) በአማራ፣በመዥንገር እና ሸኮ ሽማግሌዎች መሃል የሚያጋጩትን ባልጨመረ መልኩ ልዩ ውይይት እንዲደረግ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ጥቅምን ባማከለ መልክ እንዲፈቱ ሆኖ በባህላዊ እርቅ እንዲፈፀም ላለፈውም የካሳ ክፍያ እንዲፈፀም ማድረግ ይገባል።
ለማጠቃለል ግን አሁን ያንዣበበው የሞት አደጋ እንዲቀረፍ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ለሚጠይቀው ሕዝብ መንግስት በሰዓታት ውስጥ እንዲደርስለት ተማፅኖ እየቀረበ ነው።



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...