ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, June 5, 2018

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያሳለፈውን ውሳኔ በተመለከተ የጉዳያችን ማስታወሻ

የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ 
በእዚህ ፅሁፍ ስር የሚከተሉትን ነጥቦች ያገኛሉ 

  •   የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል ባለ ሀብትነት የማዞሩ ሂደት በተመለከተ፣
  • የመንግስት ድርጅቶች ወደ ግል በከፊል እና በሙሉ የማዞር ጉዳይ የሚያመጣው አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅኖዎች፣
  • የዛሬው የኢህአዴግ ውሳኔ በርካታ ጥያቂዎች ይዟል፣
  • የውጭ ባለ ሀብት ሁሉ ጠላት ነው የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ፣
  • የባድሜ ጉዳይ እና የኢትዮ- ኤርትራ ግንኙነት፣
  • በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እአአ ታህሳስ 12/2000 ዓም የተደረገው ስምምነት አንቀፆች (Agreement Between Eritrea and Ethiopia signed in Algiers, 12 Dec. 2000)


ጉዳያችን/Gudayachn
ግንቦት 29/2010 ዓም (ጁን 6/2018 ዓም)

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግንቦት 28/2010 ዓም በጠራው ስብሰባ ላይ በሁለት ወሳኝ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።ውሳኔዎቹ ሁለት ሲሆኑ የመጀመርያው ከእዚህ በፊት ሙሉ በሙሉ በመንግስት እጅ የነበሩ ዋና ዋና ድርጅቶች ማለትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣መብራት ኃይል እና ቴሌን ጨምሮ በብዛኛው በመንግስት ይዞታ ስር ሆነው ቀሪው ድርሻ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች በአክስዮንነት እና ሌሎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንዲሰጡ የሚል እና ሁለተኛው ከኤርትራ ጋር የነበረው ግንኙነት ለማሻሻል የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ወደ ተግባር መቀየር የሚሉ ውሳኔዎች ናቸው።የአልጀርሱን ውሳኔ በተመለከተ የባድመን ለኤርትራ መሰጠት ያጠቃልላል።

የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል ባለ ሀብትነት የማዞሩ ሂደት በተመለከተ

የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል (የግል የሚለው እራሱ ብዙ መብራራት ይፈልጋል) የማዞር ጉዳይ በሁለት አካላት ሲቀነቀን ዓመታት አሳልፏል።የመጀመርያው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የምዕራቡ ዓለም ሲሆን በሌላ በኩል በሀገር በቀሉ ባለሀብቶች ነው።የምዕራቡ ዓለም ኢትዮጵያ ላለፉት አርባ ዓመታት በመንግሥትነት የተያዙ ትልልቅ ድርጅቶች በተለይ የስልክ፣አየርመንገድ እና መብራት መያዛቸው ለሌላ የአፍሪካ ሀገሮች ምሳሌ እንዳይሆን ትልቅ ስጋት አለባቸው።ለምሳሌ የባንክ ሴክተሩን ብንመለከት የውጭ ሀገር ባንክ ፈፅሞ ያልገባባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።ይህ ደግሞ በእራሱ ይዞ የሚመጣው በጎ እና በጎ ያልሆኑ እድሎች አሉ።የአፍሪካ የአሁኑ ምጣኔ ሀብት ባብዛኛው የተያያዘው ከቀድሞ ቅኝ ገዢዎቻቸው ጋር የተጣመረ ነው።ይህም በመሆኑ ፖለቲካውም በእነኝህ አካላት በቀላሉ እንዲዘወር አድርጎታል።ይህ ሁኔታም ለብዙ የአፍሪካ ሀገሮች የምጣኔ ሀብት እና የፖለቲካ ፖሊሲያቸውን በሚፈልጉት መልክ እንዳይቀርፁ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።

የመንግስት ድርጅቶች ወደ ግል በከፊል እና በሙሉ የማዞር ጉዳይ የሚያመጣው አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅኖዎች 

ቁልፍ የምጣኔ ሀብት አውታሮች ለምሳሌ የመብራት፣አየር መንገድ፣ባህር ትራንዚት፣ቴሌ የመሳሰሉት ድርጅቶች በመንግስት ቁጥጥር ስር በዋናነት መያዛቸው አስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት እነኝህ አውታሮች ለሁሉም ባለ ሀብት እና ለሕዝብ እኩል ካለምንም አድልዎ ማዳረስን የመንግስት ያህል የለም ከሚል እሳቤ ነው። ይህ ማለት በፖሊሲ ደረጃ ለምሳሌ ቴሌ አገልግሎቱን የሚሰጠው ትርፍ በሚያገኝበት በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ትርፍ በማያገኝበት እንደ ማጂ ዞን ያሉ የጠረፍ ቦታዎች ሁሉ ከአዲስ አበባ የሚያገኘውን ትርፍ በማካፈል አገልግሎቱን ያዳርሳል።ሆኖም ግን ሙሉ በሙሉ በግል ድርጅቶች እጅ ከወደቀ ግን ትርፍ የሚገኝበት ቦታ ላይ ብቻ እንጂ ገጠራማ ቦታዎች አገልግሎቱን ለማግኘት አይችሉም።የብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ያልተመጣጠነ የአካባቢ እድገት የሚያጋጥመው አንዱ የግል ዘርፉ በቁልፍ የምጣኔ ሀብቶች ላይ የወሳኝ ሚና ሲኖረው እና ትርፍ ብቻ ያለመ ፖሊሲ ምስኪኑን ያገለለ ይሆናል። ይህ ብቻ አይደለም የግል ባለሀብቱ የውጭ ባለ ሀብት ከሆነ የመጣበት ሃገርን ፖለቲካዊ ተፅኖ አስፈፃሚ የመሆኑ አጋጣሚ ቀላል አይደለም።ለእዚህም ነው በርካታ የዓለም አቀፍ የንግድ ድርጅቶች በታዳጊ ሀገሮች ውስጥ ገብተው የሚያደርጉት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ለመንግሥታት መቀያየር ምክንያት የሚሆኑበት ሁኔታ ቀላል አይደለም።

ከላይ ከተጠቀሰው የግል ባለ ሃብቱ አሉታዊ ገፅታ በተለይ በሌሎች አፍሪካ ሀገሮች በምሳሌነት ናይጀርያ እና ኮንጎን መጥቀስ ይቻላል፣በኢትዮጵያ እንዳይደገም የግሉን ዘርፍ በተለየ አቀራረብ ማሳተፍ ይቻላል።የናይጀርያ እና የዛየር ሀብት ለድሃው ለምን አልደረሰም? ለምንድነው የተረጋጋ መንግስት እንዳይኖራቸው የሆነው? የውጭ ባንኮች እና ባለመዋለ ንዋይ አፍሳሾች በመንግሥታት አለመረጋጋት ዙርያ ሚናቸው ምንድነው? የሚሉት ሁሉ በሚገባ ቢፈተሹ በርካታ ጉዳጉድ የያዘ ታሪክ አፍሪካ ተሸክማለች።

በሌላ በኩል ግን የግል ባለ ሃብቱ በቁልፍ የምጣኔ ሀብት ድርጅቶች ላይ መሳተፍ ይዞ የሚመጣው ሶስት መልካም ነገሮች አሉ።እነርሱም የቴክኖሎጂ ሽግግር፣የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት እና የመዋለ ንዋይ መሳብ ነው። እነኝህ መልካም ዕድሎች ግን ዕድል ሊሆኑ የሚችሉት ከሙስና የፀዳ፣የሀገሩን ርዕይ የሚያስቀድም እና ትክክለኛ ፖሊሲ የቀረፀ መንግስት ወደ ስልጣን ላይ ሲመጣ ብቻ ነው።እዚህ ላይ ሲንጋፖር፣ቦትስዋና እና ደቡብ ኮርያን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል።እነኝህ ሀገሮች የግል ባለ ሃብትን ከምዕራቡ ዓለም ቢስቡም ትክክለኛ የቀረጥ ገቢ ለመንግሥታቸው በማስገባት እና የገባውን ገንዘብ ከሙስና በፀዳ መልክ በትክክል ለሕዝብ ልማት በማዋል የግል ባለሀብቱን ሚና ተጠቅመውበታል።በተቃራኒው ዋልጌ እና በሙስና የተነከሩ መንግሥታት ያላቸው እንደ ናይጄርያ እና ኮንጎ ያሉ መንግሥታት ከውጭ ባለሀብቶች ጋር የማይገባ ግንኙነት እያደረጉ ሀገራቸውን ለበለጠ ድህነት እየዳረጉ ይገኛሉ።

የዛሬው የኢህአዴግ ውሳኔ በርካታ ጥያቂዎች ይዟል

ከላይ ከተጠቀሰው  የግል ዘርፍ እና የመንግስት ግንኙነት አንፃር የዛሬው የኢህአዴግ ውሳኔ በብዙ ጥያቄዎች የታጀበ ነው።ከጥያቀዎቹ ውስጥ
- የእዚህ አይነቱ አቅጣጫ ቀያሪ ውሳኔ ሲደረግ ሕዝብ ቀድሞ እንዲወያይበት ለአደባባይ ማቅረብ አይገባም ነበር ወይ?
- በጉዳዩ ዙርያ የባለሙያ ጥናት በተለይ ከትርፍ እና ኪሳራ አንፃር ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ታሪካዊ እና ባህላዊ እሴት አንፃር መታየት ያሉባቸው ጉዳዮች ታይተዋል ወይ?
- የእዚህ አይነት ውሳኔ ከሁለት ዓመት በኃላ በሚኖር ምርጫ ፓርቲዎች የሚያቀርቡት የውድድር አጀንዳ መሆን አይገባውም ነበር?
- እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ የሀገር ምልክት የሆኑ ድርጅቶችን በቀላሉ በውጭ ሀገር ባለሀብቶች እጅ ማስገባት የሚያመጣው ጉዳት ተጠንቷል?
- የመገናኛ ብዙሃን በታፈኑበት ሀገር የውጭ ባለ ሀብት ምን ያህል የሀገር ሕግ አክብሮ እየሰራ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ለሕዝብ የሚነግር በሌለበት ሀገር የውጭ ባለ ሀብቶች ከባለስልጣናት ጋር የሚሰሩትን ህገ ወጥ ተግባር ለሕዝብ ማን ይነግረዋል?
- የፓርላማ አባላት እና ፓርላማው እራሱ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎች የመረዳት፣የመተንተን እና ተከራክረው ሕግ የማስቀየር አቅም አላቸው ወይ?
- ከሀገር ውስጥ የሚመጣው ባለ ሀብት ምንጩ የተዘረፈ ገንዘብ ከሆነ በትክክለኛ መዋለ ንዋይነት ይታያል? የሚሉት እና በርካታ ጥያቄዎች ማንሳት ይቻላል።

የውጭ ባለ ሀብት ሁሉ ጠላት ነው የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ

የውጭ ባለ ሀብት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አውታር ላይ የሚገባበት በጎ እና በጎ ያልሆኑ ሁኔታዎችን በምናነሳበት ጊዜ ግን ያማንክደው የእኛ የኢትዮጵያውያን ማስተካከል የሚገባን የውጭ ባለ ሀብት ሁሉ ጠላት ነው የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ አለ።ኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብቷን ለውጭው ዓለም በሚገባ እንዳልከፈተች በጣም ግልጥ ነው።እዚህ ላይ የሀገር ውስጥ ተወላጆች በሚገባ በሥራ ሳይሰማሩ የውጭ ባለ ሀብት ሊመጣ አይገባም ከሚለው እስከ አንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ሱቅ ከፍቶ ስመለከት ሃገሩን ተቆጣጠሩት እስከሚለው አስተሳሰብ ብዙ መታረም ያለባቸው አስተሳሰቦች አሉን።ይህንኑ ሃሳብ ወደ ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ያህል ጥልቀት በንግድ ዘርፍ ተሰማርተው የሀገራቱን ሕጎች ተገን አድርገው እየኖሩ ነው ? ብለን ብንጠይቅ በርካቶች በእየሃገራቱ ውስጥ ተከብረው እና ታፍረው እንደሚኖሩ እንገነዘባለን።ይህ ሁኔታ ምናልባት እንደ ደቡብ አፍሪካ ባሉ ሀገሮች ችግሮች ቢገጥሙትም ባብዛኛው ለምሳሌ በኬንያ፣ዑጋንዳ፣ እና ሌሎች ሀገሮች በጥቃቅን ንግድ ዘርፎች ሳይቀር ተሰማርተው ይኖራሉ።በአሜሪካ እና አውሮፓም እንዲሁ በርካቶች በግል ዘርፉ ተሰማርተው ይኖራሉ።ይህንኑ ጉዳይ የውጭ ሀገር ዜጎች መርካቶ ውስጥ በምን ያህል ደረጃ አሉ? ብለን ብናስብ ግን አሁንም የሚሰማን ትክክል ያልሆነ ስሜት መኖሩን መካድ አይቻልም። ይህ ማለት የውጭ ባለ ሀብት ወደ ኢትዮጵያ ስንጋብዝ የእንግዳ ተቀባይ  የመሆናችንን ያህል  የሀገራችን ሕጎች በተቻለ መጠን የውጭ ሀገር ዜጋንም እንደሚመለከት ልክ የእኛ ዜጎች በውጭ ሀገር እንደሚገጥማቸው ተግዳሮት ተገብቶ የማሰብ ባህል ሊኖረን ይገባል።ይህ ሁኔታ በእራሱ ይዞ የሚመጣው በጎ የሆነም ያልሆነም ጉዳይ ቢያስከትልም የመንግስት ስርዓቱን የመቆጣጠር ሂደት ግን ሁሉንም ሊያስተካክል ይችላል።ይህ ግን አሁንም ከሙስና የፀዳ እና አቅም ያለው የመንግስት መዋቅር ያስፈልጋል።

የባድሜ ጉዳይ እና የኢትዮ- ኤርትራ ግንኙነት 

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ዛሬ ያሳለፈው ውሳኔ ውስጥ አንዱ የአልጀርሱን ውሳኔ መቀበል እና ባድመን ለኤርትራ መስጠት ላይ መስማማት የሚል ነጥብ ይዟል።የዛሬው ውሳኔ በሰጥቶ መቀበል ደረጃ ስንመለከተው ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር በሚኖራት ግንኙነት ምን ታገኛለች የሚለው አሁን ይሄ ነው ብሎ ለመገመት ያስቸግራል።አሳዛኙ ጉዳይ ግን በእርባና ቢስ ጦርነት ያለቀው ከ80ሺህ በላይ የሚሆን የሰው ሕይወት ነው።የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት በአንድ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሰሞን የጦርነቱን ምክንያት ሲገልጡ  '' ብታዩ የሚጣሉበት ቦታ እዚህ ግባ የማይባል ትንሽ ኮረብታ ቦታ ነች" በማለት ገልጠው ነበር።ጦርነቱ በሁለቱም በኩል የቆየ የቂም እና እብሪት መገለጫ እንጂ ሌላ ትርጉም አልነበረውም።

አንድ ምሁር ከሁለት ሳምንት በፊት  ለሸገር ራድዮ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩ  እንዲህ ብለዋል " ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሲነጋገሩ የሚያተኩሩት ታክቲካዊ ጉዳይ እና ስነ ልቦናዊ የበላይነት ለማግኘት እንጂ ዘለቄታዊ በሆነው ስልታዊ ጉዳይ ላይ ማተኮር አለባቸው'' ብለዋል።ይህ አገላለጥ እኔ ሃሳቤን በሚገባ የምገልጥልኝ አድርጌ አየዋለሁ። የኤርትራ መንግስት ባድሜ ማግኘት ላይ ብቻ ሲያተኩር ህወሓት መራሹ መንግስትም ባድማ የእኔ ነች የሚል ስነ ልቦናዊ የበላይነት ለማግኘት ብቻ ሕዝብ ከህዝብ አለያይተው የኖሩት መንግሥታት ትልቅ ወንጀል ሰርተዋል።ህወሓት ባድመን ለመስጠት ከወሰነ ቆይቷል ሆኖም ግን  የትግራይ ህዝብንም ሆነ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲፈራ ኖሯል።አሁን በዶ/ር ዓብይ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ዘመን ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ እኔ አላደረኩትም ለማለት ዶ/ር ደብረ ፅዮን ዛሬ የባድመን መሰጠት ተስማምተው ተመልሰዋል።የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ግጭት ጉዳይ የባድሜ ጉዳይ አለመሆኑን ለመረዳት የአልጀርሱን ስምምነት መቀበል ብቻ ሰላም ላያመጣ በመቻሉ መረዳት ይቻላል።

ለማጠቃለል የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብስባ ቁልፍ የምጣኔ ሀብት አውታሮች ወደ ግል መዘዋወር ከሙስና የፀዳ፣ጠንካራ እና አቅም ያለው የሰው ኃይል ያለው መንግስት መኖር ወሳኝ ነው።በደካማ እና በሙስና የተዘፈቀ  መንግስት ውስጥ የውጭ ባለ ሀብት አስፈላጊ ቀረጥ ካለመክፈሉ በላይ የተከፈለውም ቀረጥ በትክክል ለሕዝብ ልማት አይውልም።ስለሆነም ሁሉም ዜጋ ሃገሩን ከባዕድ ወታደር ከመጠበቅ እኩል የምጣኔ ሀብት ቅርምቱን መቆጣጠር አለበት።የኢትዮጵያ ኤርትራ ጉዳይ በሌላ በኩል በአፍሪካ ቀንድ ከሚያንዣብበው የአካባቢ አረብ ሃገራት እና የውጭ ኃይሎች አንፃር ሁለቱ ሀገሮች ከመስማማት ውጭ አንዳችም አማራጭ የላቸውም። ይህ የባድሜ ስምምነት ግን የትግራይ ሕዝብ በህወሓት አዛውንት መሪዎቹ ላይ የሚነሳበት አዲስ የትግል ግንባር ሊሆን የማይችልበት ምክንያት አይታይም።

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እአአ ታህሳስ 12/2000 ዓም የተደረገው ስምምነት አንቀፆች 
Agreement Between Eritrea and Ethiopia signed in Algiers, 12 Dec. 2000.

Article 1

  1. The parties shall permanently terminate hostilities between themselves. Each party shall refrain from the threat or use of force against the other.
  2. The parties shall respect and fully implement the provisions of the Agreement on Cessation of Hostilities.

Article 2

  1. In fulfilling their obligations under international humanitarian law, including the 1949 Geneva Conventions relative to the protection of victims of armed conflict ("1949 Geneva Conventions"), and in cooperation with the International Committee of the Red Cross, the parties shall without delay, release and repatriate all prisoners of war.
  2. In fulfilling their obligations under international humanitarian law, including the 1949 Geneva Conventions, and in cooperation with the International Committee of the Red Cross, the parties shall without delay, release and repatriate or return to their last place of residence all other persons detained as a result of the armed conflict.
  3. The parties shall afford humane treatment to each other's nationals and persons of each other's national origin within their respective territories.

Article 3

  1. In order to determine the origins of the conflict, an investigation will be carried out on the incidents of 6 May 1998 and on any other incident prior to that date which could have contributed to a misunderstanding between the parties regarding their common border, including the incidents of July and August 1997.
  2. The investigation will be carried out by an independent, impartial body appointed by the Secretary General of the OAU, in consultation with the Secretary General of the United Nations and the two parties.
  3. The independent body will endeavor to submit its report to the Secretary General of the OAU in a timely fashion.
  4. The parties shall cooperate fully with the independent body.
  5. The Secretary General of the OAU will communicate a copy of the report to each of the two parties, which shall consider it in accordance with the letter and spirit of the Framework Agreement and the Modalities.

Article 4

  1. Consistent with the provisions of the Framework Agreement and the Agreement on Cessation of Hostilities, the parties reaffirm the principle of respect for the borders existing at independence as stated in resolution AHG/Res. 16(1) adopted by the OAU Summit in Cairo in 1964, and, in this regard, that they shall be determined on the basis of pertinent colonial treaties and applicable international law.
  2. The parties agree that a neutral Boundary Commission composed of five members shall be established with a mandate to delimit and demarcate the colonial treaty border based on pertinent colonial treaties (1900, 1902 and 1908) and applicable international law. The Commission shall not have the power to make decisions ex aequo et bono.
  3. The Commission shall be located in the Hague.
  4. Each party shall, by written notice to the United Nations Secretary General, appoint two commissioners within 45 days from the effective date of this agreement, neither of whom shall be nationals or permanent residents of the party making the appointment. In the event that a party fails to name one or both of its party-appointed commissioners within the specified time, the Secretary-General of the United Nations shall make the appointment.
  5. The president of the Commission shall be selected by the party-appointed commissioners or, failing their agreement within 30 days of the date of appointment of the latest party-appointed commissioner, by the Secretary-General of the United Nations after consultation with the parties. The president shall be neither a national nor permanent resident of either party.
  6. In the event of the death or resignation of a commissioner in the course of the proceedings, a substitute commissioner shall be appointed or chosen pursuant to the procedure set forth in this paragraph that was applicable to the appointment or choice of the commissioner being replaced.
  7. The UN Cartographer shall serve as Secretary to the Commission and undertake such tasks as assigned to him by the Commission, making use of the technical expertise of the UN Cartographic Unit. The Commission may also engage the services of additional experts as it deems necessary.
  8. Within 45 days after the effective date of this Agreement, each party shall provide to the Secretary its claims and evidence relevant to the mandate of the Commission. These shall be provided to the other party by the Secretary.
  9. After reviewing such evidence and within 45 days of its receipt, the Secretary shall subsequently transmit to the Commission and the parties any materials relevant to the mandate of the Commission as well as his findings identifying those portions of the border as to which there appears to be no dispute between the parties. The Secretary shall also transmit to the Commission all the evidence presented by the parties.
  10. With regard to those portions of the border about which there appears to be controversy, as well as any portions of the border identified pursuant to paragraph 9 with respect to which either party believes there to be controversy, the parties shall present their written and oral submissions and any additional evidence directly to the Commission, in accordance with its procedures.
  11. The Commission shall adopt its own rules of procedure based upon the 1992 Permanent Court of Arbitration Option Rules for Arbitrating Disputes Between Two States. Filing deadlines for the parties' written submissions shall be simultaneous rather than consecutive. All decisions of the Commission shall be made by a majority of the commissioners.
  12. The Commission shall commence its work not more than 15 days after it is constituted and shall endeavor to make its decision concerning delimitation of the border within six months of its first meeting. The Commission shall take this objective into consideration when establishing its schedule. At its discretion, the Commission may extend this deadline.
  13. Upon reaching a final decision regarding delimitation of the borders, the Commission shall transmit its decision to the parties and Secretaries General of the OAU and the United Nations for publication, and the Commission shall arrange for expeditious demarcation.
  14. The parties agree to cooperate with the Commission, its experts and other staff in all respects during the process of delimitation and demarcation, including the facilitation of access to territory they control. Each party shall accord to the Commission and its employees the same privileges and immunities as are accorded to diplomatic agents under the Vienna Convention on Diplomatic Relations.
  15. The parties agree that the delimitation and demarcation determinations of the Commission shall be final and binding. Each party shall respect the border so determined, as well as the territorial integrity and sovereignty of the other party.
  16. Recognizing that the results of the delimitation and demarcation process are not yet known, the parties request the United Nations to facilitate resolution of problems which may arise due to the transfer of territorial control, including the consequences for individuals residing in previously disputed territory.
  17. The expenses of the Commission shall be borne equally by the two parties. To defray its expenses, the Commission may accept donations from the United Nations Trust Fund established under paragraph 8 of Security Council Resolution 1177 of 26 June 1998.

Article 5

  1. Consistent with the Framework Agreement, in which the parties commit themselves to addressing the negative socio-economic impact of the crisis on the civilian population, including the impact on those persons who have been deported, a neutral Claims Commission shall be established. The mandate of the Commission is to decide through binding arbitration all claims for loss, damage or injury by one Government against the other, and by nationals (including both natural and juridical persons) of one party against the Government of the other party or entities owned or controlled by the other party that are (a) related to the conflict that was the subject of the Framework Agreement, the Modalities for its Implementation and the Cessation of Hostilities Agreement, and (b) result from violations of international humanitarian law, including the 1949 Geneva Conventions, or other violations of international law. The Commission shall not hear claims arising from the cost of military operations, preparing for military operations, or the use of force, except to the extent that such claims involve violations of international humanitarian law.
  2. The Commission shall consist of five arbitrators. Each party shall, by written notice to the United Nations Secretary General, appoint two members within 45 days from the effective date of this agreement, neither of whom shall be nationals or permanent residents of the party making the appointment. In the event that a party fails to name one or both of its party-appointed arbitrators within the specified time, the Secretary-General of the United Nations shall make the appointment.
  3. The president of the Commission shall be selected by the party-appointed arbitrators or, failing their agreement within 30 days of the date of appointment of the latest party-appointed arbitrator, by the Secretary-General of the United Nations after consultation with the parties. The president shall be neither a national nor permanent resident of either party.
  4. In the event of the death or resignation of a member of the Commission in the course of the proceedings, a substitute member shall be appointed or chosen pursuant to the procedure set forth in this paragraph that was applicable to the appointment or choice of the arbitrator being replaced.
  5. The Commission shall be located in The Hague. At its discretion it may hold hearings and conduct investigations in the territory of either party, or at such other location as it deems expedient.
  6. The Commission shall be empowered to employ such professional, administrative and clerical staff as it deems necessary to accomplish its work, including establishment of a Registry. The Commission may also retain consultants and experts to facilitate the expeditious completion of its work.
  7. The Commission shall adopt its own rules of procedure based upon the 1992 Permanent Court of Arbitration Option Rules for Arbitrating Disputes Between Two States. All decisions of the Commission shall be made by a majority of the commissioners.
  8. Claims shall be submitted to the Commission by each of the parties on its own behalf and on behalf of its nationals, including both natural and juridical persons. All claims submitted to the Commission must be filed no later than one year from the effective date of this agreement. Except for claims submitted to another mutually agreed settlement mechanism in accordance with paragraph 17 or filed in another forum prior to the effective date of this agreement, the Commission shall be the sole forum for adjudicating claims described in paragraph 1 or filed under paragraph 9 of this Article, and any such claims which could have been and not submitted by that deadline shall be extinguished, in accordance with international law.
  9. In appropriate cases, each party may file claims on behalf of persons of Eritreans or Ethiopian origin who may not be its nationals. Such claims shall be considered by the Commission on the same basis as claims submitted on behalf of that party's nationals.
  10. In order to facilitate the expeditious resolution of these disputes, the Commission shall be authorized to adopt such methods of efficient case management and mass claims processing as it deems appropriate, such as expedited procedures for processing claims and checking claims on a sample basis for further verification only if circumstances warrant.
  11. Upon application of either of the parties, the Commission may decide to consider specific claims, or categories of claims, on a priority basis.
  12. The Commission shall commence its work not more than 15 days after it is constituted and shall endeavor to complete its work within three years of the date when the period for filing claims closes pursuant to paragraph 8.
  13. In considering claims, the Commission shall apply relevant rules of international law. The Commission shall not have the power to make decisions ex aequo et bono.
  14. Interest, costs and fees may be awarded.
  15. The expenses of the Commission shall be borne equally by the parties. Each party shall pay any invoice from the Commission within 30 days of its receipt.
  16. The parties may agree at any time to settle outstanding claims, individually or by categories, through direct negotiation or by reference to another mutually agreed settlement mechanism.
  17. Decisions and awards of the Commission shall be final and binding. The parties agree to honor all decisions and to pay any monetary awards rendered against them promptly.
  18. Each party shall accord to members of the Commission and its employees the privileges and immunities that are accorded to diplomatic agents under the Vienna Convention on Diplomatic Relations.

Article 6

  1. This agreement shall enter into force on the date of signature.
  2. The parties authorize the Secretary General of the OAU to register this agreement with the Secretariat of the United Nations in accordance with article 102(1) of the Charter of the United Nations.

ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...