ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, June 6, 2018

ለኢትዮጵያውያን በሙሉ! የማኅበራዊ ሚድያ ጥሪ በመምህር እንደስራቸው አጉማሴ እስር ጉዳይ

በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ጀምሮ ለሃያ አራት ዓመታት በእስር እየተሰቃዩ ለሚገኙት አባት መምህር እንደስራቸው አግማሴ ከእስር እንዲፈቱ እና ወደ ቤተሰባቸው እንዲቀላቀሉ የማኅበራዊ ሚድያ ጥሪ ለማዘጋጀት እና በሀገር ቤት እና በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀርቧል።ሙሉ መልእክቱን ይመልከቱት።

ለኢትዮጵያውያን በሙሉ!
============
የማኅበራዊ ሚድያ ጥሪ በመምህር እንደስራቸው አግማሴ እስር ጉዳይ ይመለከታል  
===================================================================
ይህ የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው።ይህ የሰባት ልጆች አባት ሆኖ 24 ዓመታት ያህል በእስር ቤት የቆየ አባት ጉዳይ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ካላት የተክሌ ዝማሜ መምህር እና ሊቅ የ24 ዓመታት በእስር ቤት ተዘግቶባቸው ዝም እንዲሉ የተደረጉበት ጉዳይ ነው። መምህር እንደሥራቸው አጉማሴ ለ24 ዓመታት ከተዘጋባቸው እስር ቤት ተለቀው ከቤተሰባቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ድምጽዎን ያሰሙ።

ቅዳሜ ሰኔ 2/2010 ዓ.ም (June 9 /2018) በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ 2 ሰዓት እኝህ የሀገር ሀብት ዕንቊ አባት ከእስር እንዲፈቱ በትዊተር እና ፌስቡክ ዓለም አቀፍ ጥሪ ይቀርባል። ተሳታፊ ይሁኑ።

የጥሪው ዋና ዓላማ 
============
የዚህ የማኅበራዊ ሚድያ ጥሪ ዋና ዓላማ መንግሥት፣ ሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በመምህር እንደሥራቸው ላይ የተፈፀመውን ግፍ እንዲረዳ ማድረግ እና ትኩረት መሳብና በመጨረሻም መምህሩ እንዲፈቱ ግፊት ማድረግ ነው።
እርስዎ በበጎ ኅሊና በጥሪው ላይ ለመሳተፍ ይዘጋጁ እንጂ መንገዶቹን እንጠቁምዎታለን። በጥሪው ላይ የሚሳተፉባቸው መንገዶች የሚከተሉትን ይጨምራል።

ሀ) ከቅዳሜ በፊት 

1ኛ/ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀኖች ውስጥ 

** ቅዳሜ በተባለው ሰዓት ጥሪው እንደሚደረግ ፖስተሩን በመለጠፍ፣ የማኅበራዊ ሚድያውን ማንቃት፣ ** በፌስ ቡክ፣ በትዊተር የሚሰራጩ ፖስተሮችን፣ ቃላትን እና ዐረፍተ ነገሮችን ከአሁኑ ማዘጋጀት እና ፈጠራን መጨመር፣ 

** የሚዘጋጁት ፅሁፎች እና ፖስተሮች በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሊዘጋጁ ይችላሉ።
2ኛ) ቅዳሜ ጥሪ እንደሚደረግ የሚገልጥ መልዕክት  ለምናውቀው ሰው በኢሜል፣ በውስጥ መስመር፣ በቫይበር/ዋትስአፕ/ቴሌግራም እና በግላችን ገጾች ላይ በመለጠፍ ከቅዳሜ በፊት ባሉት ቀናት ማስታወቂያውን ማሰራጨት ፣

ለ) በዕለተ ቅዳሜ 
    =========
1ኛ) ቅዳሜ 
** በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ካለምንም እረፍት በተከታታይ የ“ይፈቱልን” ማስታወቂያውን መልቀቅ።
** መልዕክቶቹ ቀደም ብለው ያዘጋጇቸው ወይንም ሌሎች የለቀቁትን "ሼር" በማድረግ በፌስ ቡክ እና ትዊተር ገጽዎ ላይ መለጠፍ ነው።
ማሳሰቢያ መምህር እንደስራቸውን ማንነት ለማወቅ ይህንን ተጭነው ያንብቡ ።
የመምህር እንደስራቸው የመንፈስ እና የስጋ ልጆች የአባታቸውን መፈታት እየጠበቁ ነው።
አንተ አቡነ (ያሬዳዊ ዜማ ቪድዮ)

ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments: