ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, June 13, 2018

የኢትዮጵያ ሕዝብ በመጪው ዕሁድ የህወሓትን መግለጫ ተቃውሞ በመላው የኢትዮጵያ ከተሞች ሰልፍ በመውጣት ህወሓትን ማስጠንቀቅ አለበት። መቶ ሚልዮን ሕዝብ ዲሞክራሲ ወይንም ሞት! ብሎ ለመፋለም መነሳት አለበት።(የጉዳያችን መልዕክት)


ጉዳያችን/ Gudayachn
ሰኔ 7/2010 ዓም (ጁን 14/2018)
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰኔ 9/2010 ዓም ቅዳሜ የመቀሌ ሰልፍ በተደረገ ማግስት ሰኔ 10/2010 ዓም ዕሁድ በአዲስ አበባ፣ሐዋሳ፣አዳማ፣ባህርዳር፣ጎንደር፣ደሴ፣ሐረር፣ነቀምት፣ወዘተ ዲሞክራሲ ወይንም ሞት! የሚል አስገራሚ ሰልፍ በማድረግ ለሕወሐትም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከዶ/ር ዓብይ የለውጥ ሂደት ጋር አብሮ መቆሙን ማሳየት አለበት።
  • ህወሓት ወጣቱ የዓለም ዋንጫ በሚመለከጥበት ሰሞን ተቃውሞው ይቀንሳል የሚል የተሳሳተ እሳቤ ይዟል።
  • ለእዚህ አይነቱ የህወሓት  ትዕቢት የኢትዮጵያ ሕዝብ የትዕግሥቱ ልክ እንዳበቃ ማሳየት ያለበት ጊዜ አሁን ነው።

ኢትዮጵያውያን አሁን ያለንበት የእስረኞች መፈታት፣ስለ ኢትዮጵያዊነታችን በነፃነት ለመናገር፣ኢትዮጵያውያንን የሚያከብር ጠቅላይ ሚኒስትር ለማግኘት መስዋዕትነት ከፍለውበታል።እናት እልጇ አስከሬን ላይ ተቀምጣ የግፍ ፅዋ ጠጥታበታለች፣ በአንድ ቀን ከሃምሳ ያላነሱ ወጣቶች በጥይት አረር በባህር ዳር እረግፈውበታል፣ ከአምስት መቶ በላይ ወጣቶች በቢሸፍቱ በአንድ ጀንበር ብቻ በእረቻ በዓል እረግፏል፣ ድምፃችንን ስሙን ብለው የደቡብ ሕዝብ ኢትዮጵያውያን ጥይት ተርከፍክፎባቸዋል። ይህ ለውጥ በዕቃ ዕቃ ጫወታ የመጣ ለውጥ አይደለም።ይህ ለውጥ ይቅርታ፣ፍቅር እና ሕብረትን እየዘመረ የመጣው ከሰባ ሚልዮን ብር በላይ ለፕሮጀክት ሥራ ብለው እነ  ዓባይ  ፀሐዬ በተራራ ፀሐይ እንደዘረፉት ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም።ይህ ሕዝብ እህቶቹን በአደባባይ በጉዞ ወኪል ስም  የሸጡበት በእየኤምባሲው የተሰገሰጉ የህወሓት ባለስልጣናትን ሳያውቃቸው ቀርቶ አይደለም። ይህ ሕዝብ ኢትዮጵያን በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር በስሟ ተበድረው በውጭ ሀገር ባንኮች በልጆቻቸው ስም ያስቀመጡ የቡድን መሪ የህወሓት ሰዎች እንዳሉ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም።ህዝቡ ስጋውን ውጫ ለመብላት እንጂ አጥንቱን ለመብላት የተዘጋጁ ግን አልመሰለውም ነበር።

ዛሬ ግንቦት 6/2010 ዓም ህወሓት እኩይ ተግባሩን ተቃውመው የወጡትን የኢሕአዴግ ምክርቤት ውሳኔዎች የሚኮንን መግለጫ አውጥቶ ዳግም ልርገጣችሁ የሚል የተለመደ ዲስኩሩን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሲያሰማ አምሽቷል።የእስረኞች መፈታት፣የፍቅር መሰበክ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ እያደረጉ ያሉትን የለውጥ ነፋስ ምክንያት ስያጉረመርሙ የነበሩ ህወሓቶች ከአሁን በኃላ የኢትዮጵያን ሕዝብ  በምንም አይነት ለመረገጥ እንዳልተዘጋጀ ሊያውቁት ይገባል።በአሁኑ ሰዓት ህወሓት የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካ  ቀዳሚ የፀጥታ ስጋት ሆኗል።There is no an immediate danger, other than TPLF for the peace and stability of the horn of Africa. ስለሆነም ከኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ጎን የቆመው የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይህንን የሰላም ስጋት የሆነ ህወሓት ካልተወገደ በምንም አይነት በኢትዮጵያ ሰላም እንደማይሰፍን ለመጨረሻ መጨረሻ ጊዜ ተረጋግጧል። ስለሆነም  
ለእዚህ አይነቱ የህወሓት  ትዕቢት የኢትዮጵያ ሕዝብ የትዕግሥቱ ልክ እንዳበቃ ማሳየት ያለበት ጊዜ አሁን ነው።የመጀመርያ እርምጃው መሆን ያለበት እርስ በርሱ ለማጋጨት ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር የሚርመሰመሱትን የወያኔ ወኪሎች  በቀጥታ በማጋለጥ እና ለሕግ በማቅረብ አደብ ማስያዝ አለበት።የትግራይ ሕዝብ ህወሓት ይህንን ያህል ለበለጠ ወንጀል የሚዘጋጀው በቡድን ዝርፍያ ውስጥ ስለገባ በወንጀል ስለሚጠየቅ ትግራይ ሕዝብ ውስጥ ገብቶ ለመደበቅ እንደሆነ ማወቅ አለበት። ከቡድን ዘራፊ ጋር ለመቆም የሚፈልግ መብቱ ነው።ፅዋውንም ለመጠጣት አብሮ መዘጋጀት አለበት። 

በመጪው ቅዳሜ ይደረጋል የተባለው የመቀሌ ሰልፍን በራሱ የመቀሌ ነዋሪዎችም ደግመው ሊያስቡት የሚገባ ህወሓት በበርካታ የዝርፍያ እና የግድያ ወንጀል ውስጥ የገባ ቡድን ነው።በ21ኛው ክ/ዘመን የእንደዚህ አይነት ቡድንን ደግፎ በመሰለፍ የሚገኝ ትርፍ ሳይሆን አደገኛ ኪሳራ ነው።


የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰኔ 9/2010 ዓም ቅዳሜ የመቀሌ ሰልፍ በተደረገ ማግስት ሰኔ 10/2010 ዓም ዕሁድ በአዲስ አበባ፣ሐዋሳ፣አዳማ፣ባህርዳር፣ጎንደር፣ደሴ፣ሐረር፣ነቀምት፣ወዘተ ዲሞክራሲ ወይንም ሞት! የሚል አስገራሚ ሰልፍ በማድረግ ለሕወሐትም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከዶ/ር ዓብይ የለውጥ ሂደት ጋር አብሮ መቆሙን ማሳየት አለበት።በተመሳሳይ መልኩ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመጪው ሳምንት ህወሓትን የሚያስጠነቅቅ ዓለም አቀፍ ሰልፍ ማዘጋጀት አለባቸው።ዓለሙ ከኢትዮጵያ ጋር ነው።ህወሓት በትክክል እኩይ ስራው የበለጠ ይጋለጣል። አሁንም ዲሞክራሲ ወይንም ሞት! ሞት ለዲሞክራሲ ፀሮች እና ዘረኞች! መሪ መፈክራችን ነው።



ያመናል በለው።

  
ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments: