ጉዳያችን /Gudayachn
ሰኔ 5/2010 ዓም (ጁን 12/2018 ዓም)
በእዚህ ፅሁፍ ስር : -
1ኛ) ዶ/ር ጃን ኤርክ ከሊደን ዩንቨርስቲ በፈድራሊዝም እና ያላማከለ አስተዳደር ከኢትዮጵያ በሚል
የሰጡት ማብራርያ ቪድዮ እና
2ኛ) የሐረርወርቅ ጋሻው ለአውስትራሊያው ሲቢኤስ ራድዮ የጎሳ ፈድራልዝምን አስመልክተው
የተናገሩት ቪድዮ ያገኛሉ።
በኢትዮጵያ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌድራሊዝም ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያ ልትደርስበት ከሚገባት የእድገት ደረጃ በምን ያህል ወደ ኃላ እንዳስቀራት ቢጠና በሩብ ክፍለዘመን ውስጥ መድረስ ከሚገባን የዕድገት ደረጃ በእጅጉ እንደተጎተትን ለመረዳት ይቻል ነበር። ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌድራሊዝም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ ከቀዬው አሰድዷል፣ሺዎች ተገድለዋል፣ቤተሰብ ተበትኗል። ፈድራሊዝም በራሱ የእድገት ፀር አይደለም።ፈድራሊዝም ሕዝብ የእራሱን ባህል፣ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ግንኙነቱን የሚያዳብርበት እና እንዲሁም በፌድራል መንግስት ውስጥ ያለውን ኃላፊነት የሚወጣበት መንገድ ነው።ፈድራሊዝም ጎሳ እና ቋንቋን መሰረት ካላደረገ ምንን መሰረት ማድረግ አለበት? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል።
ፈድራሊዝም መሰረት ማድረግ የሚገባው እና አሁን ባለንበት ዓለም ሁሉ የሚጠቀምበት ታሪክን÷ባህልን እና መልክአምድራዊ አቀማመጥን ባማከለ መልኩ ነው።አሁን ወቅቱ የፌድራል አስተዳደር መሰረታዊ ችግሩን መፈተሽ፣መወያየት እና አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ደግሞ ህገመንግስቱ ላይም መቀየር ያለበትን እስከመቀየር መድረስ የማይቻልበት ምክንያት የለም።ይህንን ጉዳይ ለመጪ መንግስት ተብሎ የሚተው አይደለም::
ዶ/ር ጃን ኤርክ በኢትዮጵያ የጎሳ ፈድራሊዝም ታስቦበት እና ተጠንቶ የመጣ ሳይሆን በ1983 ዓም ድንገት ሽምቅ ተዋጊዎች ሲያሸንፉ የመሰረቱት መሆኑን ያብራራል።አዎን! በኢትዮጵያ ፈድራሊዝም ከሀገሪቱ ታሪክ፣ባህል፣ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር እና መልካምድራዊ አቀማመጥ ላይ ባለሙያዎች ሳያጠኑት ሕዝብ ሳይመክርበት በድንገት የተጫነ ድንገቴ ነው። ዶ/ር ጃን የኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ ሕግን መሰረት ከማድረግ ይልቅ ከሚገባው በላይ ፖለቲካዊ ስለሆነ ድህጣን ጎሳዎች መብታቸው ሊከበር እንደማይችል ያብራራል።
የሐረርወርቅ ጋሻው፣በሌላ በኩል አሁን ያለው የጎሳ ፖለቲካ ፌዴራሊዝም የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመለያየት የመጣ አደጋ ነው።ለኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት እንጂ የጎሳ ፖለቲካ ፌድራሊዝም አያስፈልጋትም ትላለች።በእዚህ ፅሁፍ ላይ ፈድራልዝም ወይንም ማዕከላዊነት ለኢትዮጵያ ይበጃል አይበጅም ለማለት ሕዝብ መምከር፣መንግስት የመመካከርያ መንገዱን ማመቻቸት እና ህገ መንግስቱን እስከመቀየርም ድረስ የሚደርስ ውሳኔ ሕዝብ እንዲወስን ማድረግ ኢትዮጵያ ወደፊት የማደግ እና አለማደግ ሁኔታ ላይ ወሳኝ ሚና አለው። ውይይቱ ግን በፍጥነት መጀመር አለበት።ብሔራዊ ጉባኤ መጠራት አለበት።ይህ ለመጪ መንግስት ተብሎ የሚቀመጥ ጉዳይ ሊሆን አይገባውም።ሕዝብ እያለቀ ነው።የበለጠ ጥፋት ደግሞ ሊከሰት ይችላል።
ከእዚህ በታች ዶ/ር ጃን ኤርክ ከሊደን ዩንቨርስቲ በፈድራሊዝም እና ያላማከለ አስተዳደር ከኢትዮጵያ አንፃር ያቀረቡትን እና ወ/ሮ የሐረርወርቅ ጋሻው ለአውስትራሊያው ሲቢኤስ ራድዮ ከጎሳ ፖለቲካ ይልቅ ማዕከላዊ አስተዳደር ይሻለናል በማለት ያቀረቡት ሃሳብ ቪድዮ በተከታታይ ከስር ያዳምጡ።ሁለቱም ቪድዮዎች እያንዳንዳቸው ከአስር ደቂቃዎች የበለጡ አይደሉም።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

ዶ/ር ጃን ኤርክ ከሊደን ዩንቨርስቲ በፈድራሊዝም እና ያላማከለ አስተዳደር ከኢትዮጵያ አንፃር
Video Source ; -Centre for Innovation - Leiden University You Tube
የሐረርወርቅ ጋሻው ለአውስትራሊያው ሲቢኤስ ራድዮ የጎሳ ፈድራልዝምን አስመልክተው የተናገሩት
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment