Friday, May 16, 2014

Free Zone 9 Bloggers And Journalists! የዞን 9 ጦማርያን፣ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ!

'''ታስሬ አልጠየቃችሁኝም'' የሚለው ቃል ትዝ ሲለኝ ወደ አዕምሮዬ የሚመጣው (በተለይ በውጭ ሀገር ላሉቱ)  -
ሰው ሲታሰር ዝም ማለት።ቢያንስ መጠየቅ ባንችል በፌስ ቡካችን ላይ ሃዘናችንን በመግለፅ ለመለጠፍ መፍራት ሃይማኖተኛነታችንን አይፈታተንም?

''ታስሬ አልጠየቃችሁኝም'' የሚለው ቃል መጠየቅ ያልቻለ ሰው እርቀት ቢያግደው ቢያንስ መጮሁ እንደጠየቀ አይቆጠር ይሆን?

''እምነት ሆይ ወዴት ነሽ? ሃይማኖት ሆይ ወዴት ነሽ? በግፍ ለታሰሩት መጮህ እኮ ሃይማኖት ነው ጎበዝ!

አሁንም ''ታስሬ አልጠየቃችሁኝም'' ሲታወሰኝ የታሰሩትን ለመጠየቅ ያልፈሩቱ ሲታሰሩ መጠየቅ ያልቻለ ከተፈረደበት ለታሰሩት  አዘንኩ ብሎ ፌስ ቡክ እና ትዊተር ላይ ለመለጠፍ የፈራ (ያውም በውጭ ሆኖ) ፍርድ የለበት ይሆን? ሰው ፈራጅ አለመሆኑ እንጂ ሲታሰብ ስራችን ከበድ ያለ ነው። ''እምነት ሆይ ወዴት ነሽ?



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments:

በጠ/ሚ/ዐቢይና ሙ/ጥ/ዲ/ዳንኤል ላይ በውሸት ወሬ የዘመቱት ''አፈ-ጊንጦች'' በቴዲ አፍሮ ዘፈን ሊሸሸጉ ሲሞክሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየሳቀባቸው ነው።

ጠ/ሚ/ዐቢይ አሕመድ እና ሙ/ጥ/ዲ/ዳንኤል ክብረት በታላቁ የዓባይ ግድብ ምርቃት ቀን። ======== ጉዳያችን ምጥን ======== አፈ ጊንጥነቱ እና የውርደት ካባው ''አፈ ጊንጥነት'' የሚለውን ...