Thursday, May 15, 2014

ዛሬ ግንቦት 8/2006 ዓም በኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም ላይ የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት 25ኛ ዓመቱ ነው።በኢትዮጵያ የቢቢሲ ዘጋቢ የነበረው አሌክስ ላስት ያልሰማናቸው ታሪኮች ይነግረናል።(ኦድዮ)

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት መንግስታቶቿ ያልተሳኩ የወታደራዊ መፈንቅል ሙከራዎች ተደርገዋል።ሶስተኛው የዘመኑ መንግስት ኢህአዲግም ከእዚህ ነፃ ይሆናል ማለት አይቻልም። አንዳንዶች የአሁኑ መንግስት የጦር ሰራዊት አወቃቀር የተለየ ነው ይላሉ።ለእዚህም የሚያቀርቡት ምክንያት አብዛኞቹ የጦሩ ከፍተኛ መኮንኖች በትጥቅ ትግል ላይ የሚተዋወቁ ብቻ ሳይሆኑ ከአንድ አካባቢ የመጡ መሆናቸውን እንደ ምክንያት ያቀርባሉ። ነገር ግን ቀድሞም ቢሆን በተለይ በ 1967 ዓም ንጉሱን ከስልጣን ያወረደው የጦር ኃይል ባብዛኛው በዝቅተኛ እና ባለመስመር መኮንኖች የተመራ መሆኑን ነው። ከእዚህ አንፃር ኢህአዲግም የተለመደ የተሳካ ወይንም ያልተሳካ ወታደራዊ መፈንቅል ሊታደል ይቻላል።ይህ በጊዜ የሚፈታ ነው።

ከእዚህ በታች በኮ/ል መንግስቱ ላይ የተሞከረው መፈንቅል ጉዳይ በወቅቱ በኢትዮጵያ የቢቢሲ ዘጋቢ አሌክስ ላስት ምስክርነትን ከእዚህ በታች ያለውን ኦድዮ ከፍተው ያዳምጡ-
አፈንዲ ስለ መፈንቅሉ በመጦመርያ ገፁ ላይ  ለመፈንቅሉ መክሸፍ ምክንያት የሚላቸው በወቅቱ የደህንነት ቢሮ ኃላፊን ኮ/ል ተስፋዬን ነው።እርግጥ ነው ሌሎች ፅሁፎች ላይ የእርሳቸው መጨረሻ ሰዓት ላይ መክዳትን በምክንያትነት ቢያስቀምጡም ሌሎች የሚሰጧቸው ምክንያቶችም አሉ።ዝርዝሩን ይህንን በመጫን ያንብቡ።



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments:

በአቴንስ፣ግሪክ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ላለፉት 40 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት የነበረውን ፖሊጎኖ የሚገኘው ቤተክርስቲያን በፖሊስ ታሸገ።የቅዱስ ሲኖዶስ አፋጣኝ ምላሽ እየተጠበቀ ነው።

የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የታሸገችበት የጉግል የእንግሊዝኛ ትርጉም እና የግሪክኛ ዋናው ኮፒ። በግሪክ አቴንስ የምትገኘው እና ወደ ግማሽ ክ/ዘመን አገልግሎት ስትሰጥ የነበረችው እና በአቴንስ ፖሊጎኖ የምትገኘው የ...