ጋዜጠኛ ተስፋለም ወደ ፍርድ ቤት እንደ ወንጀለኛ ታስሮ ሲወሰድ
''የዞን 9 ጦማርያን ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል
የዞን 9 ጦማርያንን የጊዜ ቀጠሮ ሊያይ ተሰየመው ችሎት ዛሬ ሌላ አሰቃቂ ዜና አብሮ ሰምቷል፡፡ ሁለቱ የዞን9 አባላት በፍቃዱ ሃይሉና አቤል ዋበላ በማእከላዊ መመታታቸውን እና ውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን ፓሊስ ማስረጃ የላቸውም ሲል ተከራክሯል፡፡ ለክርክሩ ምላሽም ውስጥ እግራቸውን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቶርቸር ህግ መንግስታዊ አይደለም ሲል "አስተያየቱን" ሰጥቷል፡፡ እነደትላትናው ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያቶች የተነሳ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 10 ቀናትን ለምርመራ ፈቅዶአል፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለተከሳሾቹ ጭብጨባ እና ፉጨት ማሰማት የተከለከለ ሲሆን ተከሳሾች ሲወጠ ባሳዩት አጋርነትም ከዛሬ በሁዋላ ካጨበጨባችሁ እነዳትገቡ እናደርጋለን የሚል ማስፈራሪያም ተሰጥቷል፡፡ ወ/ ሮ ስንታየሁ የተባሉ የሬጅስትራር ሰራተኛ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ለዳኛ በመንገር (በተለመደ ቋንቋ በማቃጠር) አጋርነት እያሳዩ የነበሩትን ወጣቶች ተግባር ለማስቆም ሞክረዋል፡፡
ዞን 9 በድጋሚ የዞን 9 አባላት ያወሰድዋቸው ምንም አይነት የአሸባሪነት ስልጠና እንደሌላ እያረጋገጠ በህገ መነግስቱ አንቀጽ 18 መሰረት ማንኛውም ሰው ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ ከሆነ ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው ቢልም በታሰሩ አባላቶቻችን ላይ የደረሰውን ግርፋት አጥብቆ ያወግዛል።'' ይላል ዜናው።
የዞን 9 አባላት እነማን ናቸው? ሊንኩን ከፍተው ጉዳያችን ላይ ያንብቡ።
////////////////////////////////።።።።።።።።።።/////////////////////////።።።።።።።።።።።።////////////////////
No comments:
Post a Comment