ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, May 2, 2014

ሰበር ዜና - በኤርትራ መንግስት -ሻብያ ውስጥ ቀውሱ ተባብሷል።በሱዳን፣በኬንያ፣በግብፅ እና አሁን በናይጄርያ አምባሳደር የነበሩት ሞሐመድ አሊ ኦማሮ ባለፈው ማክሰኞ አስመራ ላይ በደህንነቶች ተያዙ።

ማክሰኞ ሚያዝያ 21/2006 ዓም የታሰሩት ሞሐመድ አሊ ኦማሮ  (ፎቶ አዋቴ ዶት ኮም)

ሞሐመድ አሊ ኦማሮ ቀደምት እና ለሻብያ እንደ አንድ የድርጅቱ የረጅም ጊዜ አባል አባባል ''ዓይን'' የተባሉ ስራዎችን የሰሩ አንጋፋ ሰው እንደነበሩ ይነገራል።ግለሰቡ
- እ አ አቆጣጠር ከ 1960ዎቹ ጀምረው በሻብያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ሲያገለግሉ ነበር፣
- በጦርነቱ ወቅት የነበረው የሻብያ ራድዮ መስራች ናቸው፣
- በጦርነቱ ወቅት መቀመጫውን በሳውዳረብያ  ያደረገው የአረብ ሀገሮች የሻብያ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል፣
- አሁንም በጦርነቱ ጊዜ የሻብያ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ሱዳን ውስጥ ሰርተዋል፣
- ከጦርነቱ በኃላ በሱዳን፣በኬንያ፣በግብፅ እና ባለፈው ማክሰኞ አስመራ ላይ እስክያዙ ድረስ በናይጄርያ አምባሳደር ነበሩ።

ዜናውን የዘገበው አዋቴ ዶት ኮም (awta.com) እንደሚያብራራው በኤርትራ ውስጥ ከፍተኛ የስልጣን ሽክቻ በተለያዩ ቡድኖች መካከል  መኖሩን እና የሞሀመድ አሊ መያዝ በራሱ እንደ ድረ-ገፁ አገላለፅ ''ለዓመታት ሲንከባለል የነበረውን የተለያዩ ቡድኖች የስልጣን ሽምያ  'የሚያፈላው' ነው።'' ብሏል።

ባለፈው ሳምንት የአፋር ቀይባህር ነፃ አውጭ ግንባር በአሰብ አካባቢ የሚገኝ የሻብያ የጦር ካምፕ አጥቅቼ በርካታ ገደልኩ የጦር መሳርያም ማረኩ ማለቱ ይታወሳል።

ጉዳያችን
ሚያዝያ 24/2006 ዓም 

No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)