ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, May 1, 2020

በኮሮና ወረርሽኝ ከተጠቁት የጣልያን ከተሞች ውስጥ የሚላን ከተማ ከኢትዮጵያውያን 6ሺህ ኢሮ (ከ220ሺህ በላይ ብር) የሚያወጣ ዕርዳታ አገኘች።

Italian city, Milan, gets humanitarian aid from Ethiopians residing in the city.
በዓለማችን የኮሮና ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ ካጠቃቸው አገሮች ውስጥ ጣልያን አንዷ ነች።እስከዛሬ ሚያዝያ 23/2012 ዓም ድረስ በጣልያን 205,463 ዜጎቿ በወረርሽኙ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ ውስጥ 27,967 ሕይወታቸው አልፏል።ይህ በእንዲህእያለ በጣልያን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የጣልያን እና አካባቢው ሃገረ ስብከት ስር የምትገኘው ፈለገ ሰላም ዳግማዊ ቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ትናንት ሚያዚያ 22 /2012 ዓ.ም በሚላን ከተማ ለሚገኝው የጣልያን ቀይ መስቀል ድርጅት እርዳታ አበርክታለች።

በእዚህም መሰረት የቤተክርስቲያንዋ ካህናት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ በጣልያን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣እንዲሁም በጣልያን የነፃ ትምህርት ዕድል አግኝተው በመማር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጨምሮ በችግሩ ዙርያ በስካይፕ የጸሎትና የቃለ እግዚአብሔር መርሐግብር ላይ እየተገናኙ ባደረጉት ምክክር ሁሉም ያቅማቸውን 6ሺህ ኢሮ (ከ220ሺህ በላይ ብር) በማዋጣት አሰባስበው ለሚላኖ ከተማ ቀይ መስቀል አስፈላጊ የሆኑትን ምግቦችንና መገልገያዎችን ገዝተው ቦታቸው ድረስ ወስደው መለገሳቸውን ጉዳያችን በቦታው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ከጣልያን ቀይመስቀል ዜና ተረድታለች።ይህንንም የዕርዳታ ስጦታ የሚላኖ ፈለገ ሰላም ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ጉባኤ ቆሞስ አባ ሳሙኤል እና መላከ ብስራት አባ ገ/ሚካኤል ገብሩ የሚላኖ ፈለገ ሰላም ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጸሐፊ ከምዕመናን ጋር በመሆን በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ለጣልያን ቀይ መስቀል ማስረከባቸውን ዜናው ጨምሮ ያብራራል።

የሚላን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋህዶ ምዕመናን ያደረጉት ተግባር ትልቅ አርዓያነት ያለው ተግባር ከመሆኑም በላይ በሌሎች አገሮች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትም ሆኑ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰቦች ለአገራቸው ከሚልኩት ድጋፍ በተጨማሪ የሚኖሩበት አገር ያሉ ችግሮችን የመደገፍ ሥራ መስራታቸው የሚኖረው በጎ ተፅኖ ትልቅ ነው።በሌላ በኩል ቤተክርስቲያን የማኅበራዊ ተሳትፎዋን በእዚህ ዓይነት መልክ ማጠናከሯ የሚፈጥረው መንፈሳዊም ሆነ ሞራላዊ ጥቅም በቀላሉ የሚታይ አይደለም።የሚላን ከተማ ቀይ መስቀል ዕርዳታውን አስመልክቶ በገፁ ላይ የለጠፈው ዜና እና ርክክቡ ሲደረግ የሚያሳየው ፎቶ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...