በትግራይ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ፀረ-ህወሓት ተቃውሞዎች ሲሰሙ ነበር።ባሳለፍነው ሳምንትመጀመርያ ላይ ግን የተቃውሞ እንቅስቃሴው በነጋዴዎች በኩል ተጀመረ።ትግራይ የአንድ የህወሓት ፊውዳል ስርዓት ሰለባ ሆናለች ያሉት ነጋዴዎች፣የፖለቲካ ስልጣን ከቀበሌ እስከ ርዕሰ መስተዳድሩ ድረስ በአንድ ቤተሰብ ስር ወድቃለች ብለዋል።ፖለቲካው ብቻ ሳይሆን የምጣኔ ሃብቱም እንዲሁ በአንድ የአቦይ ስብሐት ቤተሰብ ስር መውደቁን ነጋዴዎቹ አምርረው አስታውቀዋል።ለእዚህም በማስረጃነት ነጋዴዎቹ ያነሱት የመሶበ ሲቢንቶ ምርትን እንደማሳያነት ያወሳሉ።በመሶበ ስቢንቶ ፋብሪካ ከስራ አስኪያጅ እስከ ዘበኛ የአቦይ ስብሐት ዘመዶች መሆናቸው ሳያንስ ህዝቡ በቀነሰ ዋጋ ከቀረው የኢትዮያ ክፍል ማለትም ከዳንጎቴ፣ ሓበሻ፣ ሙገር ስቢንቶ ፋብሪካዎች የሚመረተው ምርት እንዳይገበይ የተደረገው በእዚሁ የቤተሰብ ትስስር ያለበት የህወሓት አሰራር መሆኑን ነጋዴዎቹ ተቃወሙ።በመቀጠልም ትግራይን ከአንድ አምባገነን ቡድን አገዛዝ ነፃ እንናድርጋት የሚለው እንቅስቃሴ ተጀመረ።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
የትግራይ ነጋዴዎች በአመፅ ላይ (ፎቶ አምዶም ገ/ስላሴ)
የተቃውሞ እንቅስቃሴው ቀደም ብሎ በዋናነት የተነሳበት ህወሓት የትግል መነሻዋ እንደሆነ ብዙ ጊዜ የምትኩራራበት የማይሓንሰ ደደቢት ላይ ነው።በእዚህ ቦታ ያለው ተቃውሞ ከሰላማዊ ሰልፍ ባለፈ የመንገድ የመዝጋት እንቅስቃሴ ሁሉ ያጠቃለለ ነበር። በትግራይ ሰሞኑን የነበሩት ፀረ-ህወሓት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አድገው በአሁኑ ጊዜ ወደአጠቃላይ የተደራጀ የተቃውሞ እንቅስቃሴ እየተቀየረ እንደሆነ ነው የተሰማው።
በሌላ በኩል ይሄው የትግራይ ፀረ ህወሓቱ ትግል ሕዝባዊ መሰረት ከመያዙ በላይ የራሱን አመራር እንዳደራጀ ነው የሚሰማው።በእዚህም መሰረት እንቅስቃሴው ''ፈንቅል'' የሚል ስያሜ እንደተሰጠው እና ህውሃትን መፈንቀል ዋነኛ ግቡ እንደሆነ ተሰምቷል።በመሆኑም በሽሬ እንዳስላሴ እና በዋጀራት እስከ ዛሬ ድረስ ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን የህዝቡ ጥያቄ ከመሰረተ ልማት ወደ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እያደገ እና የአስተዳደር መዋቅሮች ላይ ሁሉ ላይ ጥያቄዎች መነሳታቸው ተሰምቷል።
''እኛ በውሃ ጥም እያለቅን እነርሱ ውስኪ መሯቸዋል፣ወንድሞቻችን ዛሬም በደደቢት በረሃ እና ሌሎች ቦታዎች በህወሓት ታስረው እየተሰቃዩብን ነው አሁን ግን ይበቃናል!'' ያሉት የሽሬ እንዳስላሴ ነዋሪ ነበሩ።ከእዚህ በፊት ለዓመታት በስማችን ነገዱ ከአሁን በኃላ ግን እንዲነገድብን አንፈቅድም ያሉት ሌላው የሽሬ እንዳስላሴ ነዋሪ፣በቅርቡ ትምህርት ቤት እንዲሰራ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው መሰረት ድንጋይ ተጥሎ እና ገንዘቡ ለክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ገቢ ተደርጎ የውሃ ሽታ መሆኑን ለአብነት ያነሳሉ።ፋና ብሮድካስቲንግም የቀዳማዊ እመቤት ፅህፈት ቤት ገንዘቡን ለክልሉ ገንዘብ እአ ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ገቢ መደረጉን እንዳረጋገጠለት ዛሬ ማምሻውን ገልጧል።በሌላ በኩል የተቃውሞውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ፋና ከትግራይ ተቃዋሚ ወጣቶች የደረሰው መረጃ አስመልክቶ እንደዘገበው የክልሉ መንግስት ነዋሪዎቹ ለሚያነሷቸው ረጅም ዓመታት ለፈጁ ጥያቄዎች ምላሽ የማይሰጣቸው ከሆነ የፌዴራል መንግስት ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደመሆናችን ለጥያቄዎቻችን ምላሽ ያሰጥልን ሲሉም ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
ህወሓት በትግራይ ሕዝብ ላይ ለሰራችው ግፍ ማስፈራርያ የምትጠቀመው የኤርትራ መንግስት ሊወረን ነው የሚል ነበር።ሆኖም ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ስያሻሽሉ ሌላው ብሔር ትግራይ ላይ ሊዘምት ነው የሚል ሰፊ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ሕዝቡን ለማደናበር ሙከራ አደረገች።በእዚህም ሳብያ ከአንዳንድ ቦታዎች ትግርኛ ተናጋሪዎች ለቀው እንዲወጡ የሚል ትዕዛዝ ሳይቀር አሰራጨች። ሆኖም የህወሓት ወሬ ሐሰት መሆኑ ሲጋለጥ የበለጠ ማጣፍያው አጠራት።አሁን ሕዝቡ ለራሱ ቀዳሚ አደጋ ህወሓት መሆኗን ከምንግዜውም በላይ ተገነዘበ።እነሆ ፈንቅል የተሰኘው ሕዝባዊ አመፅ በይፋ ተጀመረ።
በእዚህ ሳምንት ከነበሩት ተቃውሞዎች ውስጥ ጥቂቱን በፎቶ ከስር ይመልከቱ።
በደደቢት የነበረው ተቃውሞ (ፎቶ አምዶም ገብረስላሴ ገፅ የተገኘ)
ተቃውሞ በወጀራት (ከአምዶም ገብረስላሴ ፎቶ)
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment