- በፅሁፉ መጨረሻ ላይ ድምፃዊ ሙሐመድ አህመድ እና ሌሎች አርቲስቶች የተሳተፉበት ''መንቃት አንጀምርም ወይ!'' አዲስ ቪድዮ ዜማ ያገኛሉ።
============
በሮበርት ሃይደን በፒተስበርግ ዩንቨርስቲ እኤአ 1993 ዓም ሕትመት ላይ ዩጎዝላቭያ የመበታተን አደጋ ሳይደርስባት ምሁራን የሚፅፉት ፅሁፍ በጸሃፊዎቹ ባፈለቁት ሃሳብ ወይንም ትንታኔ መሆኑ ቀርቶ የት አካባቢ ተወለዱ የሚለው ገኖ ወጥቶ እንደነበር ያትታል። በወቅቱ የብሔር ''ቾቪንዝም'' ዋና መለያ እየሆነ መምጣቱን ይሄው ሕትመት ያስነብባል (Hayden, R. M. 1993)
''ቾቪንዝም'' ቀጥተኛ ትርጉሙ ከመጠን ያለፈ የእኔ ብሔር፣ፆታ፣ባሕል ወይንም ቡድን የተለየ እና ልዩ ተፈጥሮ እና አቅም አለው ብሎ የማሰብ ምናባዊ ስሜት ነው።ቃሉ የመጣው በ1830ዎቹ እአአቆጣጠር የፈረንሳዩ ናፖልዮን ታማኝ ወታደር ኒኮላ ቾቨኒ ነው።ቃሉ በተለይ በዘመነ ናዚ፣በሴቶች የእኩልነት ትግል የወንዶች የበላይነትን ለመታገያ እና በዘመናችን የተነሱት የጎሳ አክራሪዎች መገለጫ እየሆነ ያለ ቃል ነው።
ሰዎች የራሳቸው ጎሳ ከሁሉ የበለጠ መሆኑን የሚነግሯቸውን በመጀመርያ ደረጃ ሲሰሙ እንደቀላል እና እነርሱ እንደዛ የማያስቡ ነፃ ሰዎች እንደሆኑ ይመለከቱታል።እየቆየ ግን አብሮ ከማደግ እና እየተጋነኑ የሚቀርቡት ትርክቶች በምክንያታዊነት የሚያምነውን፣የሰው ልጅ ሁሉ እኩል ነው ብሎ በዕምነቱ የፀናውን ሳይቀር እንደ ዘመኑ ኮሮና ቫይረስ ሳያውቀው ይወረዋል።ችግሩ ደግሞ እራሱ መያዙን ሳያውቀው ምልክቱን ሳያሳይ መኖሩ ነው።
በኢትዮጵያ የተለያዩ የብሔር ፖለቲካ ቡድኖች የብሔራቸውን አባላት ለመቀስቀስ ''ቾቪንዝም'' በግልጥም ሆነ በስውር አራምደዋል።ሻብያ፣ህወሓት፣ኦነግ እና በቅርቡ ደግሞ በዓማራ ዙርያ የሚያቀነቅኑ አደረጃጀቶች ሁሉ የእነርሱ ብሔር ከሌላው የተለየ እንደሆነ አድርገው ለመሳል በርካታ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አድርገዋል፣መፃህፍት ፅፈዋል፣ካድሬ አሰማርተው ህዝባቸውን ሰብከዋል።አሁን በሀገራችን የምናየው የግጭት መንስኤ አንዱ ለዓመታት የተዘራው የብሔር ''ቾቪንዝም'' ውጤት ነው። ቅስቀሳው የአጭር ጊዜ ግብን አልሞ የተነሳ ስለሆነ ከጊዜ በኃላ ቀስቃሾቹ ለመመለስ ወይንም ለማብረድ ቢሞክሩም አይችሉም።ይልቁንም ለስልት ብለው የጀመሩት 'የብሔር 'ቾቪንዝም'' በመጨረሻ ራሳቸውን ይዞ የሚጠፋ አደገኛ መርዝ ሆኖ ይወጣል።
በተለይ ህወሓት እና ሻብያ ወጣቱን ወደ ትግል ለማስገባት ከተጠቀሙበት መንገድ አንዱ ይሄው ''ቾቪንዝም''ነው።ለምሳሌ ህወሓት በደርግ ዘመን መቀሌን ከተቆጣጠረ በኃላ አካባቢውን ለቀው ወደ መሃል አገር ለመሄድ ብዙ ወጣት ማሰቡን እንደተረዳ ያደረገው የዘፈን ፕሮግራም እያዘጋጀ ሴቶቹ ወንዶቹ ወገብ ላይ መቀነት እንዲያስሩ በማድረግ ታላቂቱ ትግራይን ትተህ ወዴት ትሄዳለህ እኔ ሴቷ ስዋጋ የሚል መልዕክት እንዲተላለፍ በማድረግ ብዙ ወጣት ለመሰብሰብ ችላለች።
''ቾቪንዝም'' በዓለማችን ላይ ብዙ ሕዝብን መቀመቅ ውስጥ ከቷል።የ''ቾቪንዝም'' ቀስቃሾች ሲያረጁ የተከሉት መርዝ ቶሎ ስለማይነቀል ለትውልድ የሚቆይ ፀብ አፍርቶ ያንን 'ታላቅ ሕዝብ ነህ' ያሉትን ሕዝብ የበለጠ ችግር ውስጥ ከተውታል።ለምሳሌ ሂትለርን ብንመለከት የጀርመን አርያን ሕዝብ ታልቅ እንደሆነ እና ዓለምን መግዛት እንዳለበት ሰበከ።ብዙ ጀርመኖች ለካ ታላቅ እና የተለየን ነን እያሉ ተከተሉት። የዓለም ሕዝብ በህብረት ተነስቶ ከአራት ማዕዘን ከቦ አገሪቱን ለሁለት ተከፍላ ለዓመታት እንድትቆይ ተደረገች። የ''ቾቪንዝም'' አደገኛነት ጤነኛውንም ሰው ''ታላቅ ነኝ እንዴ?'' እያለ እንዲያብድ ያደርገዋል። የስብከቱ ጥልቀት እና ብዛት ከሰውነት ያወጣል።
ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚድያ እና በትግራይ ሚድያዎች የተጀመረው ይሄው ነው።በትግራይ ሚድያዎች የሚቀርቡ ቃለ መጠይቆች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጠያቂዎቹም ሆኑ መላሾቹ የትግራይ ''ቾቪንዝም'' ለማንፀባረቅ ሲሞክሩ ይታያሉ። ''ይሄ ሕዝብ ሻብያ በ 1977 ዓም መንገድ ዘግታበት አለቱን ሰንጥቆ በሱዳን በኩል መንገድ የሰራ በዓለም ላይ ልዩ የሆነ ሕዝብ ነው'' አለ አንዱ ዛሬ በአንድ የቀጥታ የማኅበራዊ ሚድያ የቪድዮ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ።በማኅበራዊ ሚድያ በተለይ በየቀኑ የትግራይ ''ቾቪንዝም'' ላይ ብቻ የሚያወሩ የቀጥታ ስርጭቶች ቁጥራቸው እየበዛ ነው።ብዙዎቹ አቅራቢዎች በአውሮፓ እና በአሜሪካ የሚኖሩ ቅምጥሎች እና በኑሯቸው የደላቸው የመቀሌ ሕዝብ ውሃ ማጣት ያማያውቁ፣ሽሬ እንዳስላሴ ዙርያ ያለ ገበሬ ክሊኒክ በማጣት እናቶች እየሞቱ እንደሆነ የማያውቁ ፣ ነገር ግን ትግራይ ልዩ ሕዝብ እንደሆነ ሲሰብኩ ለአፋቸው አንዴም ሳት የማይላቸው ናቸው።
'የተከበራችሁ' የትግራይ 'ቾቪንዝም'' ፕሮፓጋንዳ አራማጆች ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ።''ቾቪንዝም'' ማንንም ጠቅሞ አያውቅም።በእዚህ በ21ኛው ክ/ዘመን በእዚህ ፋሺሽታዊ ቅስቀሳ የሚታለል ትውልድ የለም።የሚታለሉ ቢኖሩ ከቀረው ሕዝብ ጋር በሰላም እንዳይኖር ከማድረግ ሌላ የምታተርፉት አንዳች ነገር የለም።ስሜታዊነት፣የውሸት ስብከት እና የአጭር ጊዜ ግብን ብቻ ታሳቢ ያደረገ የ''ቾቪንዝም'' ስብከት መዘዙ ለልጆቻችሁም ጭምር ነው።ከሁሉ ጋር በፍቅር፣በመከባበር እና በመተጋገዝ ለመኖር የማይችል ትውልድ ማፍራት ነገ እራሱን የሚችል ሳይሆን የበለጠ ከሁሉ ጋር ልጋጭ በማለት የራሱም ሆነ የሌላው ፈተና የሚሆን ትውልድ ነው ማፍራት የሚቻለው።ስለሆነም የትግራይ ''ቾቪንዝም'' ሰባኪዎች ይህንን ክፉ ሥራ እንድታቆሙ ትለመናላችሁ። ቀደም ብሎ የኤርትራ፣ኦሮሞ፣ዓማራ ''ቾቪንዝም'' ስብከቶች ብለውት ብለውት ደክሟቸው ሁሉም ባይተዉት እጅጉን ቀንሰዋል።የቀሩት ደግሞ እድሜ ያስተምራቸዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።የትግራይ ''ቾቪንዝም'' ግን በግልጥ እና በብዛት ሰሞኑን እንዳዲስ አገርሽቷል።አገሩ ሽማግሌ የሌለው አስመሰላችሁት።ይህንንስ እያያችሁ ዝም የምትሉ የትግራይ አባወራዎች እና እማወራዎችስ መምከር አይገባችሁም ወይ? የ''ቾቪንዝም'' ሥራ ማንን ጠቀመ? ስንቱን ለስደት እና ለባሕር አውሬ ከመዳረግ ሌላ ምን አተረፈ? ይልቁንም ፊደል በቆጠሩ ''ቾቪንስቶች'' ህዝቡ የተለየ እየተደረገ የሚሰበከው ስብከት ለመገንጠል ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ እንዴት አይገባንም? ነገ ከጥፋት እና እልቂት በኃላ ጉዳዩ እንዴት ተነሳ ብሎ ማጥናት እና ምክንያቶቹን ለመዘርዘር የጥናት መድረክ ማንጋጋት አይጠቅም።ይሄው ጥፋቱ ሳይመጣ ''ቾቪንዝም'' ወይንም ሞት! ያሉትን ምከሩ።
ማጣቀሻ
1 Hayden, R. M. (1993). The triumph of chauvinistic nationalisms in Yugoslavia: Bleak implications for anthropology. Anthropology of East Europe Review, 11(1 & 2), 73-78.
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

ሰዋዊ ዜማ
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
Gudayachn Multimedia, Kommunikasjon og Konsultent
ማጣቀሻ
1 Hayden, R. M. (1993). The triumph of chauvinistic nationalisms in Yugoslavia: Bleak implications for anthropology. Anthropology of East Europe Review, 11(1 & 2), 73-78.
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment