ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
Monday, February 13, 2023
Wednesday, February 8, 2023
የብልጽግና ፓርቲ በመንግስት ስም ''የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ'' በሚል ያወጣው መግለጫ ፋሺሽት ጣልያን በ1929 ዓም በአዲስ አበባ ካወጣው መግለጫ ጋር ተመሳሳይ የሚያደርገው ጉዳይ።
- የብልጽግና ወታደሮች የፈጠሩትን የጸጥታ እና የደህንነት ችግር እንዳላየ ያለፈ በግፍ የተሞላ እና በደም የተጨማለቀ መግለጫ ነው
ግፍ እና የግፍ ግፍ ሞልቶ ፈሷል። ኢትዮጵያ ያመነችው፣ሚልዮኖች አደባባይ ወጥተው የደገፉት፣በመስቀል አደባባይ ቦንብ ሲወረወረወርበት እኔ ልሙት ብለው ከፊታቸው ቀድመው የደረሱ እና ህይወታቸውን የሰጡለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያን አሳዝኗታል። ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግፍ በተሞላ አነጋገር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ህገወጥ ሲኖዶስ በኦሮምያ ክልል መመስረቱን ቀላል ጉዳይ ነው ብለው ከመቀለዳቸው በፊት፣ቤተክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከባለቤታቸው ጋር በቤተክህነት ጠርታ በቅዱስ ፓትሪያሪኩ እጅ ካባ ሸልማለች።
የዛሬው የብልጽግና የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ ከጣልያን የ1929 ዓም መግለጫ ጋር የሚያመሳስለው ጉዳይ የግፍ መልዕክቱ ይዘት ነው። የጸጥታና ደህንነት ግብረ ኃይል መግለጫ የደህንነትና የጸጥታ የሚለው ስሙ ለኢትዮጵያ ከሆነ ሰሞኑን ከ30 በላይ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ካህናትን ጨምሮ በጥይት ሲረግፉ፣ቤተክርስቲያን ደጆቿ በብልጽግና ወታደሮች እና በህገወጡ ቡድን ጀሌዎች የመሰበራቸው ጉዳይ የጸጥታና ደህንነት ጉዳይ አለመሆኑ ያስገርማል። የወጣቶችን ደም እየረገጡ የቤተክርስቲያንን ቅጽር ግቢ እየገቡ በሯን እየሰበሩ የገቡትን ህገወጦች በተመለከተ አንዳች ቃላት ያልጨመረው የዛሬው የጸጥታና የደህንነት ግብረ ኃይል መግለጫ ጣልያን በየካቲት 12፣1929 ዓም የአዲስ አበባ ህዝብን ጨፍጭፎ ለጭፍጨፋው ምክንያት ያደረገው እራሳቸው ኢትዮጵያውያንን በወቀሰ መልኩ ካወጣው መግለጫ ጋር ተመሳሳይ ያደርገዋል።
Saturday, February 4, 2023
እነ አቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስት ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል። በአዕምሯችን ውስጥ የሚነሱ በወቅታዊ የኢትዮጵያ እና የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙርያ 7 ጥያቄዎች እና አጫጭር መልሶች።
- ቤተመንግስትም ያለህ መከላከያም ያለ የኦርቶዶክስ ልጅ ሥራህን ለማንም ትተህ እንዳትወጣ።
- ሃገር በጽንፈኛ እየፈረሰ ከኦርቶዶክሳዊነት ጎን እስከቆመ ድረስ ኢትዮ 360፣የቀድሞ የህወሃት አባል፣ኢህአፓ፣ የመቀሌ ልጅ፣የሱማሌ ፕሬዝዳንት ብሎ መለያየት የለም።ሁሉን በአንድ መስመር ተይዞ ይሄዳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ምስጢራዊ የኦሮምያ ብልጽግና ቡድን ከአቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስ ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል። ግንቦት 24፣2014 ዓም ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካሕናት ጉባዔ
2. ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦንስ 12
3. የቀድሞው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ 7 ድምጽ አግኝተዋል፡፡
ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በእጩነት ከቀረቡት መካከል
1. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 20 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል 17
3. ብፁዕ አቡነ ኤልያስ 8 ድምጾች አገኙ።
ጥያቄ = የሃይማኖት ጉዳይ ሲሆን ብቻ ልናገር ፖለቲካ ይቅርብኝ?
Tuesday, January 31, 2023
ጠ/ ሚ/ር ዐቢይ ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመክፈል የሞከሩ ሕገወጦችን አስመልከተው የተናገሩት ንግግራቸው በታሪክም በሕግም ያስጠይቃቸዋል።
- የሞሰቡን ባለቤት ከራሱ ሞሰብ ላይ ቆንጥረው ያጎረሱትን እየቆጠሩ ከውለታ ቁጠርልኝ፣
- ቤንዚን ማርከፍከፍ
- ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተፈጸመው ወንጀል የሚያስከትለው መዘዝ ገብቷቸዋል።
- ሚኒስትሮች! የሃይማኖታችሁ ጉዳይ አይመለከታችሁም! ዝም በሉ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ጥር 23፣2015 ዓም ሰላም እና ሃይማኖት በተመለከተ የተናገሩት በሚል በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተናገሩት ንግግር በዋናነት ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ለመክፈል በኦሮምያ ክልል የተነሳውን ቡድን አስመልክተው የተናገሩት በታሪክም በሕግም ያስጠይቃቸዋል።
Monday, January 30, 2023
የብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን የማስተዳደር አቅሙ የወደቀ ለመሆኑ ህዝብ ድምዳሜ ላይ እየደረሰ ነው።የአቡነ እስጢፋኖስ በጅማ ፖሊስ ጣብያ ታስረው መዋል ፓርቲው ክቡር ለሆነ የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ እሴት (''ሶሻል ቫልዩስ") ያለው የንቀት ደረጃ ህዝብ በሚገባ ለክቶበታል።
- ይህ ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል የሆነው ከ70 ሚልዮን በላይ የሆነ ቀረጥ ከፍሎ የሚያድረው ህዝብ በከፈልኩት ቀረጥ መንግስት ቤተክርስቲያኔን የመጠበቅ ግዴታህን ተወጣ የሚል እጅግ የከበደ ጥሪ ነው፣
- ጅማን ህይወት የዘሩባት አቡነ እስጢፋኖስ ላይ የተፈጸመው ግፍ ብልጽግና በህዝብ ላይ ያለው የንቀት ጥግ ያሳያል።
- የኢትዮጵያ ኦ/ ተ/ቤተክርስቲያን በተሞከረባት የመበተን ሙከራ አንጻር ቤተክርቲያኒቱ እንደ ተቋም ምዕመናኖቿ ደግሞ እንደ የቤተክርስቲያን ልጅነት ሊወስዷቸው የሚገቡ ሁለት ስልታዊ እርምጃዎች ምን እና ምን ናቸው?
Sunday, January 29, 2023
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተመለከተ ዛሬም ወሳኙ ጉዳይ ውስጣዊ አስተዳደራዊ መዋቅሯን ማዘመን አና ማቀላጠፍ ነው።የውጪው ፈተናዋ አስከምፅአት ቀን ድረስ የሚኖር ነው።(የጉዳያችን የዛሬም ጩኸት አንድ ነው!)
የዛሬ አስር ዓመት ምን ይገጥመናል ብሎ መፃፍ አና ዛሬ ይሄ ሆነ ሲባል ስሜትን በቁጣ አየገለፁ መናደድ ይለያያሉ።ጉዳያችን የዛሬው ቀን እንደሚመጣ ከአስር ዓመታት በላይ ጽፋለች።የጽሑፎቹን ሊንኮች ከስር ያገኛሉ።
- አሁን ያሉት ቤተክርስቲያንቱን የመግፋት ድርጊቶች ችግር ብቻ ሳይሆን ያለው ለቤተክርስያንቱ ዕድል ይዞ የሚመጣ መልካም አጋጣሚም ነው።
======
ጉዳያችን
====== የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በምእመናኖቿ ብቻ ሳይሆን በስርጭትም ሆነ በማኅበራዊ አና ምጣኔ ሃብታዊ መለኪያዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ አካል ነች። ይህንን እውነታ መጋፋቶች መሬት ላይ ያለውን አውነታ መቀየር አይቻልም።አሁን ያሉት ቤተክርስቲያንቱን የመግፋት ድርጊቶች ችግር ብቻ ሳይሆን ያለው ለቤተክርስያንቱ ዕድል ይዞ የሚመጣ መልካም አጋጣሚ ነው።የቤተክርስቲያኒቱ አስተምሮ ላይ ያሉ ግንዛቤዎች በአዲሱ ወጣት ትውልድ ዘንድ መደናበር የለም።ወዴት መሄድ አለብን፣አንዴት ቤተክርስቲያንን አናልማ ውዥንብር የለም።የቤተክርስቲያኒቱ ውጫዊ ተግዳሮቶች መነሻ መሰረታዊ ባህሪዎች የመለየት ችግር የለም።አነኝህ ሥራዎች ላለፉት ዓመታት በጥራት ግንዛቤ የወሰደ ከ70 ሚልዮን በላይ ምዕመን አለ።አሁን ያሉት ችግሮች የሚነሱት ከቤተክህነት አና ከመንግስታዊ የፖለቲካ አካላት መሆናቸው የችግሩ ስብጥር እና ጥግ በራሱ የተሰበሰበ መሆኑ ለመፍትሄዎቹ ግልፅ ያደርጋቸዋል። ይህንን ሁሉ በፍጥነት ለመመከት ግን ቤተክርስቲያኒቱ ውስጣዊ መዋቅሯን በፈጠነ መልክ ማዘመን መቻል ይጠይቃል።ይህንን ደግሞ ቁርጠኘነቱ እና በጎ ፈቃዱ ከቤተክህነት በኩል ካለ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ለሥራው ዝግጁ ናቸው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ በጉዳያችን ላይ የወጡት ጽሑፎች መለስ ብሎ ለማየት ለሚፈልግ ከብዙ ጥቂቶቹን ብቻ ከአዚህ በታች ርዕሶቹን አና የተፃፉበትን ጊዜ (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር) ከስር ለማካፈል ሞክርያለሁ። ዛሬም ትኩረት የሚያስፈልገው ውስጣዊ የመዋቅር ማዘመን አንጂ በክርስቶስ ዘመን የነበረው አና ክርስቶስ ተመልሶ አስከሚመጣ የሚኖረው የውጭ ፈተና አይደለም። ይህ ማለት ውጫዊ ፈተናዎች በሙሉ ችላ ይባሉ ማለት አይደለም።የአንድ ተቋም ህልውና ግን አደጋ ላይ የሚወድቀው በውጫዊ ተፅዕኖ ሳይሆን ከውስጣዊ የአሰራር፣የመዋቅር አና የአቅም ግንባታ አለመጠናከር ነው።ቤተክርስቲያኒቱ የውስጡን ስታጠናክር በፍጥነት የውጭውን ፈተና መመከት ብቻ አይደለም በጎ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅሟን የሚጨምር ፈጣን አቅም ከመቅፅበት በራሱ ይመጣል።
ከአዚህ በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ፈተናዎች በተመለከተ ጉዳያችን ላይ ከወጡት ውስጥ የሚከተሉትን ለናሙናነት አቀርባለሁ።ማንም ሰው ጉግል ላይ ርዕሶቹን በመፃፍ ብቻ አያንዳንዱን ጽሑፍ በቀላሉ ማንበብ ይችላል።
የጉዳያችን የዛሬ መልዕክትም አንድ ነው። የኢትዮጵይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን በቀላሉ ገፍቶ ኢትዮጵያን ማስቀጠል ፈፅሞ አይቻልም። የአርሷን ያህል የትህትናም ሆነ የፀጋ ባለቤት አሁንም የለም።ይህ ማለት የሌለውን የራሴ የሚለው የማመን መብቱን መጋፋት ወይንም ዝቅ አድርጎ ማቅረብ ማለት አይደለም።አውነታውን ማንም የማይነቀንቀው ሀቅ ነው።
ከእዚህ ቀደም በጉዳያችን ላይ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በተመለከተ ከወጡት ጽሑፎች ውስጥ የጥቂቶቹ ርዕሶች እና ሊንኮች : =
ርዕስ = የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ችግር በማያዳግም መልኩ ለመፍታትት ሁሉም ይነሳ! (ሚያዝያ፣2019 ዓም እኤአ)
ርዕስ = በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ላይ ሰሞኑን የነበረው ሁኔታ ለቤተክርስቲያን የደወል ድምጽ ነው::ወደፊት ምን ይሰራ? (መስከረም 6፣2019 እኤአ)
ርዕስ = የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን ሁሉን አቃፊ የሆነ ፖለቲካዊ ዕሳቤ መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ፓርቲ በመመስረት እና ሚናውን በማስፋት የኢትዮጵያ ህልውናን በትክክል ማረጋገጥ ይቻላል። (ጉዳያችን ሃሳብ) መስከረም 16፣2019 እኤአ የተፃፈ።
ርዕስ = የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ደህንነቷን ለመጠበቅ በፍጥነት መውሰድ የሚገባት ሁለት የመፍትሄ ርምጃዎች (የጉዳያችን ሀሳብ) (ህዳር 16፣2010 እኤአ የተፃፈ)
ርዕስ = በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ የሚታየው የመንግስት አያያዝ በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ጦርነት ሊያስነሳ ይችላል (ጉዳያችን ልዩ እና ወቅታዊ ) (መስከረም 2019 ዓም እኤአ የተፃፈ)
ርዕስ = በጅማ ዩንቨርስቲ የ ኦርቶዶክስ ተማሪዎች ላይ ከ ሰሞኑ የተፈፀመ ግፍ (GUDAYACHN EXCLUSIVE ) (ጥር 2013 እኤአ የተፃፈ)
===============////=========
Tuesday, January 24, 2023
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለመክፈል የተሞከረው ሙከራ በሁሉም ክልል በሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱን ልጆችና አባቶች ዘንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅግ የጠነከረ ህብረት እና አንድነትን ፈጥሯል።
- በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን በሙስሊሙም ማኅበርሰብ ዘንድ ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል የሚደረገው ሙከራ ከፍተኛ ቁጣን ፈጥሯል።
- ንዝረት የተኛ ነርቭ ያነቃቃል።
- ቤተክርስቲያን ተሸንፋ አታውቅም ሊከፋፍሏት የሞከሩትን ሁሉ ግን አለት ሆና ስታደቅ በታሪክ ታይቷል።
- ቅዱስ ሲኖዶስ የነገውን አስቸኳይ ስብሰባ ህገወጦቹን ከማውገዝ ባለፈ የቤተክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ ሁኔታ ለማዘመን ከምር ከምዕመናን ጋር መክሮ ወደ ሥራ የሚገባበት መሆን አለበት። ይህንን የአንድነት ስሜት መጠቀም ይገባል።
-
በቀሲስ መንግሥቱ ጐበዜ ሉንድ ዩንቨርሲቲ ፣ ስዊድን (ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አርኪኦሎጂ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና በሉንድ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት...
-
አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን =============== ጉዳያችን /Gudayachn =============== ብሉምበርግ የተሰኘው የአሜሪካ ድረገፅ በፖለቲካ እና ፖሊሲ አምድ ስር የአድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን አሜሪካ ኢትዮጵ...
-
The Ethiopian herald News Paper August 20 , 2020 BY STAFF REPORTER Addis Ababa ************************** (EPA) ADDIS ABABA - Over sixty-mil...

