ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, February 8, 2023

የብልጽግና ፓርቲ በመንግስት ስም ''የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ'' በሚል ያወጣው መግለጫ ፋሺሽት ጣልያን በ1929 ዓም በአዲስ አበባ ካወጣው መግለጫ ጋር ተመሳሳይ የሚያደርገው ጉዳይ።


አዲስ አበባ የቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀን ጥቁር የመልበስ ትዕዛዝ መሰረት ምዕመናን ጥቁር ለብሰው።

  • የብልጽግና ወታደሮች የፈጠሩትን የጸጥታ እና የደህንነት ችግር እንዳላየ ያለፈ በግፍ የተሞላ እና በደም የተጨማለቀ መግለጫ ነው

ግፍ እና የግፍ ግፍ ሞልቶ ፈሷል። ኢትዮጵያ ያመነችው፣ሚልዮኖች አደባባይ ወጥተው የደገፉት፣በመስቀል አደባባይ ቦንብ ሲወረወረወርበት እኔ ልሙት ብለው ከፊታቸው ቀድመው የደረሱ እና ህይወታቸውን የሰጡለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያን አሳዝኗታል። ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግፍ በተሞላ አነጋገር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ህገወጥ ሲኖዶስ በኦሮምያ ክልል መመስረቱን ቀላል ጉዳይ ነው ብለው ከመቀለዳቸው በፊት፣ቤተክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከባለቤታቸው ጋር በቤተክህነት ጠርታ በቅዱስ ፓትሪያሪኩ እጅ ካባ ሸልማለች።

ይህ ሁሉ የህዝብ ፍቅር መሰረቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን እና አንድነቷን እንደሚደግፉ እና ለእዚያም እንደሚሰሩ በንግግራቸው በመግለጻቸው ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባለፈው ሳምንት ግዙፍ ሃገራዊ የጸጥታም ሆነ የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ብቻ ሳይሆን ሃገር የሚበትነውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስን የሚከፍል ህገወጥ ቡድን በኦሮምያ ክልል መመስረቱን አስመልክተው ጉዳዩን አቅልለው ለማሳየት ከመሞከር አልፎ የህገወጦቹ ቃል አቀባይ እስኪመስሉ ድረስ በጉዳዩ ላይ የካቢኔ አባሎቻቸውም ቃል እንዳይተነፍሱ ሲያስጠነቅቁ አምሽተዋል።

ዛሬ የካቲት 1፣2015 ዓም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የሁለት ሰዓት የዜና እወጃ ላይ ሦስት ጊዜ እየተደጋገመ የተነበበው የብልጽግና ፓርቲ በመንግስት ስም ''የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ'' በሚል ያወጣው መግለጫ ፋሺሽት ጣልያን በ1929 ዓም በአዲስ አበባ ካወጣው መግለጫ ጋር ተመሳሳይ የሚያደርገው ነጥብ አለ።

የዛሬው የብልጽግና የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ ከጣልያን የ1929 ዓም መግለጫ ጋር የሚያመሳስለው ጉዳይ የግፍ መልዕክቱ ይዘት ነው። የጸጥታና ደህንነት ግብረ ኃይል መግለጫ የደህንነትና የጸጥታ የሚለው ስሙ ለኢትዮጵያ ከሆነ ሰሞኑን ከ30 በላይ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ካህናትን ጨምሮ በጥይት ሲረግፉ፣ቤተክርስቲያን ደጆቿ በብልጽግና ወታደሮች እና በህገወጡ ቡድን ጀሌዎች የመሰበራቸው ጉዳይ የጸጥታና ደህንነት ጉዳይ አለመሆኑ ያስገርማል። የወጣቶችን ደም እየረገጡ የቤተክርስቲያንን ቅጽር ግቢ እየገቡ በሯን እየሰበሩ የገቡትን ህገወጦች በተመለከተ አንዳች ቃላት ያልጨመረው የዛሬው  የጸጥታና የደህንነት ግብረ ኃይል መግለጫ ጣልያን በየካቲት 12፣1929 ዓም የአዲስ አበባ ህዝብን ጨፍጭፎ ለጭፍጨፋው ምክንያት ያደረገው እራሳቸው  ኢትዮጵያውያንን  በወቀሰ መልኩ ካወጣው መግለጫ ጋር ተመሳሳይ ያደርገዋል።

በኢትዮጵያ ስም የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተባለ የመንግስት ኮሚቴ መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ላይ የብልጽግና ታጣቂዎች ያደረሱትን የግፍ ጭፍጨፋ በዛሬው መግለጫው ዓይኑን በጥቁር ጨርቅ ሸፍኖ ምንም እንዳልሆነ ለማለፍ መሞከሩ በአሳፋሪ የመንግስት ታሪክ ውስጥ ተመዝግቦ ይኖራል። ቤተክርስቲያኒቱ መከፈል የለብኝም፣በመክፈል ስራው ደግሞ የመንግስት ግልጽ የሆነ ድጋፍ አለ፣ ካህናቶቼን እና ምዕመናኖቼን እየገደሉብኝ ነው ብላ በሦስት ቀን ጾምና ጸሎት ማዘኗ፣በደረሰባት ግፍ ልጆቿ ጥቁር ለብሰው መውጣታቸው ሁሉ እና ይህንንም ድምጿን ለማሰማት አደባባይ ታቦተ ህጉን ይዛ በሰላማዊ መንገድ ድምጼን ለምድርም ለሰማይም ገዢም አሰማለሁ ማለቷ እንደ ሁከት ፈጣሪ አድርጎ የሚተነትነው የብልጽግና የጸጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ እንደ የጣልያኑ የ1929 ዓም የተገደለውን ህዝብ በወቀሰበት እና እራሱ ጨፍጭፎ በደም የተጨማለቀ መግለጫ እንዳወጣ ዛሬም ብልጽግና ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሠላሳ በላይ ንጹሃን ምዕመናን ካህናትንም ጭምር ገድሎ ስለሞቱት ምንም ያልተነፈሰው እና ገዳዮቹ የብልጽግና ወታደሮች የፈጠሩትን የጸጥታ እና የደህንነት ችግር እንዳላየ ያለፈ በግፍ የተሞላ እና በደም የተጨማለቀ መግለጫ ነው።
============////===========


No comments:

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...