ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, February 4, 2023

እነ አቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስት ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል። በአዕምሯችን ውስጥ የሚነሱ በወቅታዊ የኢትዮጵያ እና የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙርያ 7 ጥያቄዎች እና አጫጭር መልሶች።

  • ቤተመንግስትም ያለህ መከላከያም ያለ የኦርቶዶክስ ልጅ ሥራህን ለማንም ትተህ እንዳትወጣ።
  • ሃገር በጽንፈኛ እየፈረሰ ከኦርቶዶክሳዊነት ጎን እስከቆመ ድረስ ኢትዮ 360፣የቀድሞ የህወሃት አባል፣ኢህአፓ፣ የመቀሌ ልጅ፣የሱማሌ ፕሬዝዳንት ብሎ መለያየት የለም።ሁሉን በአንድ መስመር ተይዞ ይሄዳል።
==========
ጉዳያችን
=========
እነ አቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስት ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ምስጢራዊ የኦሮምያ ብልጽግና ቡድን ከአቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስ ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል። ግንቦት 24፣2014 ዓም ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካሕናት ጉባዔ 
ሲደረግ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራአስኪያጅ ምርጫ ሲደረግ የቤተክህነት ምስጢራዊ የብልጽግና ቡድን አቶ አካለወልድን ለማስመረጥ ከፍተኛ ፍትግያ አድርጓል።በምርጫው ሂደት ላይ ጉባዔውን ለማወክ ግልጽ የሆነ ማስፈራራት ሲፈጸም የኢጣልያ፣ፈረንሳይ እና አካባቢው ሊቀጳጳስ እና የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ አቡነ ሕርያቆስ ያደረጉት ተጋድሎ በአግባቡ ለሕዝብ አልተገለጸም።አቡነ ሕርያቆስ ጉባዔውን በግልጽ በመገሰጽም ሆነ የምርጫው ሂደት በህገ ወጦች እጅ ሊገባ ሲል ጉባዔውን እረግጠው በመውጣት ምርጫው ትክክለኛ መስመር እንዲይዝ ከፍተኛ ተጽኖ ለመፍጠር የሞከሩበት ሂደት በቤተርክስቲያኒቱ ታሪክ ሲዘከር የሚኖር ነው።

ይህ ብቻ አይደለም አቡነ ሕርያቆስ ምርጫው በመንግስት ማስፈራርያ መሆን የለበትም ብለው ጉባዔውን እረግጠው ከወጡ በኋላ ተለምነው ሲገቡ ምርጫው በሕጉ እንዲፈጸም ቃል አስገብተው ነበር። በመጨረሻም በምርጫው አርባ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ከተወዳደሩት
1. ብፁዕ አቡነ አብርሃም 26 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2. ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦንስ 12
3. የቀድሞው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ 7 ድምጽ አግኝተዋል፡፡
ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በእጩነት ከቀረቡት መካከል
1. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 20 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል 17
3. ብፁዕ አቡነ ኤልያስ 8 ድምጾች አገኙ።

በቀጣይ ቀናት የብልጽግና የደህንነት ሰዎች በአቶ አካለወልድ አለመመረጥ በመብሸቅ ወደ አቡነ ሕርያቆስ ያረፉበት ቤት ድረስ ተልከው ለማስፈራራት የሞከሩ ሲሆን አቡነ ሕርያቆስም ካለአንዳች ፍራቻ ተገቢውን ምላሽ እንደመለሱ መረጃ አለ።ይህ ማለት አቶ አካለወልድ በቤተክህነት ሥራ አስኪያጅነት እንዲመረጡ ቢደረግ ኖሮ ምን ዓይነት ከባድ ጥፋት በቤተክርስቲያን ላይ የብልጽግና ቡድን ሊያደርስ በምስጢር ተዘጋጅቶ እንደነበር በሚገባ መረዳት ይቻላል። በመሆኑም አሁን እየተፈጸመ ያለው ቤተክርስቲያንን በግልጽ የመውረር እና የማፍረስ ተግባር መንፈስ ቅዱስ ባወቀ በእነ አቡነሕርያቆስ ላይ አድሮ ጉባዔውን ባያጸና ኖሮ በምስጢራዊ መስመር ከባድ ጥፋት ሊፈጸም እንደነበር በጣም ግልጽ ነው።

በአዕምሯችን ውስጥ የሚነሱ በወቅታዊ የኢትዮጵያ እና የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙርያ 20 ጥያቄዎች እና አጫጭር መልሶች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ጥረት እየተደረገ ባለበት በእዚህ ጊዜ ብዙ ጥያቄዎች በአዕምሯችን ውስጥ ይመጣሉ።ከእነኝህ ውስጥ 20ዎች ብዬ ለመምረጥ ሞክርያለሁ።በእነርሱ ላይ የራሴን ምላሽ ለመስጠት እሞክራለሁ።እነኝህ ጥያቄዎች ነገ በማኅበራዊ ሚድያም ሆነ ሌላ ቦታ ስናገኝ አንድ ዓይነት ምላሾች እና ምንም ዓይነት መደናገሮች መኖር የለባቸውም።

ጥያቄ = የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንደ ፖለቲከኞች በድርድር ይፈታል?

መልስ= ፈጽሞ በድርድር አይፈታም።ያለው መንገድ ቤተክርስቲያንን የከዱት ይቅርታ ቅዱስ ሲኖዶስን ጠይቀው፣የወሰዱትን መልሰው፣የሰበሩትን ጠግነው ሲቀርቡ ብቻ ነው። ፖለቲከኞችም ሆኑ አሁን የህዝቡን መነሳት አይቶ የጽንፍ ኃይሉ እንደፖለቲካ ድርድር የሚለው አሁን የህዝቡን መነሳት እና ነገሩ እንደማያዋጣ ሲያውቁ የሚያቀርቡት ነው።

ጥያቄ = ኦርቶዶክሳውያን የመንግስትን ሥራ ከቤተመንግስትም ከመንግስት ስራም ለቀው መውጣት አለባቸው?

መልስ = ፈጽሞ። መጀመርያ ሥራህ ቤተመንግስት ሆነ ጦር ሰራዊቱ ውስጥ ክልል ሆነ ቀበሌ ለቀህ መሄድ የለብህም። የሚፈለገው ይሄው ነው። በመጀመርያ ሃገሬ የእኔ ነች ማንም በችሮታ የሚሰጠኝ እና የሚነጥቀኝ አይደለችም ብሎ ማመን ያስፈልጋል።ይህንን እምነትህን ነው ቀድሞ ሊነጥቁህ የሚፈልጉት።ወለጋ ሃገርህ እንዳልሆነ ሊነርግሩ ሲሞክሩ ውስጥህ ሃገርህ ሌላ እንደሆነ የሚስብ ስሜት ሊፈጥሩብህ እንደሞከሩ ተረዳ።ስለሆነም ኢትዮጵያ ሁሉ ሃገርህ፣ስራህ ሁሉ ማንም በችሮታ የማይሰጥህ መሆኑም ማመን እና ባለህበት ሃገርህን እንደምትጠቅም ማመን አለብሕ

ጥያቄ = ቤተክርስቲያንም ሃገሬም ለገጠማት ችግር የእኔ ድርሻ ምንድን ነው?

መልስ = መጀመርያ ባለህበት የሥራ መስክ ይህ ያንተ ግዛት መሆኑን እመን። ቦታህን አትልቀቅ። ቀጥሎ ውጭ ሃገር ሁን ሃገር ቤት፣ቀበሌ ውስጥ ሁን መምህር በእጅህ ባለው እና ባንተ ልክ ልትሰራ የምትችለውን በደንብ ለይተህ በሌሎች የማይደጋገም ሥራ ከአንተ ችሎታ አንጻር መስራት ያለብህን ለይተህ ሥራ። ዝም ብለህ ተመልካች ከሆንክ ከሞተው በላይ ከቆመው በታች መሆንህን እመን። 

ጥያቄ = ዐቢይ ነገ በቴሌቭዥን ቀርቦ እያለቀሰ ተሳስቼ ነበር ብሎ ሊቀርብ ይችላል? ይህ ለውጥ ያመጣል?

መልስ = የለቅሶ ድራማ ጠብቅ።ለዓላማ የማይከፈል ነገር የለምና ያደርገዋል። ነገር ግን ባይሳካለትም በህሊናው ግን ቤተክርስቲያኒቱን ሰውቷታል። ቢያንስ በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ህገወጦቹን እጅግ በሚያሳፍር ደረጃ ደግፏል።ማንም እንዳያግዳቸው የራሱን ካቢኔ ጨምሮ አስፈራርቷል።የሙስሊሞች ችግር ጊዜ የሰላም ሚኒስቴር መስርያቤት ችግሩን እንዲፈታ ተመድቦ የነበረበት ጊዜ እንዳልነበር አሁን ግን የሰላም ሚኒስቴርን ያስፈራራው እራሱ ጠቅላዩ መሆኑ የሄደበትን እርቀት ያሳያል።

ጥያቄ = ቤተክርስቲያንን የማጥፋት ሥራ የአካባቢውን ጂኦ ፖለቲክስ ይቀይራል?

መልስ = በትክክል ይቀይራል። ቤተክርስቲያንን የማጥፋት ሥራ በአንዳንድ መንግስታት የረጅም ጊዜ ዕቅድ ነበር።አሁን ዐቢይ ይህንን መነገጃ ለማድረግ ግልጽ ድፍረት አሳይቷል።ቤተክርስቲያን መፍረሷ ደግሞ ጂኦ ፖለቲካውን ያበላሻል ያሉ እንደሩስያ ያሉ መንግስታት በጥብቅ ጉዳዩን እየተከታተሉ ለመሆኑ አምባሳደሩ የሰጡት የሰሞኑ መግለጫ ማሳያ ነው።አምባሳደሮች በአንድ ሃገር የውስጥ ጉዳይ ብዙ አስተያየት አይሰጡም።የሩስያው አምባሳደር ይህንን ያህል እርቀት የሄዱት የቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ የጂኦፖለቲካ ጉዳይ ላይ የሚያዛንፈው ብዙ ጉዳይ ስላለ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

ጥያቄ = ስሜታችን በንዴት እንዲጎዳ የሚያደርጉ ሥራዎች ሲገጥሙ ምን ላድርግ?

መልስ = በወቅቱ ሁኔታ መበሳጨት ተፈጥሯዊ እና ጤነኛነት ነው።ነገር ግን የቤተክርስቲያን ጠላቶች ዋና ግብ ማበሳጨት ብቻ ሳይሆን ተስፋ የቆረጥክ እንድትሆን ምስጢራዊ የስነ ልቦና ዘመቻ ማድረግ ነው። በመሆኑም አንዳንዴ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት የተነሱ መሪዎች እየገለፈጡ በተነሱት ፎቶ በኢቲቪ እንዲታዩ የሚያደርጉት የተረጋጉ ለመምሰል እና የስነ ልቦና ጦርነት ለማድረግ እንደሆነ በሚገባ ተረዳ።እራስህን አረጋግተህ ለሃገርህም ሆነ ለቤተክርስቲያንህ የሚገባውን ከራስህ ጠንካራ መንፈሳዊ ህይወት እና ኃይል ጋር እራስህን በራስህ አስታጥቅ እንጂ እየተበሳጨህ እራስህን አትጉዳ።ሥራ የሚጀምረው ምን ሰራሁ? ከሚል የራስ ጥያቄ ነው።

ጥያቄ = የሃይማኖት ጉዳይ ሲሆን ብቻ ልናገር ፖለቲካ ይቅርብኝ?

መልስ = ይህ ዛሬ ለደረስንበት ደረጃ ያበቃ የስህተት አስተሳሰብ ነው።አሁን ቤተክርስቲያንን እያመሰ ያለው የዶግማ ጉዳይ አይደለም። የጎጠኛ ፖለቲከኞች ከህወሃት ኢሃዴግ እና ብልጽግና እየተወራረሱ ያመጡት የዘር ፍጅት ፖለቲካ ነው።ስለሆነም መሞገት ያለብህ ፖለቲካውንም ጭምር ነው። ቤተመንግስቱ ሲስተካከል ቤተክህነቱ ይረጋጋል። ቤተመንግስቱን ትቼ ቤተክህነቱ ላይ ብቻ ልመልከት ካልክ ያለፈውን ስህተት ትደግመዋለህ። ቤተክርስቲያን ጎጥ አትቀበልም።ይህ ሃይማኖታዊ መልዕክት ነው። ጳጳሳት ሳይቀሩ የመንግስት ጎጠኛ መንግስት አንቀበልም ማለት ይችላሉ።ማውገዝም ይችላሉ። ቤተክርስቲያኒቱ የጎጥ ፖለቲካ መንቀል በትክክል ትችላለች።ይህ ደግሞ ፖለቲካ አይደለም። ሃይማኖታዊ መልዕክት ነው።ጎጠኝነት ክርስቲያናዊ አለመሆኑን በመንገር እና በመቃወም ብቻ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ማቆም ይችላሉ።ይህንን የጎጠኘነት ፖለቲካ መቃወም ከካህን እስከ ዲያቆን፣ከጳጳስ እስከ ምዕመን ሊቃወመው የሚችለው አጀንዳ ነው።

አበቃሁ!
============////=========

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...