ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, November 4, 2021

ሄርማን ኮህን የዛሬ 31 ዓመት ኢትዮጵያን ለንደን ላይ እንዳታለለ፣ ዛሬ ፌልትማን ይህንን ትውልድ አያታልለውም!


ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ
==============
የጉዳያችን ልዩ መልዕክት
==============
በሀገር ውስጥም በውጭ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ፈፅሞ እንዳትታለሉ።አሜሪካ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የቻለችውን ሁሉ እያቀጣጠለች ነው።ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ በእያንዳንዳንዱ ወንድ እና ሴት ኢትዮጵያዊ ተጋድሎ፣ቆርጦ መነሳት እና ካለፍርሃት መስራት እንደምትድን እንወቅ። የአሜሪካ፣የምዕራብ ሚድያ እና የሽብርተኛው ህወሓት ፌስቡክ መሃል ሀገርን በወሬ ለማተራመስ ተግተው እየሰሩ ነው።

አሜሪካ አፍጋኒስታን ያለ ኤምባሲ ሰራተኞች በእዚህ ፍጥነት ይውጡ አላለችም።ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ሌሎች ሀገሮች ተስፋ እንዲቆርጡ ለማድረግ አላስፈላጊ የሆኑ የኤምባሲ ሰራተኞቼን አስወጣለሁ ብላለች። ይህ ሌላ አይምሰላችሁ መሀሉን ለማተራመስ ከሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ጋር  ያላቸው የተናበበ ሥራ ነው።

የምዕራቡ በተለይ የአሜሪካ የባይደን አስተዳደር ማንም አፍሪካዊ ሀገር እንደ ኢትዮጵያው የዓቢይ አስተዳደር አልታዘዝም ብሎት አያውቅም።ስለሆነም ይህ ጉዳይ ሌሎች አፍሪካ ሀገሮች ላይ ያለው ጉልበት ሁሉ እንደሚሰበር እና  መንገድ የሚከፍት ''አደገኛ'' አካሄድ ነው ብለው ደምድመዋል።ማንም የአፍሪካ ሀገር በቡድን ሰባት ስብሰባ እንደ ዘንድሮ ኢትዮጵያ ላይ እንዳደረጉት በእዚህ ደረጃ ርዕስ ሆኖ አያውቅም።ማንም የአፍሪካ ሀገር የውስጥ ጉዳይ በፀጥታው ምክር ቤት ከአስር ጊዜ በላይ በዝግ ጭምር ተመክሮበት አያውቅም።የባይደን አስተዳደር እና የምዕራቡ ፍላጎት ኢትዮጵያ ቀና ካለች በአፍሪካ ያለንን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የቀይ ባህርን የመቆጣጠር ኃይሏ ያድጋል ስለሆነም ኢትዮጵያን በራሷ ውስጥ በበቀሉ በጎሳ የሚከፍሏት ወያኔዎች ጋር ቆመን ጠልፈን እንጣላት ነው። ኢትዮጵያን የማጥፋት ፕሮጀክቱ ግብፅ ይግባ ሱዳን፣ እንደ አሁኑ የምዕራቡ ዓለም ቀልቡን አጥቶ የናወዘበት ጊዜ እኔ አላስታውስም።

ኢትዮጵያውያን ለግራ ለቀኙ አሉባልታ ዋጋ አንስጠው።ዓላማችን ኢትዮጵያ ላይ እናተኩር።የምዕራብ መገናኛ ብዙሃን እንዴት እንደወረዱ እና ተራ የመንደር ጠላ ቤት ወሬ ማውራት ሁሉ ላይ እንደደረሱ ለማየት የሚፅፉትን ማየት ነው። ይህ ትውልድ በወሬ የሚደናበር መስሏቸዋል። ለካ መውረድ የፈጠራ ችሎታንም አጥቦ ይወስዳል።ስንት ያውቃሉ የሚባሉት መሃል ኢትዮጵያ የታመሰ አስመስለው  የሚፅፉት ሁሉ ስታዩ የሀገሬ ገበሬ ምን ያህል አዋቂ እንደሆነ ተረድታችሁ ማረን ትላላችሁ።ባጭሩ ወርደዋል።አሁን የቀራቸው ቤተ መንግስት ውስጥ ማንኪያ ቢወድቅ እርሱን ቀይረው ቦንብ ፈነዳ ማለት ነው።ለነገሩ ቅጥረኛው ህወሓትን ለማገዝ ያላቸው አንዱ መንገድ በወሬ ኢትዮጵያውያንን ማወቅ ነው።ስለሆነም በወረደ ወሬያቸው ፈፅሞ አትታለሉ። የሽብርተኛው ህወሓት ቡድን ለራሱ በራሱ ሕዝቤ በሚለው ደምም ሰክሯል።ግራ ገብቶታል።የትም ቢሄድ ምንም ማድረግ እንደማይችል እና ዛሬም ሆነ ነገ ሁለቱም ለእርሱ ጨለማ እንደሆኑ ያውቀዋል።የሰራውን ስለሚያውቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን እንደሚያደርገውም ያውቃል።የእርሱ የእብደት ልፈፋ ከተስፋ መቁረጥ ሁሉ የመነጨ ነው።የምዕራቡም ሚድያ እና የባይደን አስተዳደር ቅዥት ምንጩ ኢትዮጵያን የማንበርከክ እና የመበተን ሥራ ነው። 

ኢትዮጵያን የሚያነሳት ከእግዚአብሔር ጋር የእያንዳንዱ ወንድ እና ሴት ኢትዮጵያዊ የቆረጠ ልብ፣ሥራ እና እስከመስዋዕትነት የቆረጠ ትግል ነው።በእዚህ ዓለምን እናስደምማለን።ኢትዮጵያ ማን እንደሆነች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የምናሳይበት የክፍለዘመናችን ግዙፉ ድል ለመቀዳጀት እንነሳ።ኢትዮጵያን በቢልዮን የሚቆጠር የዶላር የጥፋት ፕሮጀክት እንደማያስጎበድዳት፣የባይደን አስተዳደር የሌት ከቀን ሴራ እንደማያስጎነብሳት፣ የአረመኔው የህወሓት እና ጀሌው አውሬያዊ ተግባር እና ክህደት እንደማይሰብራት የምናሳይበት ጊዜ አሁን ነው። በእዚህ ኢትዮጵያ ስሟ የሚያርዳቸው ጠላቶቿ ዳግም የሚያንቀጠቅጣቸው ይሆናል።

የቆረጠ ልብ፣ለአሉባልታ የማይርድ ጀግንነት እና ለመስዋዕትነት የወሰኑ ወንድ እና ሴት ኢትዮጵያውያን ታሪክ ይሰራሉ።ለእዚህም ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።  ፌልትማን፣የባይደን አስተዳደር የአፍሪካ ቀንድ ተጠሪ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።ተልኮው ግልጥ ነው።በ1983 ዓም ሄርማን ኮህን የያዙትን ዓይነት መንገድ በመጠቀም ኢትዮጵያን ዳግም ለአውሬው ህወሓት እንድትጋለጥ በማደራደር ስም ለመቅረብ ነው።ሄርማን ኮህን የዛሬ 31 ዓመት ኢትዮጵያን ለንደን ላይ እንዳታለለ፣ ዛሬ ፌልትማን ይህንን ትውልድ አያታልለውም።ሄርማን ኮህን በወቅቱ ኢትዮጵያን ከወያኔ እና ሻብያ ጋር አደራድራለሁ ብሎ አሜሪካንን ወክሎ በመገኘት በኢትዮጵያ ላይ ቀልዶ ነበር።ዛሬም ድረስ በትውተር ገፁ የሚፅፈው የኢትዮጵያ አንድነት የሚፈታተኑ ጉዳዮች ላይ በማትኮር ነው።የአሁኑ ትውልድ ካለፈው ታሪክ ተምሯል።ሁለቴ መታለል የለም።አሁን ኢትዮጵያ ወይንም ሞት! ነው።በኢትዮጵያ ጉዳይ ላለፉት 27 ዓመታት ምን እንደሆንን የምናውቀው እኛ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ብቻ ነን። ያንን ስርዓት መልሶ እንዳይመጣ አድርገን አውርደነዋል።ዛሬ በበር እንዲገባ የሚፈቅድለት የለም። ኢትዮጵያንና ዕውነትን ይዞ በቆረጠ ልብ ውስጥ ብቻ እግዚአብሔር ይገባል።ይህ ድል ኢትዮጵያን በኃያላኑ ፊት ሁሉ የሚያስደምም የዘላለም ስም የሚተክል እና ኢትዮጵያን ዳግም የሚያነሳ የክፍለዘመኑ ታላቅ ድል ነው።

የመጨረሻውን ሳቅ የምንስቀው የኢትዮጵያ ኃይሎች ነን!

=============///==============


No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።