ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, November 13, 2021

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሌላ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወኑ ነው።

ኖርዌይ 

Voluntary Ethiopians and Norwegians agreed to assist Internally Displaced People (IDP) in Ethiopia with out any discrimination of ethnicity and Language..

  • በዘንድሮ የገና በዓል ለልጆቻችን ልንሰጥ ያሰብነው ስጦታ ከልጆች ጋር በመነጋገር በማስቀረት የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ እንደሚገባ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
  • በዓይነቱ ለየት ያለ አደረጃጀት ዛሬ ተመስርቷል።

=====================

ጉዳያችን ዜና /Gudayachn News

=====================

በመላዋ ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው አሁን ባለችበት ፈታኝ ጊዜ በምን መልኩ መርዳት አንዳለባቸው ሲያወጡ ሲያወርዱ ነበር የከረሙት።በእዚህም መሰረት ሁሉንም የሲቪክ ድርጅቶች፣በተለያዩ የኖርዌይ ግዛቶች የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ስብስቦችን እና ማኅበራዊ አደረጃጀቶችን ማዕከል ባደረገ መልኩ የጋራ አደረጃጀት ማስፈለጉ ላይ ተስማምተው ይህ አደረጃጀት እና ድርጅት ምን መምሰል እንዳለበት፣መተዳደርያ ደንቡን እና በዋናነት ምን መስራት ይችላል በሚሉ ጉዳዮች ላይ ላለፉት አምስት ወራት በአስተባባሪ ኮሚቴ ሲያዘጋጅ ቆይቶ ዛሬ ከመላዋ ኖርዌይ በዙም በተደረገ ስብሰባ ''ለኢትዮጵያ እንቁም በኖርዌይ'' የተባለ ድርጅት የመተዳደርያ ደንቡን እና ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚያስተባብሩ ሰባት አባላት ያሉት የአመራር አካላትን እና ሁለት የውስጥ ኦዲት እና ቁጥጥር መርጧል።በተለይ አመራሮቹ ሲመረጡ በመላዋ ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ለመወከልበተቻለ መጠን በኖርዌይ ካሉት ትላልቅ ከተሞች ለመወከል  በሚል የአመራሮቹን ስብጥር ለመጠበቅ ጥረት ተደርጎ ነበር።

በእዚህ መሰረት የሚከተሉት ለስራ አስፈፃሚነት ዕጩ ቀርበው የነበሩ ሲሆን 9ኙ ለስራ አስፈፃሚነት እና ለኦዲት እና ኢንስፔክሽን መርቷል።በእጩነት የቀረቡት የ11ዱ ስም ከእዚህ በታች ያገኛሉ። -

1) ዶ/ር ኃይሉ ከበደ ከስታቫንገር ከተማ 

2) ዶ/ር ነፃነት ግዛው ከትሮምሶ ከተማ 

3) አቶ አስማማው ተሻማሁ ከትሮንዳይም ከተማ 

4) ዶ/ር ፋሲል እጅጉ ከኦስሎ ከተማ 

5) ወ/ሮ ኢትዮጵያ ብሮተን ከኦስሎ ከተማ 

6) ኢንጅነር ስምዖን ጴጥሮስ ከኦስሎ ከተማ 

7) አቶ ሳምሶን ደረጀ ከበርገን ከተማ 

8) ኢንጅነር ክፍሌ አሰፋ ከበርገን ከተማ 

9) ወ/ሮ ገነት በቀለ ከበርገን ከተማ 

10) ፓስተር ዮሐንስ ከበርገን ከተማ 

11) ኢንጂነር ካሳሁን ገድሉ ከኦስሎ ከተማ 

በዛሬው የምስረታ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያውያን ኮምዩኒቲ ሥራ አስፈፃሚዎች እና አባላት፣የሲቪክ ድርጅቶች ሥራ አስፈፃሚዎች እና አባላት እንዲሁም የሃይማኖት ድርጅቶች ተወካዮች እና አባላቶቻቸው የተሳተፉ ሲሆን በቅርቡ በኖርዌይ ሕግ ምዝገባውን የሚያካሂድ ሲሆን አሁን በአፋጣኝ በሀገራችን በጦርነቱ ችግር የደረሰባቸው ወገኖቻችንን ዘር፣ሃይማኖት እና ቋንቋ ሳይለይ ድጋፍ ለማድረግ እንዲችል በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን የገንዘብ ማሰባስብ ሥራ እንዲጀምሩ ጥሪውን አስተላልፏል።

በመጨረሻም በተለይ አሁን የተቸገሩ ወገኖች ካሉበት አፋጣኝ ችግር አንፃር ከመደበኛ ድጋፍ በተጨማሪ በዘንድሮ የገና በዓል ለልጆቻችን ልንሰጥ ያሰብነው ስጦታ ከልጆች ጋር በመነጋገር በማስቀረት የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።በመጨረሻም ድርጅቱ የኢትዮጵያ ችግር እስኪቀረፍ ድረስ በቀጣይነት የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራ እና ወደ ሀገር ቤት በሕጋዊ መስመር እንዲላክ እንደሚያደርግ ተብራርቷል።የህ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተግባር በሌላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በናሙናነት ሊጠቀሙበት የሚችሉት መሆኑን ጉዳያችን ለማስገንዘብ ትፈልጋለች።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ከክፉ ሁሉ ይጠብቃት!


==========///==========


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...