=============
ጉዳያችን / Gudayachn
==============
ከሚሴ ዙርያ የሚገኘው የመከላከያ እና ሚሊሻ የህወሓት ወራሪን እያፀዳ ባለበት ሰዓት ከሚሴ ሕዝብ ደህንነት ሲባል ሙሉ ጥቃት ከተማ ውስጥ ባያደርግም በከሚሴ የገባው የህወሓት ወራሪ እና የሸኔ ታጣቂ ከግጭት አልፈው ፍጥጫ ላይ ናቸው።ወረራና ትንኮሳ በፈፀመባቸው የአማራ እና የአፋር ክልሎች ገዳይነቱ፣ ጨፍጫፊነቱ እንዲሁም ዘራፊና አውዳሚነቱን ያስመሰከረው ሽብርተኛው ህወሓት ዓላማውን ለማሳካት እንደ ፈረሰ ከሚጋልበው ሸኔ ጋር አሁን ላይ በከሚሴ ተፋጧል፡፡
ጉዳዩ ይህ ነው፡- ጁንታው ከከምሴ ከተማ ከመንግስት ተቋማት፣ ከግል ድርጅቶች ከእህል መጋዝኖች፣ ከሱቆችና ከመሳሰሉት የንግድ ድርጅቶች እንዲሁም ከግልሰቦች ቤት የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት ለፍቶና ደክሞ ያፈራቸውን ንብረቶች ከኋላ ባሰለፋቸው ጋሻ ጃግሬዎቹ በጉልበት እያሰገደደና እምቢ ያሉትን እየገደለም ጭምር በመዝረፍ በተሸከርካሪዎች እየጫነና እያሸሸ ይገኛል፡፡ ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ነው እያታገልኩ ያሉት በሚለውና ከጁንታው ጋር ጋብቻ ፈፅሞ ኢትዮጵያን ለማፍረሰ ከሚንቀሳቀሰው ህወሃት የሽብር ተልዕኮ ተቀብሎ በርካታ ንፁሃን የኦሮሞ ልጆችን እየጨፈጨፈ ባለው ሸኔ ታጣቂዎች መካከል አሁን ላይ ከሚሴን ጨምሮ በዙሪያዋ ባሉት ወረዳዎች እርስ በእርሳቸው እየተገዳደሉ ነው፡፡
ይህን ተከትሎም በሸዋ ሮቢት እና በአጣዬ ሆስፒታል የሚታከሙ ቁስለኞች አብዛኛዎቹ በሁለቱ ጽንፈኛ ቡድኖች የእርስ በእርስ የተኩስ ልውውጥ የቆሰሉ ናቸው፡፡ ንብረቱን በመዝረፍ እርቃኑን እያሰቀሩት ያሉት የአካባቢው ህዝብም ጭምር ከሁለቱ ሽብርተኛ ቡድን ታጣቂዎች ጋር ቅሬታዎችን ከማቅረብ አልፎ ቁጣውን በመግለፅም ጭምር ግጭት ውስጥ ገብቷል፡፡ የአካባቢው ወጣቶችም ከወላጆቻቸው የተዘረፈው ንብረት እንዲሁም ህወሃት ከዚህ በፊት በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈፀመው እኩይ ተግባር ሳያንስ አሁን ላይ በንፁሃን ዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለው ግድያ ራሳቸውን በማደራጀት ግጭት ውስጥ የገቡትን ሁለቱንም የሽብር ቡድኖች ለመታገል ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን፤ ይህን ለማሳካትም በከሚሴ የሚገኙ የህወሃት አመራሮችን ተከታትለው ለመግደል እንዲሁም የሸኔ ታጣቂ አመራሮችን ለመንግስት አሳልፎ ለመስጠት ውስጣዊ ትግል ጀምረዋል። ይህ የህወሃት አጸያፊ ድርጊት በሸኔ ውስጥ ጥያቄ እያስነሳ ሲሆን ከቡድኑ ጋር አጋርነት የፈጠርነው ለዚህ ከሆነ በጣም ተሳስተናል። ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ራሱ ህወሃትን በማጥቃት አካባቢያችንን ነፃ አውጥተን ራሳችን መቆጣጠር ይኖርብናል በሚል ከሚሴ አካባቢ የሚገኙ አንዳንድ የሸኔ አመራሮች ሚስጥራዊ ውይይት እያደረጉ መሆናቸውን ምንጮች ይገልጻሉ። ከዚህም ባላፈ የህወሃት አመራሮች ሸኔ ለጊዜው በውጊያ ላይ መሳተፍ የለበትም በሚል እያገለሉ መሆናቸው በቀጣይ መንግስትን ማስወገድ ብንችል እንኳን እንደ 1983ቱ ሁሉ መልሰው ሊያጠቁን እንደሚችሉ ፍንጭ የሚሰጥ ነው የሚል ስጋት አላቸው። በተጨማሪም የህወሃት የሽብር ቡድን የህዝብን ሃብት ሲዘርፍ ዝም ብለን ካየን በጊዜ ሂደት ህዝቡ ራሱ ሊዋጋን ይችላል፤ በዚህም ህወሓት ሊታደገን አይችልም የሚል ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡
ባጠቃላይ ህወሓት እና ሸኔ እርስ በርስ ለመመታታት ባለፈው የጀመሩትን መገዳደል ወደየለየለት ጦርነት ለመግባት ዝግጅታቸውን የጨረሱ ሲሆን አሁን ጥያቄው ማን ቀድሞ ይመታል የሚል ብቻ ነው።ይህ በእንዲህ እያለ በሰሜን ሸዋ የአማራ እና የኦሮሞ ሚሊሻዎች የሚያስደንቅ ህብረት እና አንድነት የፈጠሩ ሲሆን ደቡብ ወሎ በጥምረት እየገቡ የሚሸሸውን የህወሓት ወራሪ ማጥቃት መጀመራቸውን እና የጋራ የመረጃ መለዋወጥ ስራዎች ላይ ሁሉ የተቀናጀ ሥራ እየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment