===========
የጉዳያችን ማስታወሻ
===========
''At various points in their History the Ethiopians have repeatedly demonstrated that they are capable of living in interethnic harmony and build their common state. The general election this year, held in peace and in line with democratic standard this idea. High level of support for the government was demonstrated at recent mass demonstrations in Addis Ababa''
''' ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ደጋግመው እንዳስመሰከሩት በልዩነቶቻቸው መሃል አብሮ የመኖር እና የጋራ ሀገራቸውን የመገንባት ችሎታቸውን አሳይተዋል።በቅርቡ በሀገሪቱ የተደረገው ብሔራዊ ምርጫ በሰላም እና የዲሞክራሲ ደረጃን አሟልቶ መጠናቀቁ ለእዚህ ምስክር ነው።አሁን ያለው መንግስትም ከሕዝቡ ከፍተኛ ድጋፍ እንዳለውም በቅርቡ በአዲስ አበባ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በራሱ ገላጭ ነው።'' ያሉት በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የሩስያው ተወካይ አና ኢቭስትግኔቫ ሰኞ፣ጥቅምት 29፣2014 ዓም ማታ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባደረገው ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ላይ ነው።በእዚህ ስብሰባ ላይ የፀጥታ ምክር ቤቱ አባላት ኢትዮጵያን ርዕስ አድርገው ባደረጉት የግንዛቤ ማስጨበጫ ማለት የሚቻለው ስብሰባ ላይ በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ባደረጉት ንግግር ''እኛ ኢትዮጵያውያን ጥቅምት 24 ቀን በህወሓት የተደረገውን ጥቃት መቼም አንረሳውም'' ካሉ በኃላ ''እንደ አንድ ሀገር እኛ ኢትዮጵያውያንን በአንድ ላይ ያስነሳን ጉዳይ ለሀገራችን ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት ካለን ፅኑ ፍላጎት አንፃር ነው'' ብለዋል።
ከውጭ ለህወሓት የሚሰሩት እና ኢትዮጵያ እንድትተራመስ የሚፈልጉ ሀገሮች ከሚድያ ዘመቻ እስከ የኢኮኖሚ እቀባ፣ከአጎዋ የአሜሪካ የቀረጥ መብት ክልከላ እስከ ልዑክ ልኮ ማስፈራራት የቀራቸው የለም።በትግራይ እናቶች እና ሕፃናት እንዲሁም ወጣቶች ደም የሚነግዱት የህወሓት ፍቅር እንጂ የትግራይ ሕዝብ ረሃብ እና ሞት የማይገዳቸው አክቲቪስት ተብዬዎች ከአስፍልት መንበርከክ እስከ ገንዘብ ማዋጣት፣ከጀኖሳይድ ትርክት እስከ በኢትዮጵያ ላይ ስም የማጠልሸት ሥራ ሁሉ ሞክረዋል።አሁን የቀራቸው የለም። ህወሓት እና የትግራይ ወራሪ ከአስር ዓመት ልጅ እስከ 67 ዓመት አዛውንት እያንጋጋ እስከ ደቡብ ወሎ ድረስ ሕዝቡን ዘርቶት በፋኖ፣ሚሊሻ እና መከላከያ እያስጨረሰ ነው።አለኝ ያለውን ኃይል በምዕራብ ግንባር በኩል ወደ ሱዳን ለመውጣት መሬት ቢጭር የኢትዮጵያ ኃይሎች የማይቀመሱ ሆነውበት ተስፋ ቆርጦ ሽሬ ላይ በሻማ ቁጭ ብሎ የሚሆነውን መጠበቅ ሆኗል ስራው።ይህ ብቻ አይደለም።የህወሓት ማሰልጠኛ ማዕከሎች፣የመሳርያ ማከማቻዎች እና አሉኝ የሚላቸው መካናይዝድ ኃይል በመከላከያ ተመቷል።የአማራ ገበሬ እና የአፋር አርብቶ አደር ህወሓትን ባገኘበት ቦታ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን እንደገባ ውሻ እርምጃ እየወሰደ ነው።ከእርምጃው በኃላ ደግሞ ኢትዮጵያ የምታርፍበት እንዲሁም መሣርያውን መልሶ ስለሚታጠቅ ገበሬው ይህንን ሥራ ቀን ከሌት የሚሰራው ሥራ ሆኗል።
ትግራይ ውስጥ ክረምቱን በመጠኑ ይገኝ የነበረ ውሃ አሁን በጋው እየገፋ ሲሄድ ካለ ኤሌክትሪክ የማይነሳው የውሃ ማከፋፈያ መቆም ጭንቅ ሆኗል።ህዝቡ በውሃ ሲጠማ እነ ጌታቸው ብቻ የታሸገ ውሃ እየጠጡ በሕዝቡ የውሃ ጥም ይሳለቃሉ።ክረምቱን ገበሬው ያለችውን መሬት እንዳያርስ ገበሬውን ወደ ማሰልጠኛ እየላኩ ለጦርነት ሲማግዱት ስለሰነበቱ አሁን በትግራይ የተመረተ ምርት አይታሰብም።በውጭ ሆነው ግፋ በለው! እያሉ እነርሱ በምቾት እየኖሩ ሕዝቡን ያስፈጁት የህወሓት ደጋፊዎች ቢያንስ አሁን ለምግብ የሚሆን ነገር ሲገዳቸው አይታዩም።
ህወሓት በእዚህ ጊዜ ድርድር እንዲደረግ እና መውጫውን መንገድ ለማስቀመጥ ይፈልጋል።የባዕዳን አጋሮቹም በእግር እና በጥፍራቸው ህወሓትን ለማዳን ተደራደሩ የሚለውን ቃል እየተጠቀሙ ነው።የአፍሪካ ሕብረትን አልቀበልም ሲል የነበረው ጁንታ አሁን ኦባሳንጆ የሚቀመጡበት ሶፋ ሲያማርጥ ከርሟል። አሁን የውጭ እና የውስጥ የሽብርተኛው ህወሓት ''አጋሮች'' እና እራሱ ህወሓትም ጥይታቸውን ጨርሰዋል።አሁን የኢትዮጵያ መንግስት እና ሕዝብ ጊዜ ነው።ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲኦል ድረስ እወርዳለሁ ያለውን በሕዝብ ደም የታጠበው ህወሓት ላይ የሚወርድበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው።
==============////=============
No comments:
Post a Comment