ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, November 19, 2021

ከዛሬ ጀምሮ በመጪው ሳምንት ድረስ ጁንታው የመጨረሻ የሽብር ሥራ ለመስራት እያሰበ ነው። በሁሉም መስክ መንግስት እና እያንዳንዱ ሰው ሊተገብራቸው የሚገቧቸው ተግባራት
===============
ጉዳያችን /Gudayachn
===============

አሁን ያለው ሁኔታ 

👉 የሽብርተኛው ህወሓት ወራሪ ከሰሜን ወሎ ይዞ ወደ አፋር ሚሌ ይንደረደርበት የነበረው ምሽግ በመሰበሩ እና በአስር ሺዎች የሚቆጠር ጀሌ ስላለቀበት የተረፈውን እና የሸሸውን ጀሌ በቻለው ወደ ሰሜን ሸዋ ለመላክ እየሞከረ ቢሆንም የሰሜን ሸዋ ገበሬ ጨምሮ ልዩ ኃይል እና መከላከያ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል።

ጁንታው የመጨረሻ የሽብር ሥራ ለመስራት እያሰበ ነው።የሚያስፈልጉ የጥንቃቄ አካባቢዎች 

👉 በእዚህ ሳምንት መጨረሻ እና በመጪው ሳምንት ላይ ጁንታው የመጨረሻ እንጥፍጣፊ ሙከራውን በተለይ በዲጂታል ወሬ ለመዝመት የውስጥ እና የውጭ ኃይላቸውን ከምንጊዜም በላይ እንዲዘምቱ ተነግሯቸዋል።በእዚህ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በቀጣዩ ሳምንት በዋናነት አጠናክረው ሊያደርጉ ያሰቡት -
  •  በሁሉም ማኅበራዊ ሚድያ የጁንታው ጀሌ ገና ያልያዟቸው ከተሞች እንደ ደብረብርሃን ያሉት በሙሉ እንደተያዙ ተደርጎ በሰፊው ለማውራት፣
  • ለእዚህ ዘመቻ የሚታወቁት ሚድያዎች በተጨማሪ ሁሉም በራሱ አዳዲስ የማኅበራዊ ሚድያ እየከፈተ የወሬ ዘመቻ ላይ እንዲዘምት፣
  • የውስጥ ወኪሎቻቸው ከእዚህ በፊት ከነበረው በተለየ በከተሞች ውስጥ በቻሉት የወሬ ዘመቻ ላይ እንዲሰማሩ።የጁንታው ሰራዊት ብዙ እንደሆነ ማውራት፣ የስነ ልቦና ጦርነት ማድረግ 
 👉 አሁን በአዲስ አበባ የሽብርተኛው ህወሓት ሴል እየተበጣጠሰ ስለሆነ ሁሉም መዋቅሩ ተበጣጥሶ ሳያላቅ የቀረው ቡድን በቶሎ አንድ አይነት ሽብር በአዲስ አበባ እና ደብረ ብርሃን ላይ እንዲፈፅም።በእዚህም በሰፊው በአዲስ መልክ ከሚደረገው ዘመቻ ጋር ትንሹን የሽብር ጥቃት ተጋኖ እንዲወራ በውጭም ሆነ በውስጥ እንዲዘመት።ለእዚህም የቀረው የሸኔ ሴል በትልልቅ ከተሞች ሰላማዊ ሕዝብ ላይ ጥቃት እንዲፈፅም እና የመንግስት የፀጥታ መዋቅር የተዳከመ አስመስሎ እንዲቀርብ ማድረግ።

 👉 የኃላ ረድፍ ሆነው በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የጁንታው ጠላት ነን የሚሉ ግን ለአማራ የሚቆረቆሩ መስለው መንግስትን ከህዝብ ጋር የሚያጣሉት ዩቱበሮች እና የማኅበራዊ ሚድያ አንቀሳቃሾች አዳዲስ የማጣያ አጀንዳዎች እንዲፈጥሩ እና በተለይ መንግስት በአማራው ላይ ሴራ ሰራ የሚል አጀንዳ ማናፈስ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲሰሩ እና  ለእዚህ ሥራ ደግሞ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ነገር ግን በተግባር በሕዝብ ላይ ለሽብርተኛው ቡድን የፕሮፓጋንዳ ተኩስ  ዩቱበሮች ትኩረት ተደርጎባቸዋል።

 👉 የተቀናጀ የዲጂታል ጥቃት ለመፈፀም መሞከር።በተለይ ይህ ጥቃት በመንግስት ድርጅቶች እና የህዝብ አገልግሎት ሰጪ አካላት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ለማድረግ 

መንግስት እና ሕዝብ ምን ያድርጉ?

መንግስት ምን ያድርግ?

👉 መንግስት የውጭ ለምሳሌ እንደ አሜሪካ ያሉ ልዑክ ጋጋታ የመንግስት ቁልፍ ሰዎችን ሥራ አስፈትቶ የሚወጥር አጀንዳ መስጠት መሆኑን እና የልዑኩ ምልልስ የመንግስትን ስሜት ለመለካት እና የማደናገርያ የተኩስ ሽፋን ለሽብርተኛው መስጠት በመሆኑ። እነኝህ ልዑካን የሚያመጡትን አጀንዳዎች ለጊዜው  ኃይሉ ጦርነቱ ላይ ማትኮር አለበት።

👉 መንግስት ራሱ ለውጭ ኃይሎች አጀንዳ መስጠት አለበት።ለምሳሌ የምዕራባውያን ለሽብርተኛው ቡድን እየሰጡ ያሉትን መንግሥታት  በግልጥ በተባበሩት መንግሥታት መድረክ መክሰስ እና ግልጥ ደብዳቤ ለተባበሩት መንግሥታት በመፃፍ ማስጠንቀቅ አለበት።በእዚህም 

1) መንግስት አጀንዳ ሊሰጡ የሚፈልጉ አካላትን ለራሳቸው አጀንዳ መስጠት ይችላል።

2) የኢትዮጵያ ወዳጆች የትኞቹ ሀገሮች ወይንም ሀገር በቀጥታ ጣልቃ እየገባ መሆኑን እንዲረዱ ያደርጋል።የችግሩን ዲግሪም እንዲረዱት ያደርጋል።

👉 መንግስት የኢትዮጵያን ህልውና የማስከበር አንቀሳቃሽ ሞተር እና አስተባባሪ በመሆኑ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የገቡ ኤምባሲዎች ኢትዮጵያን ለቀው እንዲሄዱ ማድረግ፣በሀገር ውስጥ እየተተገበረ ያለው አዋጅ ጠንከር ብሎ እንዲቀጥል ማድረግ አለበት።የለሰለሱ አካሄዶች ፈፅሞ አያስኬድም።እዚህ ላይ ''ጠላትህን ለማሸነፍ ጠላትህ እየሄደ ባለበት መንገድ ካልሄድክ አታሸንፍም'' የሚለው አባባል ማሰብ ያስፈልጋል።

👉 መንግስት አንድ ልዑክ ለምሳሌ በክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ የሚመራ ልዑክ ወይንም የተለያዩ ልዑካን በተለያየ አቅጣጫ በተመረጡ የአፍሪካ፣የአውሮፓ እና ጃፓን ጭምር ሄደው በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ማስረዳት እና ዲፕሎማሲያዊ ጦርነቱን መመከት አለባቸው።ልዑኩ በአሜሪካ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ወዳጅ የምክር ቤት አባላትን ለማናገር ሁሉ መሄድ አለበት።በእዚህም ከንግድ ሰዎች ጋር እና ከእየሃገራቱ ሚድያዎች ጋር የመነጋገር እና የማስረዳት ዕድል ሁሉ መጠቀም ይችላሉ።የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት ወይንም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አፍሪካ በአካል እየተገኙ በኢትዮጵያ ላይ ለመዝመት ያደረጉት  ጥረት ኢትዮጵያ መማር አለባት።በአካል መሄድ አስፈላጊ ነው።

👉 መንግስት የፕሬስ መግለጫዎቹን መቀጠል እና የዲጂታል ጥንቃቄውን እያደረገው እንዳለው ማጠናከር።

ሕዝብ ምን ያድርግ?

ትልቁ ኃላፊነት የህዝብ ነው።ሕዝብ ማለት ከሀገር ቤት እስከ ውጭ ያለው ሁሉ ያጠቃልላል።በቀጣይ ቀናት በተለየ 

👉 በቀዳሚነት ስነልቦናውን ያጠንክር።ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።በእዚህ መጠራጠር አይቻልም።የጠላት ዋና ኢላማ የሕዝብ ስነ ልቦና መምታት ነው።ለእዚህም ዋና መንገዱ በውሸት ወሬ የስነ ልቦና ጦርነት ማድረግ ነው።ስለሆነም ለስነ ልቦና ጦርነት ላለመጋለጥ መስማት የሌለበትን አለመስማት።ይልቁንም አፀፋዊ ጥቃት መፈፀም የህዝብ ኃላፊነት ነው።

👉 እያንዳንዱ በእያንዳንዱ ቦታ እና በሚኖርበት ቦታ ከማናቸውም የሽብርተኛ ጥቃት የመጠበቅ ኃላፊነቱ የራሱ መሆኑን ማመን።

👉 እያንዳንዱ ሰው በቤተሰብ ደረጃ አጀንዳ አድርጎ መወያየት አለበት።ይህ የሽብርተኛው ሥራ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ቤተስቡን ለማፍረስ መሆኑን ባልና ሚስት እንዲሁም ልጆች ሊያምኑበት ይገባል።በእዚህ መሰረት በውጭ ያለው በገንዘብ የተፈናቀሉትን በመርዳት፣በሀገር ቤት ያለው በዘመቻው እና በሁሉም መስክ ለሚያደርገው ሥራ ቤተሰቡ ጭምር ድርሻውን እንዲያውቅ ያደርገዋል።

 👉 በቅርቡ ያሉት በጥቅም፣በመዋለል እና በቸልተኛነት አሁን ኢትዮጵያ የገጠማት የህልውና ጉዳይ ዝቅ አድርገው በማሳየት ሕዝብ ሊያዘናጉ የሚሞክሩትን በማስተማር፣ ሆን ብለው ለጠላት ያደሩትን ደግሞ ለፍርድ በማቅረብ እና በማኅበራዊ ቅጣት ጭምር የራሱን ውሳኔ መወሰን አለበት።

ማጠቃለያ 

አሁን ኢትዮጵያ የገጠማት ፈተና የማታሸንፈው አይደለም።የፈተናው አመጣጥ በአንድ ጊዜ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እና ከውስጥ የተነሱባት ከሃዲዎች ጋር በአንድነት መሆኑ ብቻ ነው የፈተናው ክብደት ያመጣው።ሕዝብ ወስኗል።ይህ በራሱ በቂ ነው። ይህም ሆኖ ግን ከዛሬ ጀምሮ በተለይ በቀጣይ ሳምንት ላይ ሽብርተኞቹ ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ የከተማ መዋቅራቸው እየታደነ በመሆኑ የቀራቸውን ሴል ከመያዙ በፊት አጥፍቶ ለማጥፋት ምንም አያደርግም ማለት አይቻልም። አይሆንም ከማለት ይሆናል ብሎ በስነ ልቦናም በተግባርም የበለጠ ዝግጁ መሆኑ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም።የሽብርተኛው ህወሓት ቡድን ቀሪ መጠቀምያዎቹ ሁለት ናቸው። እነርሱም የውሸት ፕሮፓጋንዳ በማድረ የህዝብ ስነልቦና ለመጉዳት መሞከር እና የሽብር ጥቃት በሰላማዊ ሕዝብ ላይ መፈፀም ናቸው።ሁለቱም የሚከሽፉት ለሁለቱም ጥቃት ላለመጋለጥ በሚደረግ የተቀናጀ የህዝብ ሥራ እና የውስጥ አሾክሿኪን ለይቶ በመቅጣት ነው።

=========////===========

No comments: