ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, January 20, 2020

የጥምቀት ብሔራዊ በዓላችንን ደስታ ለመንጠቅ የፈለጉ አልተሳካላቸውም። የስነ-ልቦና ዘመቻቸው ሙሉ በሙሉ ከሽፏል!



  • ሳትሰለፍ እና ሳትለፈልፍ ኢትዮጵያዊ የሞራል ልዕልናህን የምትሰቅልባቸው ቀላል መንገዶች በእዚህ ፅሁፍ ውስጥ ተካተዋል።ሕዝብ አንቂዎች ሃሳቡን ወስደው በግዙፍ መልክ ሊያንቀሳቅሱት ይገባል።


ጉዳያችን / Gudayachn
ጥር 11/2012 ዓም (ጃንዋሪ 20/2020 ዓም)

=============
የጥምቀት በዓል ባብዛኛው ተጠናቋል:: የቅደሰ ሚካኤል ታቦታት ግን ነገ ቃና ዘገሊላ በዓል ስለሆነ እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ወደ መንበራቸው ይገባሉ::እነኝህ ታቦታት ደግሞ ሌላው ጋር ለማጀብ ሄዶ የነበረው ምዕመን በብዙ እጥፍ ሆኖ የሚያጅባቸው ታቦታት ናቸው።በዘንድሮው ጥምቀት ባብዛኛው በሚያስደስት መልኩ ተፈፅሟል::እንደ ሆሳዕና ያሉ ቦታዎች ችግር ለመፍጠር ሙከራ ተደርጎ ከሽፏል::ከእዚህ ተምረናል::
ሐረር ስርዓት አልበኞች ታቦታቱን ለማስቆም ሞክረዋል÷የክልሉ ፖሊስ ድርጊት ህዝብ አሳዝኗል÷ሰው ቆስሏል በእዚህ አዝነናል::ሁሉም በእምነቱ ለማይገፋባት ኢትዮጵያ የበለጠ መስራት እንደሚገባ ከምን ጊዜውም በላይ ግልጥ ሆኗል::

መንግስት በተቻለ ለጸጥታው መጠበቅ መድከሙ ይታወቃል::በክልል ደረጃ ያሉት የጸጥታም ሆነ የአመራሮች ዘገምተኛ እና የግል ፍላጎታቸውን በአመራር ስልጣናቸው ላይ ለመጫን ሲሞክሩ እና ችግር ሲፈጥሩ ታይተዋል።በአጠቃላይ መንግስት ያደረገው ዝግጅት ብቻ ሳይሆን የህዝቡ በተለይ የወጣቱ የትቀናጀ የመረጃ አሰራር ሁሉ በራሱ ይህ የጥምቀት በዓል አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።እያንዳንዱ የሚጠበቅበት ገብቶታል።ኃላፊነት ተሰምቶታል።ለአገሩ ሰላምም ሆነ ለሁሉም ዕምነት በእኩል አገሬ ብለው የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለማጠልሸት የሚፈልጉ ስርዓት አልበኞች ችግር ለመፍጠር መሞከራቸው በራሱ አስተማሪ ነው።

ጉዳዩ ስነ ልቦናዊ ጦርነት ነው 

በጥምቀት ሰሞን ከሆነው አንዱ የፕሮፌሰር መራራ ኦፌኮ ጀዋርን እና በኦሮምያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለመከፋፈል የቤት ሥራ የተሰጠው ዲያቆን ኃይለ ሚካኤል የተባለ ግለሰብ በሰላሌ የምርጫ ቅስቀሳ በሚል ከከተራ አንድ ቀን ሲቀረው ጀዋርን ከጀርባው አቁሞ (ጀዋር በደስታ ሲፍነከነክ ይታያል)  የኦሮሞን ሕዝብ በራሱ የሚከፋፍል፣በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ግልጥ የሆነ ጦርነት አውጁአል።

በእዚሁ ንግግሩ ላይ የደብረ ሊባኖስን ገዳም ሳይቀር ቃል በቃል ጠቅሶ ''ሕዝብ ሰብሮ እንዲገባ'' መልዕክት አስተላልፏል።ከእዚህም በተጨማሪ ''ቤተክርስቲያን የፊውዳሎች  የፖለቲካ ኤምባሲ ነች'' በማለት  ሲናገር ተሰምቷል።እነኝህ የጥላ ንግግሮች የሚናቁ የጥላቻ ንግግሮች አይደሉም።ሆኖም ግን ዋና ግባቸው ስነ ልቦናዊ ጦርነት በኢትዮጵያውያን ላይ መክፈት ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማጥፋት እንዲሁም ከሕዝቡ ጋር ለማጋጨት በብዙ ትውልዶች ተሞክሯል።ግን አልተቻለም።ባለመቻሉም ቅድምያ የስነ ልቦና ጦርነቱ ተመራጭ ሆኖ ለጥፋት ኃይሎች ታይቷቸዋል።በቅድምያ ግን የእዚህ አይነት የምርጫ ቅስቀሳ  እየሰሙ ዝም ያሉት የምርጫ ቦርድ፣  የማዕከላዊው መንግስት፣የኦሮምያ ክልል ባለሥልጣኖች፣ በኦፌኮ፣በጀዋር፣በዲያቆን ኃይለ ሚካኤልም ሆነ የጥላቻ ዘመቻ ባስተላለፉት የኦኤምኤን ሚድያ ላይ ምንም ዓይነት ሕጋዊ ርምጃ ባለመውሰዳቸው በሕግ ያስጠይቃቸዋል።ይህ ጉዳይ ደግሞ በተከታይ በሚፈጠሩ ችግሮች ምርመራ ላይ መነሻው ወደኃላ ሲሄድ እንደ ኦፌኮ የምርጫ ዘመቻ ንግግሮች መሆናቸው ድምዳሜ ላይ ስለሚደረስ መቼም መቼም ከፍርድ ማምለጥ አይቻልም።ለእዚህ መፍትሄው በፍጥነት የማያዳግም ሕጋዊ ርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።ርምጃው በመግለጫ ጋጋት የሚፈታ አይደለም።ተግባራዊ ሕጋዊ ርምጃ የመንግስት አካላት ማሳየት ግዴታቸው ነው።ይህ ካልሆነ አብረው ይጠየቃሉ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን የስነ-ልቦና ዘመቻውን ግብ እና መነሻ በሚገባ ተረድቶ ዘመቻውን ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ ነው ያለበት።የፅንፍ ኃይሎች ዋነኛ መለያቸው የበታችነት ስሜት መሰቃየታቸው ነው። ይህንን የበታችነት ስሜት ስቃይ የሚያስታግሱት ድሮ እንዲህ የሚባል ሰው እዚህ ቦታ አንድ ዛፍ ተክሎ ነበር አሉ እና የመሳሰሉ ታሪኮች እያነሱ አሁን ያለውን ሕዝብ የምያጋጩበት ታሪኮች በመተረክ ነው።በእዚህ አሁን ያለውን ሕዝብ ስነ-ልቦና ያሸበሩ እንደሆነ ያስባሉ።ያልተገነዘቡት ነገር ግን ይህ አካሄድ ሁለት ነገር ይዞ እንደሚመጣ ነው።አንድ፣ከምር የዛፉ ተካይ ታሪክ ሕዝብ ዛሬ አይጠቅም ብሎ ያሰበውን ታሪክ ይዞ የወጣ ቀን የፈሩት የበታችነት ስሜት በከፋ መልኩ እንደሚከሰት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ህዝቡ በበለጠ እርስ በርሱ እንዲከባበር እና የመርዘኞች አካሄድ አደጋ ከማምጣቱ በፊት እነርሱን ለማሳፈር እንደሚነሳ ነው።

ኢትዮጵያውያን ወደፊትም ሞራላዊ እና ስነልቦናዊ ልዕልናችሁን ስቀሉባቸው!

የዘንድሮ 2012 ዓም  የጥምቀት በዓል በብዙ የኢትዮጵያ ክፍሎች የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከምንጊዜውም በላይ ደምቆ ወጥቶ በነፃነት ተከብሯል።ከጅጅጋ እስከ አርባንምጭ፣ከጋምቤላ እስከ መቀሌ፣ከሞያሌ እስከ ጉጂ ዞን፣ከሐዋሳ እስከ አሶሳ፣ከጎንደር እስከ ከሚሴ፣ከአዲስ አበባ እስከ ባሌ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከታቦታቱ ጋር በድምቀት ታይቶ ተከብሯል።ይህ በእንዲህ እያለ የስነ ልቦና ጦርነቱን ለማድረግ ከፅንፈኛ ኃይሎች ድርጎ የለመዱ በአንዳንድ ቦታዎች በተለይ በአብዛኛው የኦሮምያ ክልል የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲያስወርዱ፣ሪባን ጭምር እንዳትይዙ በሚል ችግር ፈጥረዋል።ድርጊቱ የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን በመንግስት የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ ሁሉ የድርጊቱ ተሳታፊ ሆነዋል።ይህ በህጋዊ መልኩ ሲታይ የመንግስት ግልጥ ክስረት ያሳያል።በመጀመርያ ደረጃ ጉዳዩን በተራ የአስተሳሰብ ልክ ብናስበው  ግለሰብ በራሱ የፈለገውን  የቀለም ሕብር የመያዝ መብት አለው። ቤተክርስቲያን እንደ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የተለየ መብት አላት።ለግለሰብ መከልከል የማትችለውን መብት ለተቁአም ልትከለክል አትችልም።የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ደግሞ የክርስቲያን ወይንም የሙስሊም አልያም የአይሁድ ዕምነት መለያ አይደለም።የክርስትናም፣የእስልምናም ሆነ የአይሁድ አባት በኖህ ዘመን ከሰማይ የተሰጠ በሁሉም የሰው ዘር እና በእግዚአብሔር መካከል የተገኘ ቃል ኪዳንን መነሻ ያደረገ ነው።ይህ ማንንም ሊያጣላ አይችልም።

በተግባር የሞራል ልዕልናው እንዲህ ይሰቀላል

በመቀጠል የልዕልናውን ደረጃ መስቀል ተገቢ ነው።እንዴት? ለሚለው 
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ምንም ምልክት የሌለበት ሱቅ ምንም ዓይነት ግብይይት ባለማድረግ፣የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላም የሌለው ማንኛውም ምግብ ቤት ሳትቃወመው ከራስህ ጋር ተነጋግረህ ፈፅሞ ግብቶ አለመመገብ፣የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በትንሹም ቢሆን ሻጥ ያደረገች የጉልት ቸርቻሪም ብትሆን ደጋግሜ በመግዛት ስፈልግ የፈለኩትን ያህል ገንዘብ በመጨመር፣የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላም የማይታይበት የቴሌቭዥንም ሆነ የፖስተር ማስታወቂያ መንግስታውም  ቢሆን ፈፅሞ እንደማልቀበለው እና ባለመግዛት፣የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የማይታይበት ማናቸውም መጠጥም ሆነ የስነ ጥበብ ዝግጅት፣ልብስም ሆነ ማስቲካ ሳይቀር  አለመግዛት።ሳትሰለፍ እና ሳትለፈልፍ ኢትዮጵያዊ የሞራል ልዕልናህን የምትሰቅልባቸው ቀላል መንገዶች ከላይ የጠቀሱት እንደመነሻ ተነስተዋል።ወደፊትም በበለጠ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በገነት እና በሲኦል ሳይቀር ቅዱሳኑም ሆኑ ርኩሳኑ መናፍስት እስክገርማቸው ድረስ አብዝተህ አሰራጨው።ማንም ከፈለገ ከሲኦል ወይንም ከገነት ውጪ ዓለም ካለ ወደዚያ  የመሄድ መብቱን እናከብርለታለን።


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...