ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, January 18, 2020

በኢትዮጵያ የ2012 ዓም የጥምቀት በዓል አከባበር ዝግጅት ብዙ ነገሮች አመላካች ሆኗል።ዝግጅቱ በኦሮምያ ፣ሆሳዕና ፣አርባምንጭ፣አዲስ አበባ፣ ጎንደር ምን ይመስላል? (ፎቶዎች ይመልከቱ)

ጉዳያችን ዜና /Gudayachn News
ጥር 9/2012 ዓም (ጃንዋሪ 18/2020 ዓም)

በኢትዮጵያ የጥምቀት በዓል ከእሁድ ጥር 10 ጀምሮ እስከ ጥር 12 ድረስ ይከበራል።በዓሉ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የተላያዩ መልክ ይዟል።የበዓሉ አከባበር በራሱ የብዙ ነገሮች አመላካች ሆኗል።

- በኦሮምያ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከሪባን ጀምሮ ተከልክሎ ሕግ የሚያስከብር ጠፍቷል።ሻሸመኔ ዋና ማሳያ ሆናለች።በኦሮምያ ያሉ የክልሉ ተወላጆች የክልሉ የፀጥታ ኃይል ከፍተኛ በደል እየፈፀመባቸው ነው የሚናገሩት።በውጭ አገር ኢትዮጵያውያን የቤተ ክርስቲያኒቱን ዓርማ መስቀል ያልተከለከሉትን በአገራችን ተከለከልን የሚል ምሬት ይሰማል።ጉዳዩ በኦሮምያ የሕግ መጥፋት አመላካች ሆኗል።አብዲሳ አጋ፣ጃጋማ ኬሎ እና ብዙ ሚልዮኖች የሞቱላት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዛሬ በኦሮምያ ጥምቀት በዓል ላይ እንዳይታይ መደረጉ የክልሉ አስተዳደር ከፅንፍ ኃይሎች ጋር እየሰራ ለመሆኑን ማሳያ ነው የሚሉ በርካታ የኦሮምያ ክልል ነዋሪዎች አሉ።

- ሰሜን ሸዋ ፍቼ ዛሬ ረፋዱ ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መስቀል የተከለከሉ ወጣቶች ተፋጠዋል።በጣልያን ሰማዕትነት የተቀበሉት የአቡነ ጴጥሮስ አገር ፍቼ ሰንደቅ ዓላማ መስቀል ተከልክላ ከተማው ውጥረት ላይ ነች የሚለው ዜና በራሱ የክልሉ አደገኛ አካሄድ አመላካች ነው።

- በሆሳዕና ህዝቡ ለረጅም ጊዜ የጥምቀት በዓል ማክበርያ ቦታ ጠይቆ የከተማው አስተዳደር ከልክሎት እስከ ደቡብ ክልል ድረስ አቤት ብሎ  ክልሉ 20ሺህ ካሬ ፈቅዶ ለሆሳዕና ከተማ ምክርቤት ደብዳቤ ከፃፈ ሳምንት ቢሆነውም እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ኮሚቴው  ቢጠብቅም የከተማው ምክርቤት ጉዳዩን በመከልከሉ የአገረ ስብከቱ ዘንድሮ በሆሳእና ጥምቀት አለመኖሩን በሃዘን ገልጦ ደብዳቤ አውጥቷል።ጉዳዩ ከፍተኛ ውጥረት ፈጥሯል።በመላው ኢትዮጵያ የሚኖሩ  በየትኛውም ቦታ ጥምቀት የሚያከብሩ ሆሳዕናን እንዲያስቡ በማኅበራዊ ሚድያ ጥሪ እየተላለፈ ነው።

-  በጎንደር ከሰላሳ ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ጨምሮ እስከ ሁለት ሚልዮን ሕዝብ ለበዓሉ እንደምታደም ተገልጧል።በተለይ የጎብኚው ቁጥር እስከ ሁለት ሚልዮን እንደሚደርስ የዘገበው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የከተማዋን  ባለስልጣናት ጠቅሶ ነው።

- በአርባምንጭ፣አዲስ አበባ እና ጋምቤላን ጨምሮ በዓሉ በደመቀ ሁኔታ ሊከበር ከፍተኛ ዝግጅት ላይ ነው።
ከእዚህ በታች ያሉት ፎቶዎች ለታሪክ የሚቀመጡ ናቸው።


ሻሸመኔ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ያለው ሪባን ተከልክሎ ህዝቡ ይህንን እንዲሰቅል ተገዷል።
የሆሳዕና ምእመናን የጥምቀት በዓል ማክበርያ ቦታ ተከልክለው በሃዘን ተቀምጠው።

 አዲስ አበባ ጎዳናዎች እንዲህ ደምቀዋል ቻይናውያን ሳይቀሩ 
 አርባምንጭ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ 
 አዲስ አበባ ተክለሃይማኖት አካባቢ 
 ጋምቤላ ዛሬ 
 ጋሞዎች ጥምቀት ለማክበር ጎንደር ቀርበዋል። 
 ጋሞዎች ለጥምቀት በዓል  ወደ ጎንደር ሲገቡ 
 የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የሚልዮኖች ሰማዕታት ውጤት ጎንደር ላይ እንዲህ በእናቶች ተስማለች።
 ጎንደር ለጥምቀት በዓል ዝግጅት ሙስሊም ወገኖቻችን ከክርስቲያኖች ጎን አብረው ሥራ ላይ 

 አዲስ አበባ ተክለሃይማኖት አደባብይ ላይ የተሰራው የታቦት ማደርያ በወጣቶች የተሰራ 
  አዲስ አበባ ተክለሃይማኖት አደባብይ ላይ የተሰራው የታቦት ማደርያ በወጣቶች የተሰራው በምሽት ይህን ይመስላል።
 አዲስ አበባ ተክለሃይማኖት አደባብይ ላይ የተሰራው የታቦት ማደርያ በወጣቶች በሥራ ላይ እያለ 


ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

No comments:

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...