ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, January 16, 2020

የሰሞኑ የዋሽንግተኑ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር በጥሩ ሁኔታ መፈፀሙን የሶስቱም አገሮች ልዑካን አስታወቁ።Ethiopia,Egypt and Sudan officials say they have reached a preliminary agreement on Ethiopian Renaissance Dam negotiation in Washington D.C

ሰባ በመቶ የተጠናቀቀው የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ  

ጉዳያችን ዜና /Gudayachn News
ጥር 7/2012 ዓም (ጃንዋሪ 16/2020 ዓም)

በዋሽንግተን ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙርያ በኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የውሃ ሚኒስትሮች መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር በጥሩ ሁኔታ ማለቁን የሶስቱም አገሮች ልዑካን በሰጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።በድርድሩ ላይ የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን ምንቺን እና የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ተገኝተዋል።

የግድቡ ሥራ 70% መጠናቀቁ የተነገረው የታላቁ የአባይ ግድብ አወዛግቦ የነበረው ግብፆች ባነሱት የውሃው የመሙላት ጊዜ ላይ እና የድርቅ ወቅት በሚለው ትርጉም ላይ ነበር።በእዚህ መሰረት በአሁኑ ስምምነት ኢትዮጵያ በጠየቀችው መሰረት የግድቡ መሙያ ጊዜ ድረጃ በደረጃ የሚፈፀም ሆኖ በዋናው የኢትዮጵያ የዝናብ ወቅት ማለትም ከሐምሌ እስከ ነሐሴ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ መስከረምን ሊሻገር እንደሚችል ተስማምተዋል። የድርቅ ወቅት የሚለውን ትርጉም እና በእነኝህ ወቅት የሚወሰዱት ርምጃዎች በተመለከተ ሶስቱም አገሮች በሰጡት መግለጫ የድርቅ ወቅት  በተመለከተ በሶስቱም አገሮች በጋራ የሚወሰድ የጋራ ኃላፊነት እንደሚሆን እና የድርቅ ጊዜውን እንዴት እንደሚይዙት  እና እንደሚወጡት በጋራ ገምግመው እርምጃ የሚወሰድ እንደሆነ ነው የተነገረው።ይህንን አስመልክቶ የሶስቱ አገራት ልዑካን በሰጡት መግለጫ ላይ -

''ተደጋጋሚ ድርቅን እና ጊዚያዊ ድርቅን በተመለከተ አያይዙን ሶስቱም አገሮች በጋራ ኃላፊነት ይወስዳሉ'' 
''There is a shared responsibility of the three countries in managing drought and prolonged drought,''

የጋራ መግለጫው እንደገለጠው ይህ የአሁኑ መግባባት ግድቡን በተመለከተ የመጨረሻ ስምምነት ሳይሆን በቀሪ ነጥቦች ላይ ውይይቱ ዋሽንግተን ላይ ጃንዋሪ 28-29/2020 ዓም እኤአ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

በሌላ በኩል የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በትውተር ገፃቸው በእንግሊዝኛ ባሰፈሩት ፅሁፍ 

''የታላቁ የህዳሴ ግድብ በተመለከተ አስፈላጊ እና ወሳኝ ውጤት አግኝተናል።ከጎናችን የቆማችሁ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ እናመሰግናለን።በድርድሩ ያገኘነውን ውጤት ወደ ሕጋዊ ሰነድ እና መመርያዎች ይቀየራሉ'' ብለዋል።


ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...