ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, April 14, 2013

ይህ ጉዳያችን ካልሆነ ምን ጉዳያችን ሊሆን ይችላል? ኢትዮጵያ መሬት ባከራየቻቸውም ሆነ ከሸጠችላቸው ኩባንያዎች ሃገራት ጋር ክርክር ቢነሳ ጉዳዩ የሚታየው በ አለም አቀፍ ገላጋይ ፍርድ ቤት ነው

ኢጣልያ በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል በ ኤርትራ ለመጀመርያ ጊዜ ቦታ ማግኘት የጀመረችው በ አሰብ ግዛት ሩባርቲኖ በተባለ የመርከብ ኩባንያ አማካይነት ከ አንድ ሱልጣን   በ 1869 ዓም በገዛችው ትንሽ መሬት መሆኑ ይታወቃል። እንግዲህ ሃገራችንን ከ አንድ መቶ አመታት በላይ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ የቀጠለ ፖለቲካዊም ሆነ ምጣኔ ሃብታዊ ችግር እየፈጠረ መሆኑ ይታወቃል። 

አፕሪል 14/2013 ዓም በኢሳት ቴሌቭዥን በቀረበው ''የእሁድ ወግ'' የውይይት መርሃግብር ላይ አቶ ዳንኤል ጥላሁን በካናዳ ቶሮንቶ የህግ ባለሙያ ስለ መሬት ለውጭ ባለ ሃብቶች መሸጡ ጉዳይ ያነሱት ሃሳብ ሚዛን የሚደፋ እና ብዙ ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው አይመስለኝም። ቀድሞ ስለመሬት ማከራየት ሳስብ ስጋት ይሆናል ብዬ የማስበው ወደፊት መሬት በኪራይ ወሳጅ ሃገራት ከኢትዮጵያ ጋር የጸብ ማንሻ ምክንያት ቢሆናቸውስ? የሚል ነበር። ይህንን ስጋቴን ግን በማስረጃ ለማስደገፍ አለመግባባቱ እስኪፈጠር መጠበቅ አለብኝ ማለት ነው? ብዬ ያሰብኩበት ጊዜ ነበር።ዛሬ አቶ ዳን ኤል ይህንን ስጋት አጠናክረውልኛል። 

የዛሬው የመሬት ኪራይም ሆነ ሽያጭ ነገ ከገዢውም ሆነ ከተከራዩ ሃገር ጋር እስከወታደራዊ ግጭት ድረስ የማድረስ እድል እንዳላቸው የሚያመላክት ሁኔታ መኖሩን ለመረዳት አቶ ዳንኤል በኢትዮጵያ እና በተከራይ የውጭ ኩባንያዎች መካከል የተደረጉትን ውሎች ባህሪ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል።

''የኢንቨስትመንት ኮንትራቶች ሲፈረሙ የኢንቨስትመንቱን መብቶች የሚያስጠብቁ ብዙ ነገሮች አሉ።''ባይላተራል ኢንቨስትመንት ፕሮተክሽን ትሪቲስ''  መንግስት  ከህንድ ከቻይና ከግብጽ ጋር ሁሉ ተፈራርሟል።በሌላ በኩል የ 1966ቱን የ ዋሽግተኑን ''ስቴት ኢንቨስተር ዲስፕዩት'' ይህ መንግስት ተፈራርሟል። እነኚህ ውሎች ምን ያመጣሉ? እነኚህ ሁሉ ነገሮች ሲደመሩ ስትል መሬታችንን በኮንትራት እየገዙ ያሉ ሰዎች መሬቱን ይይዙና የሚዳኙት ግን በ አለም አቀፍ ህግ ነው።በ አለም አቀፍ የግልግል ፍርድቤት ነው የሚዳኙት ከመንግስት ጋር ሙግት ቢገጥሙ በመሬቱ ዙርያ ማለት ነው።ይህንን ለማጠናከር ደግሞ ምን ታውጆላቸውል? ''ፕሮክላሜሽን ሰርቲ ሰቨን''የሚባል በ1996 በ አዋጅ ታውጆላቸዋል።ይህ ህግ ደግሞ ህዝቡን እያፈናቀሉ መሬቱን ከገዙ ባለሃብቶች ጋር ክርክር ቢነሳ ጉዳዩ በ አለም አቀፍ የግልግል ፍርድቤት እንዲታይ መንግስት ህግ አውጥቶላቸዋል።ይህ ሌላ አስገዳጅ ህግ ያግዘዋል የ 1958 ''ኒዎርክ ኮንቨንሽንን'' ፈርሟል።እነኚህን ነገሮች ዘርዝረህ ስትመለከታቸው አንድ ኢትዮጵያዊ ገበሬ በማንኛውም ጊዜ ሊነቀል የሚችል ነው።ምንም አይነት መብት የለውም።መሬታችንን የሚገዛው ባዕድ ግን ከእኛ በላይ መብት አለው።ይህንን መብቱን በ አለም አቀፍ ደረጃ ማስከበር የሚችል ነው።እየሆነ ያለው ነገር ዜግነታችንን ተቀምተናል።ከመቀሌ እስከ ሞያሌ ዜግነታችን ተገፏል።መሬት ላራሹ ተገቶ የቻይና ፊውዳሊዝም እየሰፈነ እኮ ነው።''ብለዋል።

የ አሰብ የቁራሽ መሬት ሽያጭ መዘዝ እስከ አሁን ድረስ የሃገራችን ችግር አንዱ ምንጭ እንደሆነ እንደቀጠለ ሁሉ የዛሬው የመንግስት የመሬት ኪራይ እና ሽያጭ ጉዳይ ካሁኑ እልባት ካላገኘ ብዙ ችግር ማስከተሉ እንደማይቀር አመላካች ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የተደቀነ አደጋ ነው።። ይህ ጉዳያችን ካልሆነ ምን ጉዳያችን ሊሆን ይችላል?


አበቃሁ 

ጌታቸው 

ኦስሎ

                              ESAT Yehud weg 14 April 2013


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...