ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, April 25, 2013

የግብፅ የኒኩለር ማብላያ ግንባታ፣ሩስያ፣ምዕራባውያን እና ኢትዮጵያ



ግብፅ እና ሩስያ ወዳጅነታቸውን እያጠናከሩ ነው። የግብፁ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሞሪስ እና የሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ሞስኮ ላይ ባደረጉት ውይይት በአለመቀፋዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ተስማምተዋል።ግብፅ ከአለመአቀፉ የገንዘብ ድርጅት የ 4.8 ቢልዮን ዶላር ብድር ለማግኘት በንግግር ላይ መሆኗ ይታወቃል።

April 19, 2013. Russian President Vladimir Putin, second right, before the news conference on the results of his meeting with the President of Egypt Mohamed Morsi, third left, in Sochi.(RIA Novosti / Mikhail Klimentyev) (photo from rt.com)

ባለፈው ሳምንት የግብፁ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሞሪስ ጉብኝት ውስጥ ጎልቶ የወጣው ጉዳይ ግብፅ እ.ኤ.አቆጣጠር በ1986 ዓም አቁሜዋለሁ ያለችውን የኒኩለር ማብላያ ግንባታ በ 2011 ዓም ፕሬዝዳንት ሙባረክ ጉዳዩን እንደገና ቀስቅሰው ለዓለም አቀፍ ጨረታ አቅርበውት የነበረ እና ለጊዜው ወሬው ጠፍቶ የነበረውን ጉዳይ ሩስያ ልታንቀሳቅሰው የመሆኑ ጉዳይ ነው።



የሩስያው የኃይል ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ ጉዳዩን አስመልክተው ሲናገሩ ግብፅ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ውይይት ለማድረግ ልዑክ እንደምትልክ እና እንደርሳቸው አገላለፅ ''----cooperation in peaceful nuclear projects to jointly construct new nuclear power plants'' ''ለሰላማዊ ተግባር የሚውል በጋራ የሚገነባ የኒኩለር ኃይል ጣብያ ግንባታ'' እንደሚሰራ እና  2025 እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።ፕሬዝዳንት ፑቲን በበኩላቸው ግብፅ የተፈጥሮ ጋዝ ያላት ሀገር በመሆኗ በመጪው ሐምሌ ሞስኮ ላይ በሚደረገው የተፈጥሮ ጋዝ አምራቾች ጉባኤ ላይ የግብፁ ፕሬዝዳንት ወይንም ወኪላቸው እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል።

የግብፅ እና የሩስያ ወዳጅነት ታሪካዊ ፋይዳው በቀላሉ የሚታይ አይደለምበአብድል ናስር ዘመን ግብፅ የ አስዋን ግድብን ባለቤትነት እንድታረጋግጥ ከፍተኛ ድጋፍ ያደረገችው የቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት የአሁኗ ሩስያ መሆኗ አይዘነጋም።
ምዕራባውያን የኒኩለር ኃይል ባለቤትነት ጉዳይን በቀላሉ የሚመለከቱት ጉዳይ አይሆንም የሩስያ ናዋን እና የኃይል ሚዛኗን በመካከለኛው ምስራቅ  ለማስጠበቅ ደግሞ ግብፅን መያዝ ብቸኛው አማራጭ መንገዷ ይሆናል።የአባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር በእጅጉ የምያነታርካት ግብፅ የምትቀርፀው የውጭ ፖሊሲ ከኢትዮጵያ ጋር በተቃራኒ መልክ መያዙ የማይቀር መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ይሆናል። 
April 19, 2013. Russian President Vladimir Putin, right, before the news conference on the results of his meeting with the President of Egypt Mohamed Morsi in Sochi.(RIA Novosti / Mikhail Klimentyev)(photo rt.com)
ይህ ጉዳይ ምዕራባውያን ኢትዮጵያ ጠንካራ እና የህዝቡን ስሜት የሚያዳምጥ መንግስት እንዲኖር የመፈለጋቸውን ፋይዳ (ከጥቅማቸው አንፃር) ግለቱን ጨምርባቸው ይሆናል ብሎ ማሰብም ሞኝነት አይደለም።ግብፅ ከአሜሪካ እጅ የምታፈተልክበት አይነተኛ አጋጣሚ ካለ ግብፅ ላይ ተፅኖ ለመፍጠር ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያት ትሆናለች ማለት ነው።ኢትዮጵያ ደግሞ አሁን ባለው መንግስቷ በሀገር ውስጥ በቂ ድጋፍ ካለማግኘቱ አንፃር የኢትዮጵያን አንድነት የጠበቀ ጠንካራ መንግስት የመመስረትን ሂደት ጊዜ የሚሰጠው ላይሆን ይችላል።እዚህ ላይ ግን ልብ ማለት የሚገባው ውጫዊ ተፅኖዎች ከውስጣዊው ወሳኝ ጉዳይ አንፃር ሲታይ የወሳኘነት ሳይሆን ከባድ ተፅኖ የመፍጠር አቅም ብቻ እንደሚኖራቸው ነው።በእርግጥ የሀገራችን ጉዳይ ወሳኞቹ እኛ አና እኛ ብቻ እንጂ ምዕራባውያን እንዳልሆኑ መዘንጋት የለብንም ።የግብፅን የሰሞኑን  አካሂያድ  ግን ልብ ያለ ልብ ሊለው ይገባል።

አበቃሁ 
ጌታቸው 
ኦስሎ
Sources - rt.com
               -Router

2 comments:

Anonymous said...

areb limadu new guar.

Samrawit said...

Egypt is becoming one of dangerous wild nation. Democracy has already sent to garbage. US aid for decades has became useless. New extremists who are expected to poisoned even the horn of Africa has secede power. Shame to US aid.

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...