ቀደም ብለው እንደ አማልጋሜትድ ኩባንያ፣በያዝነው አመት ብቻ ደግሞ
-የ አዋሽ ባንክ ስራ አስኪያጅ ሰው ገጭተዋል አልገጨሁም ንትርክ ፣
-የ ሆላንድ ካር ኩባንያ ተጨማሪ ብድር ድጋፍ በመፈለግ ብቻ ለኪሳራ ተዳርጎ ኩባንያው ከስራ ውጭ መሆኑን፣
- የ አክሰስ ባንክ መስራች እና ኢንቨስተር አቶ አመልጋ ተመሳሳይ መሰል ችግር ገጥሟቸው ነገር ግን ተመልሰው የገጠማቸውን ችግር እንደሚቋቋሙ መግለጻቸው፣
- ሚያዝያ 9 ቀን 2005 ዓ.ም. የ አያት አክስዮን ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አያሌው እና ሌሎች ባልደረቦቻቸው ከቀረጥ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ቀርበው አቃቢ ህግ የሰባ አመቱን አዛውንት'' ከ ሰባ አመት በላይ እስር ይፈረድልኝ፣ያላቸው መኪናዎች ሁሉ ይወረሱ'' የሚል ጥያቄ አቅርቧል። በነገራችን ላይ አቶ አያሌው ለ አባይ ግድብ የ አንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ብር ቦንድ መግዛታቸው ከግንዛቤ ውስጥ መግባት እንደነበረበት ለፍርድ ቤቱ አሳስበዋል።ፍርድ ቤቱ ግን አልሰማም ፍርዱ ለ ሚያዝያ 29 ተቀጥሯል።
ከሪፖርተር ዕሁድ ሚያዝያ 13/2005 ዓም ስለ ፍርድቤት ውሎው የተነበበው ዘገባ ውስጥ እንዲህ የሚል ይገኘበታል።
''አቶ አያሌው ዕድሜያቸው 70 ዓመት መሆኑን፣ ከ15 ዓመታት በላይ በተለያዩ ሕመሞች ማለትም የልብ ቀዶ ሕክምና እንደተደረገላቸው፣ የደም ግፊት፣ የጀርባ ሰረሰር ጉብጠትና የነርቭ ሕመምተኛ መሆናቸውንና ሌሎችንም በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲመለከትላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፀባያቸው መልካም መሆኑን የሚኖሩበት ክፍለ ከተማ ወረዳ ጽሕፈት ቤት በደብዳቤ ማረጋገጡን፣ የ15 ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን፣ ባለቤታቸው የልብና የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን፣ እህታቸው የዓይን ግርዶሽ ታማሚ መሆናቸውንና እርሳቸው እየረዷቸው እንደሚኖሩም አስረድተዋል፡፡
በትምህርት ዘርፍ ከ1974 ዓ.ም. ጀምሮ በግል ተልዕኮ (ርቀት) ትምህርት በመሰማራት ለበርካታ ወገኖች የላቀ ጠቀሜታ ማስገኘታቸውን፣ በሪል ስቴት ልማት ፋና ወጊ መሆናቸውንና የቤት እጥረትን ለማስወገድ የላቀ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን በመዘርዘር፣ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከትላቸው በቅጣት ማቅለያ ሐሳባቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ አያት አክሲዮን ማኅበር 2,468 ቋሚ ሠራተኞችና ጥቃቅን ድርጅቶች በሥሩ እንዳሉ፣ ማኅበሩ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ከ310 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት ገቢ ማድረጉን፣ ለዚህም አስተዋጽኦ እሳቸው ሥራ አስኪያጅ ሆነው በሚሠሩበት ጊዜ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ይኼንንም በማቅለያነት እንዲመለከትላቸው ጠይቀዋል፡፡
የውጭ አገር ቤት ገዥዎችን በማፈላለግ በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ሰዎች በውጭ ምንዛሪ እንዲገዙ በማድረግ በድምሩ ከ145 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ እንዲገባ ማድረጋቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ትምህርት ቤቶችን በመሥራት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን፣ የጤና ጣቢያዎችን ከሐኪሞች መኖሪያ ጋር ሠርተው ማስረከባቸውን፣ የገበሬ ማሠልጠኛ ገንብተው ማስረከባቸውን፣ የአትሌቲክስ ስፖርትን ለማጠናከር አሠልጣኝ መቅጠራቸውን በዝርዝር በመግለጽ ባደረጉት አስተዋጽኦ መሠረት ፍርድ ቤቱ በማቅለያነት እንዲወስድላቸው አመልክተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የወጣቶች ማዕከል መገንባታቸውን፣ በትግራይ ‹‹ከዳስ ወደ ክላስ›› በተሰኘ መፈክር በመማር ማስተማሩ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን፣ በ1998 ዓ.ም. በድሬዳዋ ለደረሰው የጐርፍ አደጋ አንድ ባለአንድ ፎቅ ሕንፃ ገንብተው ማስረከባቸውን፣ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከበር ከፍተኛ ወጪና ቁሳቁስ በማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን፣ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርጅቱ የ340 ሺሕ ብር ስጦታና የ980 ሺሕ ብር ቦንድ ግዢ፣ አቶ አያሌው የ100 ሺሕ ብር ስጦታና የ200 ሺሕ ብር የቦንድ ግዢ መፈጸማቸውንና ለአገራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ማስረጃ በማያያዝ ለፍርድ ቤቱ አቅርበው፣ በማቅለያነት እንዲወስድላቸው ጠይቀዋል፡፡ እንዲሁም ለኢሕአዴግ በተለያዩ ጊዜያት ለተከናወኑ ፕሮግራሞች አቶ አያሌው አንድ ሚሊዮን ብር መስጠታቸውንና በማረሚያ ቤት ቆይታቸውም ባላቸው መልካም ፀባይ የተለያዩ የምሥጋና ደብዳቤዎች እንደደረሳቸው በማስረዳት፣ ፍርድ ቤቱ ሁሉንም የቅጣት ማቅለያ ጥያቄዎችንና ማስረጃዎቻቸውን በመመልከት ዝቅተኛ ቅጣት እንዲወስንላቸው ጠይቀዋል፡፡ ''
ኢትዮጵያ ''አይከን'' የሆኑ ሃገር በቀል መዋለ ንዋይ አፍሳሽ ባለ ሃብቶችዋን በተለያየ ምክንያት ማጣቷን ቀጥላለች።

No comments:
Post a Comment