ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, April 25, 2013

ሮም ለግራዝያኒ ሐውልት የተሰጠው ገንዘብ ታገደ!

የ ፋሺሺት ግራዝያኒ ሃውልት በ ኢጣልያ የመገንባቱን ሂደት አዲስ አበባ በመቃወም ሰልፍ የወጡትን ፖሊስ በመደብደብ እና ወደ እስር ቤት በመውሰድ የተንገላቱበት ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግስት የሃገሪቱን አንኳር ብሄራዊ እና ሉአላዊነት ጉዳዮች ላይ ተቆርቋሪነት ባለማሳየት  ያስመሰከረበት አንዱ ማሳያ ሆኖ አልፏል።ኢጣልያ ግን የሃውልቱ መስርያ ገንዘብ ማገዷን እየተናገረች ነው።ለኢትዮጵያ የጮሃችሁ ለእውነት የቆማችሁ ፍሬው የመታየቱ አንዱ ማሳያ ነው።
ይህ ዜና ከ ጀርመን ድምጽ ራድዮ የሚያዝያ 23/2013 እ ኤ አቆጣጠር አማርኛው አገልግሎት ድህረ ገጽ ላይ  የተገኘ ነው።እንዲህ ይላል።


''ሮም ለግራዝያኒ ሐውልት የተሰጠው ገንዘብ ታገደ

ለኢጣልያው ፋሺስት ጀነራል ግራዝያኒ መታሰቢያ ሐውልት መሥሪያ የተመደበው ገንዘብ ትናንት እንዲታገድ መደረጉን የኢጣልያ ባለሥልጣናት አስታወቁ ። ሐውልቱ የተሰራበት አፊሌ  የተባለችው የግራዝያኒ የትውልድ ከተማ የሚገኝበት የላዝዮ ግዛት ባለሥልጣናት  ገንዘቡን የሰጠነው ተጭብረብረን ነው ሲሉ አስታውቀዋል ። የላዝዮ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ዚንጋሬቲ  የአፊሌ ባለሥልጣናት የገንዘብ እርዳታ የጠየቁት ለመናፈሻ ግንባታና  ላልታወቀ ወታደር  ሐውልት መሥሪያ  እንጂ ለአወዛጋቢው ጀነራል ለግራዝያኒ ሐውልት መሥሪያ እንዳልነበር ተናግረዋል  ።  የላዝዮ ግዛት ለእርዳታ የመደበው 180 ሺህ ዩሮ ወይም 235 ሺህ ዶላር ለግራዝያኒ እስካሁን የተገነቡት መታሰቢያዎች ከአካባቢው እስኪነሱ ድረስ እንደማይሰጥ አስታውቋል ።  ጀነራል ግራዝያኒ በኢጣልያ ወረራ ወቅት በኢትዮጵያ የኬሚካል የጦር መሣሪያዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉና በርካታ ሠላማዊ ሰዎችም እንዲጨፈፈጨፉ  ትዕዛዝ ያስተላለፈ ፣ጨፍጫፊው የሚል ቅፅል የተሰጠው የጦር አዛዥ ነበር  ። የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበርና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን  ለፋሽሽቱ ግራዝያኒ ሐውልት መቆሙን በማውገዝ ጠንካራ ተቃውሞ ሲያስሙ ቆይተዋል ። ፋሺስት ኢጣልያ ከተሸነፈች በኋላ ግራዝያኒ ለፈፀማቸው የጦር ወንጀሎች በወታደራዊ ፍርድ ቤት 19 ዓመት ቢፈረድበትም 2 አመት ብቻ ታስሮ በነፃ ተለቋል ።''

Source-http://www.dw.de/ይዘት/ዜና/s-11648

No comments: