ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, April 20, 2013

ኢህአዲግ የአባይን ግድብ የቦንድ ሽያጭ በባህር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መተንኮሻ አድርጎታል።

ዛሬ እነሆ በኖርዌይ እንዲህ ሆነ

ከኖርዌይ ከተሞች ውስጥ በደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ስታቫንገር ከተማ ዛሬ ሚያዝያ 12/2005 ዓም በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር / መብራት በተገኙበት ለአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ የተዘጋጀው ዝግጅት ከኦስሎ ስምንት ሰዓታት በላይ በአውቶቡስ ተጉዘው በስብሰባው በተገኙ ኢትዮጵያውያን በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱ ተሰርዞ አምባሳደሯ በፖሊስ ቦታውን ለቀው  እንዲሄዱ ተመክረው አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል።

በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይ በሥርዓት ተቀምጠው የተገኙት ኢትዮጵያውያን መርሃግብሩ ከመጀመሩ በፊት ''በዘመነ ኢህአዲግ የተገድሉትን ኢትዮጵያውያን በቅድሚያ በህሊና ፀሎት እናስብ ይህንንም ለማድረግ ሁላችንም ከተቀመጥንበት እንነሳ'' በማለት አምባሳደሯም እንዲነሱ እና አብረው በፀሎት እንዲያስቡ ይጠይቃሉ።አምባሳደሯም ሆኑ አብረዋቸው የመጡት ፈቃደኛ አልሆኑም። በመቀጠል ኢትዮጵያውያኑ እንግዲያው ስለ አባይግድብ አሁን ልንነጋገር አንችልም በማለት ያስታውቃሉ።በእዚህ መሃል ከፍተኛ የተቃውሞ ድምፅ መሰማት ይጀምራል። 
''ከአባይ በፊት ሰብአዊ መብት ጥሰት ይገደብ!''
''የሙስሊሙ ድምፅ ይሰማ!''
''የኢትዮጵያውያን ድምፅ ይሰማ!''
''የዘር መድሎ ይቁም!'' (stop apartheid in Ethiopia!'' ወዘተ የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት ላይ ሳሉ የኖርዌይ ፖሊስ ሁኔታውን ለማረጋጋት ሁሉም እንዲቀመጡ ይነገራቸዋል። በእዚህን ጊዜ ግን ኢትዮጵያውያኑ የኮኮብ ምልክት ያለበትን ከአምባሳደሯ ጀርባ ባለው ግድግዳ ላይ የተለጠፈውን ባንዲራ የኢህአዲግ አርማ ኮኮብ በሌለበት ኢትዮጵያ ባንዲራ ሸፍነው ጨርሰው ነበር።
ፖሊሱ ኢትዮጵያውያንን ካስቀመጠ በኃላ ቀጥሎም ሁኔታው ደህና መሆኑን ለማስረዳት ይሞክራል።በእዚህ መሃል ኢትዮጵያውያኑ ይብሱን  ቁጣቸውን በዜማ ይቀጥላሉ።

''ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም 
 እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም የደፈረሽ ይውደም''

ይህን የተመለከቱት ፖሊሶች ኢትዮጵያውያኑን ከማስወጣት አምባሳደሯን ማስወጣት ትክክለኛ እርምጃ እንደሆነ ስለተረዱ አንዱ ፖሊስ ወደ አምባሳደሯ ቀርቦ አዳራሹን ለቀው እንዲወጡ በቃልም በእጁም መውጣት እንዴት እንደሆነ እያሳየ ይነገራቸውል። አምባሳደር መብራት ቦርሳቸውን አንስተው ወደ አዳራሹ ዘወር እያሉ እየተመለከቱ ወደ በሩ አዘገሙ። ኢትዮጵያውያኑ ቀጠሉ።

''ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም 
 እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም የደፈረሽ ይውደም'''
''ሌባ ሌባ አለ ገና አለ ገና!'' አምባሳደሯ ፈጠን ባለ እርምጃ በፖሊስ ታጅበው ወደ መኪናቸው ሄዱ።








ኢህአዲግ የአባይን ግድብ የቦንድ ሽያጭ በባህር ማዶ የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያንን መተንኮሻ አድርጎታል።

ማንም ኢትዮጵያዊ አባይ ቢገደብ ኢትዮጵያ ከድህነት ብትወጣ አይጠላም።ዛሬም  ተቃውሟቸውን የገለፁት ኢትይጵያውያን ለኢትዮጵያ ሞት የሚመኙ ሆነው አይድለም።ኢህአዲግ ግን በውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ያሳጣ እየመሰለው ብዙ ተቃዋሚ አለ ብሎ የሚያስበበት ቦታ ሁሉ አባይ ግድብ ቦንድን ካርድ እየመዘዘ የልዩነት መስመር በኢትዮጵያውያን መሃከል ይፈጠራል ብሎ ያስባል። ለእዚህም አይነተኛ ማስረጃው የመጀመርያው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ዝግጅት በዋሽግተን ዲሲ  ሲዘጋጅ ብዙ ኢትዮጵያውያን ካርድ ወስደው አክትቪስት ታማኝ በየነን ጨምሮ ወደ ስብሰባው ቦታ ሲሄዱ ''የእንጀራ ልጅ እና የቤት ልጅ'' በሚል መለያ አድርጎት ''አንተ አትገባም አንተ ግባ'' እያለ መለየት ጀመረ። 
''በሀገራችን ጉዳይ ያለንን ሃሳብ መስጠት እንፈልጋለን ካርድ ይዘናል'' ያሉ ታማኝንም ጨምሮ  እንዳይገቡ ተከለከሉ። 

በወቅቱ የሚገቡት ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት ሃሳብ ቢኖራቸው ሃሳባቸውን መስማት እና ምላሽ መስጠት ያን ቀን መግባባት ባይቻል ለቀጣይ ሌላ ስብሰባ አድርጎ መመካከር የጤነኛ መንግስት ልዑክ አሰራር ነበር።ኢህአዲግ ግን ከመጀመርያው የአባይ ግድብን ሲያነሳ በባህርማዶ ያለው ሕዝብ ሲቃወም በሀገር በት ያለው መደገፉ ስለማይቀር ይለያያል። በውጭ ያለውም ብሔራዊ ስሜቱ አይሎ እርስ በርሱ ይከራከራርል የሚል ታሳቢ ያደርገ አቀራረብ ስለነበረው በዋሽግተኑ ስብስባ ላይ እራሱ ኤምባሲው በድብዳቤ የጠራቸውን ሁሉ ተምታተውበት አላስገባም አለ።ኢትዮጵያውያን በገዛ የሀገራቸው ጉዳይ ባይተዋር ሆኑ።


በእንደዚህ አይነት የተጀመረው አባይ ጉዳይ ይሄው ኢህአዲግ እስካሁን ድረስ እንደማስይሳካ እያወቀ በባህር ማዶ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች እና የሀገራቸው ጉዳይ የእግር እሳት የሆነባቸውን ኢትዮጵያውይንን መተንኮሻ አድርጎ ይጠቀምበታል።በነገራችን ላይ ይሄው ተመሳሳይ መርሃግብር በኦስሎ አፕሪል 23/2013 መርሃግብር መያዙን ከአምባሲው ድህረገፅ ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያ ያስነብባል። ሃገራዊ ህብረት ሳይፈጠር፣ዜጎች ከአንድ ክልል ወደ አንድክልል ካልፈቃድ ለምን ገባችሁ ተብለው እየታሰሩ(የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ቤንሻንጉል ክልል ለመታሰር ያበቃቸው) በሺዎች መሬት እና ንብረታቸውን ተነጥቀው ሲንከራተቱ አንዳች ያልተናገረው መንግስት ይህም ከፍተኛ ተቃውሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በፈጠረበት በእዚህ ጊዜ ስለ አባይ ግድብ ቦንድ ግዙ ብሎ መጠየቅን ምን ስም እንስጠው?

ጉዳያችን Gudayachn


2 comments:

Anonymous said...

very fantastic view.

Anonymous said...

ከፍተኛ ተቃውሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በፈጠረበት በእዚህ ጊዜ ስለ አባይ ግድብ ቦንድ ግዙ ብሎ መጠየቅን ምን ስም እንስጠው?
perfect saying!

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...