ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, November 21, 2016

¨የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስትን ይመሩ ከነበሩ መካከል 5 አዛዦች በአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ተገደሉ።¨ የአግ7 ራድዮ Five state of emergency command post commanders are killed

ፎቶ አርበኞች ግንቦት 7 ድረ-ገፅ 


ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊቱን ወደ ኢትዮጵያ ማስገባቱን እና ገዢ መሬቶችን መቆጣጠሩን እየገለፀ ነው።የድርጅቱ ራድዮ ይህንኑ አስመልክቶ በፎቶ ግራፍ የተደገፈ ዘገባ አቅርቧል። የራድዮው ሙሉ ዘገባ ከእዚህ በታች እንዳለ ቀርቧል።
==================================
November 20, 2016
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
===========================
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ህዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም በቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይነብሪ በተባለው ቦታ ከመቀሌ የተላከ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይል ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ድል ተጐናፅፏል።

ይህ ከመቀሌ የተንቀሳቀሰው የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል ዋና ተልዕኮ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊትን እንቅስቃሴ ለመግታት ታስቦ ሲሆን እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በ56 መኪኖች አጓጉዞ በቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይነብሪ በተባለ ቦታ ቢያሰፍርም ለሀገራቸውና ህዝባቸው ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለመክፈል የማይሰስቱት የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በከፈቱት ድንገተኛ ማጥቃት 92 በመግደልና 65 በማቁሰል አንፀባራቂ ድል ማስመዝገባቸውን ከስፍራው የሚገኘው አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ባደረሰን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።
ፎቶ አርበኞች ግንቦት 7 ድረ-ገፅ 

ይህ በእንዲህ እንዳለም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እንቅስቃሴን ለመግታት የተንቀሳቀሰውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስትን ይመሩ ከነበሩ መካከል 5 አዛዦች የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል መቶ አለቃ ጣዕመ የሚባል እንደሚገኝበትም ታውቋል።

በተያያዘ ዜና የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ህዳር 8 ቀን 2009 ዓ.ም በቃፍቲያ ሁመራ ሩዋሳ አካባቢ ማይጐነጥ ልዩ ስሙ ማይቆማ በተባለው ቦታ ሰፍሮ ከሚገኘው የ24ኛ ክፍለ ጦር ጋር ባደረገው ውጊያ አንድ ብርጌድ ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ከማውደሙም በተጨማሪ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን ከስፍራው የደረሰን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን መረጃ ያመለክታል።

በዚሁ አካባቢ በተደረገው ውጊያ የወያኔው የ24ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጀግኖች የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ተስኖት እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።

በእለቱ በተደረገው ውጊያ 120 የወያኔ መከላከያ ሰራዊትን በመግደልና 80 በማቁሰል በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ከባድና ቀላል ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረካቸውንም ሪፖርተራችን ገልጿል።

በውጊያው እለት የቆሰሉ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ብዛት ቁጥር ስፍር የሌለው ከመሆኑ የተነሳ ሁመራ የሚገኘው ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁንና ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸውን ደግሞ ወደ ጐንደር ሆስፒታል በመላክ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ሰራዊት ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት ርምጃ የአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ እጅጉን ከመደሰቱም በተጨማሪ ከትግሉ ጐን ለመሰለፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት እየገለፁ እንደሚገኙም ታውቋል።

የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናትም በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን አገዛዙን ለመፋለም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጋር እንዳይገናኙ አካባቢውን በመውረር ህብረተሰቡ ከቤቱ ወጥቶ እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ ስራ ላይ ተጠምደው የሚገኙ ሲሆን፤የሞቱ የሰራዊቱ አባሎቻቸውንም ህዝቡ እንዳያይባቸው የራሳቸውን ሰዎች በመመልመል እንዲቀበሩ እያደረጉ መሆናቸውን ሪፖርተራችን አክሎ ገልጿል።

በደረሰባቸው የሰው ህይወትና የንብረት ኪሳራ እጅጉን የተደናገጡት የህወሀት አገዛዝ ባለስልጣናትም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይልና በ24ኛ ክፍለ ጦር ላይ ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የሚሰነዘረው ጥቃት ተጠናክሮ በመቀጠሉና ፋታ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ በአካባቢው የጦር ሄሊኮፕተሮችን በማሰማራት አሰሳና ቅኝት ሲያደርጉ እንደነበረ ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እስከአሁን ባደረጋቸው ውጊያዎችና ባስመዘገባቸው ድሎች በመደሰት በአካባቢው የሚገኙ የሚሊሸያ ታጣቂ ሀይሎች ከወንድሞቻችን ጋር ውጊያ አናደርግም በማለት በአገዛዙ ላይ እንዳመጹና ብዛት ያላቸው የሚሊሸያ አባላትም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጋር መሰለፋቸውን ከስፍራው የደረሰን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን መረጃ ያስረዳል።

ምንጭ - http://www.patriotg7.org/?p=1157 

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።