ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, December 7, 2021

የትግራይ ሕዝብ ከውስጡ የበቀለውን እና የቆሰለውን ከአውሬ የከፋ፣ የህወሓት ቡድን እንደጀርመን እና የጣልያን ሕዝብ አንቆ በፍጥነት ለሕግ ማቅረብ ወይንም እራሱ እና ልጆቹ በአውሬው መርዝ እስኪጠፋ ቡድኑን በአንቀልባ ማዘል፣ የቀረቡለት ሁለት ብቸኛ አማራጮች ናቸው።


  • ህወሓት እና ጀሌው በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት ሁሉ አውሬ በራሱ ወገን ላይ አልፈፀመውም።
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግስት አሁንም መለሳለስ የለባቸውም። ለትውልድ አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰድ አለባቸው!

ከትግራይ የተነሱ የዘረኝነት እና የፀረ-ሰው ቡድኖች የጥፋት ትርክት፣ፖለቲካ እና ሴራ ኢትዮጵያን ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በላይ ወደ ኃላ እንድትቀር ያደረጋት የጥፋት ሥራ ነው።ለህወሓት ፈፅሞ የመለሳለስ እና የመዘናጋት ስሜት ማሳየት አይገባም።የተፈፀመውን በቀለም ብዛት ቢፃፍ የሚበቃ አይደለም።የክፋት እና የተንኮል ዓይነቱ ተዘርዝሮ አያልቅም።የሽብር ቡድኑ ግቡ ኢትዮጵያን ማጥፋት ነበር።ሕዝቧን መበተን ነበር።የትግራይ ሕዝብ ወገቡንና ጅራቱ የተቆረጠው የህወሓት ጭንቅላትን ይዞ ለመንግስት ማስረከብ ወይንም በአንቀልባ እንዳዘለው በህወሓት መርዝ የበለጠ መቀጠፍ ከፊቱ ያሉት ሁለቱ ብቸኛ ምርጫዎች ናቸው።

ለህወሓት ጀሌ፣የቅርብ እና የሩቅ ድጋፍ ሰጪው ሁሉ ሽብርተኛ የሚለው ቃል ያንሰዋል።የሽብር ጅምላው ቦታ እና ጊዜ ይመርጣል።ህወሓት እና የተባበሩት ከትግራይ የተነሱ ጀሌዎቹ አውሬያዊ ተግባር ለመግለጥ አንደበት ይተናነቃል።ቃላት ያንሳል።ምክንያቱም ድርጊቶቹ ቀድሞም በሰው ሃሳብ ውስጥ አልተፈጠሩም።ድርጊቱን የሚገልጠው ድርጊቱን ሁሉ አውሬ በራሱ ወገን ላይ አልፈፀሜውም።ወደፊትም አይፈፅመውም የሚለው አባባል ይሻላል።

የዱር አውሬ በራሱ ተመሳሳይ አውሬ ላይ በማሰቃየት ግድያ አይፈፅምም። ህወሓት አማራ እና አፋር በመሆናቸው ብቻ ንፁሃንን ገድሏል።አውሬ የራሱን ተመሳሳይ አውሬ ገድሎ አይፎክርም። ህወሓት ቀኝ እና ግራቸውን ያልለዩትን ገድሎ ይፎክራል።አውሬ የራሱ ወገን የሆኑ ግልገል አውሬዎችን አይደፍርም።ህወሓት ሕፃናትን ደፍሯል።በየደረሰበት ልጃገረዶች በወላጆቻቸው ፊት ተደፍረዋል።ሚስት በባሏ ፊት ተደፍራለች።አውሬ ግን አይደለም ሊደፍር ይልቁንም ከሌላ ጥቃት ይጠብቃቸዋል።አውሬ የራሱ የሆነ አውሬ ምግብ ለመንጠቅ ሞክሮ ምግቡን ከወሰደ በኃላ ምግቡን በልቶ አይገድልም።ህወሓት በገባባቸው የአማራ እና አፋር ክልሎች ገበሬው ምግብ እንዲያመጣ አስገድዶት ከበላ በኃላ በጥይት ይገድለዋል።

ይህ ብቻ አይደለም፣ነጋዴው ገንዘብ እንዲያመጣ ከጠየቀ በኃላ ገንዘብ ተቀብሎ በአደባባይ ገድሏል።ዛሬ በባቲ ከተማ የተፈፀመውን ግፍ ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ቀርበው የተናገሩ የዓይን ምስክር እና ባለቤታቸው ያሉት ይሄንኑ ነው። አቶ ያሲን የተባሉ የከተማው ነጋዴ ''ገንዘብ አምጡ አሏቸው ሰጡ።በቀጣዩ ቀን ገንዘብ ጨምሩ ካልሆነ እንገድልዎታለን አሏቸው።ይተዉኛል ብለው ጨምሩ።ወድያው ገንዘቡን ከወሰዱ በኃላ ሱቃቸው ውስጥ ያለውን ብስኩት ሳይቀር በሙሉ ከዘረፉ በኃላ ሱቃቸው ፊት ለፊት አንበርክከው በግንባራቸው ተኩሰው ገደሏቸው።'' ይህንን የተናገሩት ባለቤታቸው እያለቀሱ ነበር። አውሬ አይነስውር ወገኑን አሰቃይቶ አይገድልም። የህወሓት የሽብር ቡድን በከተሞች ውስጥ በልመና የተሰማሩ ዓይነ ስውሮች ምንም ሳያደርጉት ገድሏቸዋል።አውሬ ግልገል ወገኖቹን ባሉበት ደርሶ አይፈጃቸውም።ህወሓት በአፋር ብቻ በአንድ ቀን በአንድ መጠለያ ጣብያ ገብቶ ከሁለት መቶ በላይ ሕፃናት ፈጅቷል።

አሁን ህወሓት በሁሉም አቅጣጫ ተመቷል።በገር ግን ገና አልሞተም።ወገቡ እና ጅራቱ ተጎምዷል።ጭንቅላቱ ግን ገና አለ።ይህ ማለት ዋናው የአውሬነት መርዙ የሚገኝበት አካል አልጠፋም ማለት ነው።ስለሆነም አሁንም የምንዘናጋበት ጊዜ አይደለም።ኢትዮጵያ መልሳ ስትደማ ልትኖር አትችልም።ኢትዮጵያ መልሳ ለባዕዳን ገበያ ልትቀርብ አትችልም።መምረር አሁንም ያስፈልጋል።የተለያዩ ምክንያት እየሰጡ የህወሓትን መልክ ሊቀባቡ የሚፈልጉትን እና ሊያለሳልሱ የሚሞክሩ እስስቶችን ከአሁኑ ማስቆም ያስፈልጋል።የህወሓት እና ከትግራይ የተነሳው ጀሌ ተግባር ከአውሬ የከፋ ነው።መለሳለስ አያስፈልግም።የተፈፀመው ከቃላት እና ከህሊና በላይ ነው።የትግራይ ሕዝብ ከውስጡ የበቀለውን እና የቆሰለውን ከአውሬ የከፋ፣ የህወሓት ቡድን እንደጀርመን እና የጣልያን ሕዝብ አንቆ በፍጥነት ለሕግ ማቅረብ እና እራሱን ከአውሬው መርዝ መጠበቅ ብቸኛው አማራጩ መንገድ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግስት አሁንም መለሳለስ የለባቸውም። ለትውልድ አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰድ አለባቸው።ኢትዮጵያ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ልጆቿን በህወሓት እና የእርሱ ውላጅ በሆኑ ትርክቶች ምክንያት ሰውታለች።ልጆቿ የበለጠ በድህነት እንዲኖሩ ተገደዋል።ከሰሞኑ እንዳየነውም የኢትዮጵያን ህልውና ሊፈታተን አደጋ ጋርጦ አልፏል።አሁንም ግን መለሳለስ ፈፅሞ አይገባም። ህወሓት እና ቡድኑ አልተሳካለትም እንጂ የቻለውን ሁሉ አድርጎ ነበር።ቢሳካለት ኖሮ ምን ያደርግ እንደነበር የፊልሙን ቀዳሚ ክፍል በአማራ እና አፋር ክልሎች ባደረገው የጥፋት ወንጀል ሁሉ አሳይቶናል።ለእዚህ ነው ፈፅሞ ልንዘናጋለት የማይገባን፣ሽብርተኛ የሚለው ቃል የማይበቃው፣ከመጥፋት መልስ ምንም ሊተካው የማይችለው ነው የምንለው።

በእስካሁኑ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድንቅ ህብረቱን አሳይቶ የጥፋት ቡድኑን አሳፍሮታል።በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የጥፋት ቡድኑ ጀሌ በአፋር እና አማራ ክልል በመከላከያ፣የክልል ልዩ ኃይል እና ፋኖ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።ቡድኑ ተተራምሷል ብቻ ሳይሆን መሰረቱ ተናግቷል። የሚናገረው ጠፍቶበት ዘባርቆ አልቸረሰም።በአንድ በኩል ከራሱ ከትግራይ እናቶች የልጆቻችን ጉዳይ ጥያቄ ወጥሮታል። በሌላ በኩል ሽንፈቱ ደፍቆታል።ይህም ሆኖ ግን ጭንቅላቱ ገና አልተመታም።ኢትዮጵያ ደግሞ የሽብርተኛው ህወሓት ራስ ሳይጠፋ እረፍት አታገኝም። መዘናጋት የለም! የበለጠ ማምረር፣የተፈፀመው የበለጠ ሊያስቆጣን ይገባል።

===============/////===========


No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...