የውጭ ሃገር ጋዜጦች ያወጧቸው ጽሁፎች ቅድምያ ሰጥተን እናነባለን፣ለሌሎች እናካፍላለን።በራሳችን ሃገር የታተመ፣ስለየራሳችን ጉዳይ በእንግሊዝኛ የተፃፉ ፅሁፎች ለራሳችን አንብበን በትዊተር፣ፌስ ቡክ እና በሌሎች ማኅበራዊ ሚድያዎቻችን ብናካፍል የውጭው ዓለም በቀላሉ በሀገሩ ቋንቋ ኢትዮጵያ ምን እያለች እንደሆነ በቀላሉ ለማስተላለፍ እንችላለን። ይህ ብዙ ሃተታ አይፈልግም። በቀላሉ ወደ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በእንግሊዝኛ የሚያወጣቸውን ዜናዎች፣የምርምር ጽሁፎች፣ኢትዮጵያን በተመለክተ የሚቀርቡ ወቀሳዎች ላይ የተሰጡ ደረጃቸውን የጠበቁ ጽሁፎች እና ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ ጽሁፎች እናካፍል፣ገጹን 'ላይክ' እናድርግ።
1) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የእንግሊዝኛ ህትመት ገጽ መግቢያ = https://www.press.et/english/?
2) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የእንግሊዝኛ ህትመት የፌስ ቡክ ገጽ መግቢያ = https://www.facebook.com/
3) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የእንግሊዝኛ ህትመት ትዊተር ገጽ መግቢያ = @PressEthio
============/////=========
No comments:
Post a Comment