ዛሬ ታህሳስ 8/2014 ዓም የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ካውንስል በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርገው ስብሰባ አደገኛ ስብሰባ ነው።
ስብሰባው በግብጽ፣ዶ/ር ቴዎድሮስ እና በባይደን አስተዳደር ውስጥ ባሉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ግንባር በፈጠሩ ሁሉ ጉትጎታ የተሰራ ደባ ነው።
ነጥቦቹ
ስብሰባውን የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጻረር መሆኑን ገልጦ መግለጫ አውጥቷል።
በገለልተኛነቱ የተመሰከረለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንደማይስማማ ገልጧል።
የተመድ ሰብዓዊ መብት ካውንስል ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በመሆን በትግራይ ምርመራ አድርገው የዘር ማጥፋት አለመፈጸሙን በአንድ ቀን ማለትም እኣአ ጥቅምት 28/2021 ዓም በጄኔቭ እና አዲስ አበባ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል።ይህንን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በመሰረተ ሃሳቡ የተስማማበት እና የአውሮፓ እና አሜሪካ መንግስታትን ጨምሮ 15 በላይ ሃገሮች የተቀበሉት ነው።የኢትዮጵያ መንግስትም በትግራይ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚያጣራ ቡድን ሁሉ መስርቷል። ስራም ጀምሯል።
በወቅቱ ሁለቱም ማለትም የተመድ ሰብዓዊ መብት ካውንስል እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጋራ በቀጣይ በአማራ እና አፋር ምርመራ እንደሚያደርጉ እና የጸጥታው ሁኔታ ብቻ እንዳገዳቸው ገልጠው ነበር።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ስብሰባውን አስመልክቶ ያለውም ስጋት የገለጠበት መግለጫ ላይ ያለውም የጀመርነው ፕሮጀክት እያለ የምን ስብሰባ ነው? የሚል ጥያቄ ነው።
የዛሬው የተመድ ሰብዓዊ ካውንስል ስብሰባ የአውሮፓ ህብረት ቢጠራውም የካውንስሉ የአፍሪካ ሃገሮች አንዳቸውም አልፈረሙበትም።
የስብሰባው ዓላማ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ገሶ በተመድ ስም እንደ ኢራን የኒኩሌር መርማሪ ቡድን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚገቡ ባዕዳን ማሰማራት እና ውጤት በሚሉት ውሳኔ አሳልፎ ኢትዮጵያን እስከመውረር ለመድረስ ነው።
ይህ አደገኛ አካሄድ በአጭር ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ጉዳት ቢያመጣም በረጅም ጊዜ ግን በአፍሪካ እና አውሮፓ መሃል ጦርነት የሚከፍት ውሎ አድሮ የተባበሩት መንግስታትን የሚከፋፍል ቁልፍ ጉዳይ ነው።ተመድ በብዙ ጉዳይ ቋፍ ላይ ያለ ድርጅት ነው።የኢትዮጵያ የዛሬው ጉዳይ የመከፋፈሉ የመጀመርያው መጀመርያ ሊሆን ይችላል።
ውድ ኢትዮጵያውያን! የዛሬው የተመድ ስብሰባ እንደ ''የውሾች ጉባዔ'' መወገዝ አለበት!
የኢትዮጵያ አምላክ ስብሰባውን ይበትነው!
===============////============
No comments:
Post a Comment