ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, July 3, 2014

'' UK where is your citizen Ato Andargachew? Yemen release Andargachew now!''ኢትዮጵያውያን ኦስሎ፣ኖርዌይ በሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ፊት አቶ አንዳርጋቸውን አስመልክተው ሰልፍ አደረጉ

የእንግሊዝ ኤምባሲ በኦስሎ (UK Embassy in Oslo, Norway )

ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 26/2006 ዓም (ጁላይ 3/2014) ኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት ቁጥራቸው ከ150 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በየመን መንግስት ኃይሎች መታገትን በመቃወም ተቃውሟቸውን ገልፀዋል።ሰልፉ የተዘጋጀው ''የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ'' በጠራው መሰረት ሲሆን የእንግሊዝ ኤምባሲ የተመረጠበት ምክንያት አቶ አንዳርጋቸው የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው በመሆኑ ነው።

በሰልፉ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች መሃከል '' ዩኬ ዜጋሽ የት ነው? የመን አቶ አንዳርጋቸውን ልቀቂ! አቶ አንዳርጋቸው የዲሞክራሲ ተሟጋች እንጂ አሸባሪ አይደለም!'' የሚሉ ይገኙባቸዋል።ሰልፉ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተሞላበት እና የእንግሊዝ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንድትሰጥ የማድረግ ዓላማ የያዘ ነበር።

በመቀጠልም  በሰልፉ አስተባባሪ  ''የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ'' አማካይነት ለእንግሊዝ ኤምባሲ የተዘጋጀውን ደብዳቤ የእንግሊዝ አምባሳደር በኖርዌይ ተወካይ ወደ ሰልፈኞቹ መጥተው ከመረከባቸውም በላይ ለተሰላፊዎቹ ባደርጉት ንግግር ''ጉዳዩን የእንግሊዝ መንግስት በአንክሮ እየተከታተለ ነው እኛም ከየመን መንግስት ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶችን ለማከናወን ጥረት ላይ ነን'' በማለት ተናግረዋል።

በመጨረሻም ሁኔታዎች ለውጥ ካላሳዩ ቀጣይ ሰልፎች እንደሚኖሩ በተለይ በመጪው ማክሰኞ በመላው ዓለም በሚገኙ የየመን ኤምባሲ እንደሚደረግ እና የመን በኦስሎ ኤምባሲ ስለሌላት በሌሎች የአውሮፓ ከተሞች የሚደረጉ ሰልፎች ላይ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቦ የሰልፉ ፍፃሜ ሆኗል።

ጉዳያችን 
ሰኔ 26/2006 ዓም  (ጁላይ 3/2014)

No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)