ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, July 8, 2014

የኢቲቪ የዛሬው የአቶ አንዳርጋቸውን ንግግር ያሳየበት ፊልም ከኢህአዲግ/ወያኔ ስሌት በራቀ መልኩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሁለት ጉዳዮችን አረጋግጦለታል


ዛሬ ሐምሌ 1/2006 ዓም ኢቲቪ አቶ አንዳርጋቸው የግንቦት 7 ንቅናቄ ፀሐፊን በድብቅ ካሜራ ያነሳውን ፊልም አሳይቷል።አቶ አንዳርጋቸው በተጎሳቆለ ሰውነት ሆነው የተናገሩት ዶ/ር ብርሃኑ ባለፈው ሳምንት ከተናገሩት ጋር ተመሳሳይ ነው።አቶ አንዳርጋቸውን ወያኔ  በየመን ካስያዘ በኃላ ወደ ሀገር ቤት አምጥቶ ከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ እንዳደረሰባቸው ኢሳት ትናንት ከታማኝ ምንጮች ማግኘቱን ጠቁሟል።በዛሬው የኢቲቪ ፊልምም ይህንን መመልከት ይቻላል።
የኢቲቪ ፊልም ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክት አስተላልፏል።በባህር ማዶ ከ 30 ዓመት በላይ መኖር ሀገር አያስከዳም፣መማር ለሀገር በረሃ ለበረሃ መንከራተትን አይከለክልም።አቶ አንዳርጋቸው በሳር በተሰራ ጎጆ ፊት ሆነው፣አንዲት ምስኪን ኢትዮጵያዊት ሲያፅናኑ የሚያሳይ ፎቶም አሳይቷል።በወያኔ አስተሳሰብ አቶ አንዳርጋቸውን ያዋረደ እና ዝቅ አድርጎ ያቀረበ መስሎት ነው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መልክቱ ታላቅ ነው።በረሃ ስለመብትህ የሚታገሉ አሉ።እውነት ነው።የሚል መልዕክት አለው። 
በሌላ በኩል ኢቲቪ ያረጋገጠልን ነገር ዶ/ር ብርሃኑ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የተናገሩትን ነው።ዶ/ር ብርሃኑ ያሉትን እና ዛሬ በኢቲቪ አቶ አንዳርጋቸው የተናገሩትን ተመልከቱ።ተመሳሳይ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብም ስለ አቶ አንዳርጋቸው የሞራል ብቃት የተነገረው ትክክል መሆኑን ነው።ይህም ፅናት፣እውነተኝነት እና ከሆድ ይልቅ ሕሊናን የማዳመጥ ፋይዳን አሳይቷል።በተለይ ወጣቱን ወደ ውጭ ለስደት መሮጥ ሳይሆን ለሀገር ነፃነት ታግሎ በሀገር ላይ በኩራት መኖርን ሁሉ አመላክቷል።  

ዶ/ር ብርሃኑ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ባለፈው ሳምንት ያሉት  እንዲህ ነበር

 'እንደ አንዳርጋቸው ከራሱ ጋር የታረቀ ሰው አላየሁም''
''በእውነት በጣም እድለኛነት ነው እንዲህ ከውስጥ ከራስ ጋር መታረቅ''
'' አንዳርጋቸው ሊገሉት ቢፈልጉ እየሳቀ ነው የሚሞተው የእነርሱን ከብትነት እያመነ ነው የሚሞተው''
''አንዳርጋቸው መስራት ያለበትን ጨርሶ ወጣቶችን ለመሪነት አብቅቶ አታስፈልገንም ሂድ ተብሎ እንግሊዝ ሀገር መኖር ጀምሯል''


አቶ አንዳርጋቸው ዛሬ በኢቲቪ ዜና እወጃ ላይ በድብቅ ካሜራ የተነሱት ፊልም ላይ ሲናገሩ የታየው -

''እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ''
''እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው''
''ምንም አይነት ብስጭት የለኝም''
''ምንም አይነት መጥፎ ስሜት አይሰማኝም።የመጨረሻ እርጋታና እረፍት ውስጥ ነው ያለሁት''

ከአቶ አንዳርጋቸው ንግግር የምንረዳው ዶ/ር ብርሃኑ እንዳሉት ስራቸውን  በሚገባ ጨርሰዋል።ለሚያምኑበት በመስራታቸውም  ዛሬም በስቃይ መሃል ሆነው ህሊናቸው ተረጋግቷል።

የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር ለመስማት ይህንን  ይጫኑ።

ጉዳያችን 
ሐምሌ 1/2006 ዓም (ጁላይ 9/2014)


No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...