ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, April 24, 2013

''ህዝብ ለሕዝብ የኪነት ልዑክ'' በደርግ ዘመን ''የአባይ ግድብ ቦንድ ግዥ'' በዘመነ ኢህአዲግ -የሀገሬ አዙሪት(አጭር ማስታወሻ ለሀገሬ ልጅ)

በዘመነ ደርግ በ ፍ 1977 ዓም ኢትዮጵያ ገጥሟት የነበረው የድርቅ አደጋ መላው አለም ከጎኗ በመቆሙ  ኢትዮጵያ የኪነት ቡድኗን በመላው አለም እያዟዟረች ባህላዊ እና ዘመናዊ ሙዚቃዎቿን በማሳየት የምስጋና ቃሏን አሰማች።የኪነት ቡድኑም ሕዝብ ለሕዝብ የኪነጥበብ ልዑክ ተሰኘ።በእዚህ ሃሳቡን ከማመንጨት ጀምሮ ቡድኑን በመምራት በመላው አለም ይዘው የተዟዟሩት አምባሳደር ዶክተር ካሳ ከበደ የቀድሞው መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ነበሩ።

በልዑካን ቡድኑ ውስጥ አንጋፋ የኪነት ሰዎች  ጥላሁን ገሠሠ፣ብዙነሽ በቀለ፣መሐሙድ አህመድ እና ሌሎችም 
የተሳተፉ ሲሆን የዛሬው ተወዳጁ አክቲቪስት ታማኝ በየነም ተካቶበት ነበር።ቡድኑ በአሜሪካ፣አውሮፓ፣መካከለኛው ምስራቅ  ተገኝቶ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከማሳየቱም በላይ በብዙ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የኢትዮጵያን ሌላውን ገፅታ በማሳየት አድናቆትን አትርፏል።ታድያ በወቅቱ ቡድኑ በሄደበት ቦታ ሁሉ እግር በእግር እየተከታተሉ ቡድኑን ይቃወሙ የነበሩ አንዳንድ ቦታ ለዱላ የትጋበዙ ከእዛ ባስ ሲል ደግሞ ግርግር በመፍጠር ዝግጅቱን ለማስቆም የሞከሩ የሻብያ፣የኢህአዲግ፣እና ሌሎች የደርግ ተቃዋሚዎች በእየዝግጅቱ አዳራሽ መግቢያ ላይ ነበሩ።አንዳንዶቹ ቦታዎች እንዲያውም ከያንያኑን አግቶ ለመውሰድ ሴራ ተጠንስሶ ነበር።አዎን በትክክል ለሚያስብ ሰው የሀገርን ገፅታ መቀየር መቃወም  አሳዛኝ ነው። የወቅቱ እሳቤ ግን ''ደርግ ሀገር ሰላም ነው ለማለት ነው----በመጀመርያ ሰብአዊ መብት ይከበር'' የሚል  ነበር።

መሃሙድ አህመድ (ሕዝብ ለሕዝብ ልዑክ አባል)
በዘመናችን ደግሞ ሌላ ሕዝብ ለሕዝብ ቡድን የአባይ ቦንድ ግዥ ሆኖ መጥቷል።አባይን መገደብ ሀገር ያለማል፣ወገን ያኮራል።የያነዎቹ የህዝብ ለሕዝብ ተቃዋሚዎች ሀገርቤት ገቡ እና የአባይ ግድብ ቦንድ ግዥ ይዘው እንደ ሕዝብ ለሕዝብ የኪነት ልዑክ በውጭ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ   ''የሀገር ገፅታ ይቀይራል ወገን ያኮራል ቦንድ ግዙ'' ብለው ጠየቁ።''ከአባይ ግድብ በፊት በመጀመርያ ሰብአዊ መብት ይከበር''ሆነ ጥያቄው።
የወጣው ቢገባም የገባው ቢወጣም ሀገሬ ከማይለቅ አዙሪት አልወጣችም።እውነትነት የሌላቸው ህዝብን ቀርቶ ቤተሰባቸውን በአግባቡ ማሳመን በማይችሉ ቃላት የሚሸነግሉ መሪዎች ተሸክማ ሀገሬ አሁንም አለችበት ቆማለች።
እንደዜጋ ማሰብ ''እሰይ አሳፈርኩት፣ኩም አድርጌ መለስኩ'' ሳይሆን ሃገሬ ከእዚህ አዙሪት የምትወጣው፣በዘረኝነት ላይ ከተመሰረተ አስተሳሰብ የምትላቀቀው ፣አባይንም በሕዝብ ፍቅር ላይ የምትመሰርተው፣''ሕዝብ ለሕዝብ የኪነጥበብ ልዑክ'' ካለአንዳች እረብሻ ለመላው አለም የምታሳየው  መቼ ነው? የሚለው ጥያቄ ነው ጥያቄው።ለእዚህስ የእኔ ድርሻ ምንድንነው? ነው ቀጣዩ ጥያቄ።

ጌታቸው በቀለ 
ኦስሎ 

1 comment:

Anonymous said...

lezih melse meschaw holowem tekebaberow sisera naw

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።