ከ ፅሁፉ በታች የምታዩት ዛፍ ቀድሞ የነበሩት ጓደኞቹ- (ዛፎች) የት ሄዱ? አልኩ እና ምናልባት ዛፍነታቸውን እረስተው ሌላ መሆን ፈልገው ትተውት ሄደው ይሆን? ብዬ አሰብኩ። እናም የ ዛፉ ታሪክ እንዲህ መሆን አለበት አልኩኝ። ከ እዚህ በፊት ዛፍ ሆነው ለ መርከብነት፣ለ ታቦትነት ወዘተ ስለተመረጡ ዛፎች ታሪክ አውቅ ነበር።እኔ ግን ዛሬ ታሪኩን መቀየር አማረኝ። ዛፉ ከሚቆረጥ ዛፍ እንደሆነ ቢፀናስ? ብዬ አሰብኩ እና እንዲህ ጫጫርኩት።
በመጨረሻ እንዲህ ሆነ
  
''ዛፍ ሆነን ከሜዳ ላይ ከሚበርደን ከ ቤት ገብተን ወንበር ሆነን ሰዎች ከ ክብር አዋርደው ቢቀመጡብን፣በር ሆነን እንደፈለጉ ቢወዘውዙን ይሻላል'' ብለው አምላክ የሰጣቸውን የ ዛፍነት ክብር ተዉት። 
ይህ ዛፍ ግን ብቻውን ቆሞ ሁሉም ሲሄዱ ታዘባቸው።
በመጨረሻ እንዲህ ሆነ
በመጨረሻ ግን በ ሃገሩ የተገኘ ብቸኛ ዛፍ ነው እና የሃገሩ ሰዎች ተሰብስበው ቤተክርስቲያን ሊሰሩ ሲያስቡ እስከመጨረሻ ወደ ጸናው ዛፍ መጡ። አከበሩትም ቤተክርስቲያን ከ ጎኑ ሰሩ።ዛፉም በ ቤተክርስቲያኑ ቅፅር ግቢ ውስጥ ተከለለ። ቀጥሎም አንድ ቀን የኔታ ወደ ዛፉ መጡ። ብቻውን የቆመባቸውን እነኛን ክፉ ዘመናት አስበው ተከዙ። ተክዘውም አልቀሩም።የሚያስተርምሯቸውን ተማሪዎች ከ ዛፉ ስር ለማድረግ ወሰኑ። ከዛፉ የተሻለ ስለ ፅናት የሚያስተምር ምሳሌ እንደማይገኝ አውቁ። አስበውም አልቀሩ የኔታ ወንበራቸውን ከ ዛፉ ስር ዘረጉ። እነሆ ዛፉ በእራሱ አርጅቶ ካልወደቀ በቀር እንደማይቆረጥ ቁርጥ ሆነ። የ ሌሊት ማህሌት፣ የ ማለዳ ቅዳሴ፣ የቀን ቅፀላ ምግቡ ሆነ። ''እስከመጨረሻ የሚፀና እርሱ ይድናል'' የሚለውን ቃል አሰበ። ቀድሞ ወንበር እና በር ለመሆን ዛፍነታቸውን የከዱ የድሮ ጓደኞቹ ቀኑበት። አሁን እነርሱ ወንበርነታቸው አብቅቶ ከደጅ ተጥለው ለ ማገዶነት የሚመጣውን አመት በዓል ይጠባበቃሉ። እስከመጨረሻ የፀናውን ዛፍ ያድርገን።ዛፍ መሆን ወንበር ከመሆን ይሻለናል።
እነሆ የ ዛፉ ታሪክ ተፈፀመ።
ጌታቸው 
ኦስሎ 

 
 
 
 
2 comments:
This is superb. I prefer to be the tree, hence my name_ Teklu.
This is superb. I prefer to be the tree, hence my name_ Teklu.
Post a Comment