ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, December 10, 2012

የ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የ ዕርቅ ጉባኤ በተመለከተ ያለኝ ሃሳብ (የ ዳላሱ ንግግር ማብቃቱ እንደተነገረ)


ኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሃገር ውስጥ ውጭ የሚገገኙ አባቶች እርቅ ጉባዔ አሜሪካ ዳላስ ላይ ማድረጋቸው እና በትናንትናው እለት መጪው ወር ሎስ አንጀለስ ላይ ተቀጣጥረው መለያየታቸውን ደጀ ሰላም የተሰኘው ብሎግ ዛሬ አስታውቋል።

እዚህ ጉባዔ ምንም እንኳን የተፈለገውን ያህል ውጤት ባይገኝም የነገን እርቀ ሰላሙን አካሂያድ በደንብ መጤን ያለበት መሆኑን ግን የሚያመላክት ይመስለኛል። በመሆኑም ሁኔታዎች ካሁኑ መስተካከል ያለባቸው መሆኑን ሁሉም ወገኖች ሊያጤኑት የሚገባ ይመስለኛል::


 ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አባቶች አቀባበል ተድርጎላቸው (ፎቶ ከ ደጀ ሰላም ብሎግ)

የ አስታራቂው ኮሚቴ በተመለከተ


አስታራቂው ኮሚቴ እስካሁን ያሳየው ትጋት የሚያስመሰግነው ነው። ሆኖም ግን ምንም እንኳን ዝርዝር ጉዳዮችን ባላውቅም ሰው ሃይል ጉዳይ መስፋት ያለበት እና ቤተ ክርስቲያኒቱ ካላት የሰው ሃይል አንጻር በመጪዎቹ ውይይቶች ምዕመናንን ፍላጎት ቤተክርስቲያኒቱን ደረጃ በሚመጥን መልክ ምዕመናን ሌሎች ቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት የሚያከብሯቸው ምዕመናን መካተት ያለባቸው ይመስለኛል።ይህም አስታራቂ ኮሚቴው አባቶችን ንግ ግር ለመስማት እራሱ ትልቅ ቤተክርስቲያንን ሃላፊነት የሚጠይቅ እና ቤተ ክርስቲያኒቱ ተጻራሪዎች አሳልፎ የማይሰጥ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ምክንያቱም ንግ ግር ነውና አባቶች ውይይቱ ወቅት ከድሮ የነበሩ ታሪኮችን፣ድርጊቶችን በስሜት ሆነው ማውራታቸው አይቀርም። በመሆኑም አሁንም ለእዚህ ደረጃ የበቃ የሰው ሃይል አስታራቂ ኮሚቴው ውስጥ መጨመር አለበት። ምናልባትም አስታራቂ ኮሚቴውን የሰው ሃይል እንደገና ማየትም ሊያስፈልግ ይችላል።እዚህ ላይ ችግሩን ያልፈቱት አባቶች ሳሉ ለምን አስታራቂ ኮሚቴው ላይ ይተኮራል የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን አሁን በኋላ የሚኖረው ውይይት ምዕመናንንም ጥያቄ የያዘ፤ አዲስ የተሻለ ሃሳብ የሚያቀርብ እና ሃገር ውስጥ ከመንግስት ጀምሮ ውጭ እስካሉት ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጭምር አስፈላጊ ሲሆን የሚያናግር ብሎም ድብቅብቅ አስራር ተላቆ እርቅ መርሃግብሩን አቅድ ሁሉ ህዝቡ ጋር ተወያይቶ የሚሄድ ጉዳዩንም ባለቤቱ ምዕመኑ የሚያሳውቅ መሆን አለበት። ይህ ሲሆን ሁሉንም እረፉ ቤተ ክርስቲያን በላይ ሆነ አገልጋይ ሊኖር አይችልም የሚል ወደመፍትሔው የሚመራ መንገድ መታየት ይጀምራል።

በእርግጥ ሃይማኖት ነው ችግር መፍትሔ የሚሰጠው እግዚያብሔር ነው።ማወቅ ያለብን ግን እግዚያብሔር ተጣሉ አለማለቱን ነው። ሁሉም በላይ ግን ትልቅ ጥንቃቄ የሚሻው እና ምዕመናን የሚጠበቀው የሚመስለኝ ሁሉንም አባቶች ለመውቀስ አለመቸኮል ነው። የችግሩ አነሳስ ባህሪ፤ሂደቱ አሁን ያለበት ሁኔታ ሃገራችን ፖለቲካዊ ገጽታ ጋር የመያያዙ ክስተት አባቶች ቶሎ ወደ ውሳኔ እንዳይሄዱ ቸግሯቸዋል ብለን ብንረዳ እራሳችንን እያታለልን ያለን አይመስለኝም።ለችግሩ መንስዔዎች ውስጥ እኛ ምዕመናን ድርሻ የሌለ እንዳይመስለን።አባቶቻችንን( ውጭም ሆነ ሃገር ቤት ያሉትን) እንዴት ከዚህ ውስብስብ ችግር እንዲወጡ እንርዳቸው ብሎ ማሰብ የእውነተኛ ልጅነት መለያ ነው። አባቶች ተፈትነዋል ፈተናውን ግን እነርሱ ብቻ ናቸው ያመጡት ማለት አይቻልምና።
ለምን ሎስ አንጀለስ?
አሁኑ ዕርቅ ጉባዔ ዳላስ ሲደረግ ሁለቱም አባቶች በጎ ፈቃድ የነበረ መሆኑ ቀደም ብሎ ተገልጾ ነበር። ሎስ አንጀለስ ላይ በመጪው ወር ይደረጋል ሲባል ግን ለምን ሎስ አንጀለስ? አልኩኝ። ሎስ አንጀለስ ለማደራደር አትበቃም ለማለት ሳይሆን።ጸሎት እንኳን ከጀመሩበት ቦታ ጸንተው ሲፈጽሙት በጎ ነው ይላሉ አባቶች። አስታራቂው ኮሚቴ ነው የመረጣት ሎስ አንጀለስን? ወይስ ቤተክርስቲያን እርቅ ጉባዔ ሁሉንም አሜሪካ ከተማ ማዳረስ አለበት?

ይህችን አነስተኛ ጽሁፍ ለመደምደም ግን አሁንም አስታራቂ ኮሚቴው መሰረተ ሰፊ ፤አቅም ያላቸው ሰዎች (አቅም ሰጪ አምላክ መሆኑ ሳይረሳ)ማካተት እና በኮሚቴው ውስጥ አቅም በታች ያሉ ካሉ በስራው አጋዥነት መድቦ ሌሎች ስራዎችን እንዲያከናውኑ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል። ከሁሉም ከሁሉም ግን እራሱ አነሳሽነት የተነሳው ኮሚቴ ተመስግኖ ምዕመናን ቤተክርስቲያኒቱ ባለድርሻዎቿ (ርስት ወራሽ ናቸና)የተወከሉበት ሰፋ፣ጠንከር እና ተጠያቂነት ያለው አስታራቂ ኮሚቴ አስፈላጊ ነው።

አበቃሁ
ጌታቸው
ኦስሎ


No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።