አቶ ኢሳያስ ለድርድር ኳታርን ሸምግይኝ ማለታቸውን ''አዋተ''የተሰኘውን
ድህረ ገፅ አስታውቋል። እርግጥ ነው አቶ ሃይለማርያም ባለፈው ለአልጀዚራ ሲናገሩ ''አቶ መለስ ከ ሃምሳ ጊዜ በላይ ጠይቀዋል እኔም
አሁኑኑ አስመራ ሄጄ ለመደራደር እቻላለሁ'' ማለታቸው ይታወሳል። ለሰላም ለመነጋገር በኳታር በኩል ከመዞር እንደ እኔ እንደ እኔ
በደብረ ዳሞ በኩል ተቀታጥሮ አንዳፍታ መወያየት ይቀል ነበር። ኳታር '' አልጀዚራ'' የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣብያ ማዕከል ብቻ ሳይሆን ባላት የ ተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ ሀብት በ
2009 ከተባበሩት አረብ እምሬት ቀጥላ በመካከለኛው ምስራቅ ካሉት ሃገራት ውስጥ በ ተባበሩት መንግሥታት የ '' ሰው ልማት ሰንጠረዥ''
(Human development Index) የሁለተኘትን ደረጃ ይዛለች።
''ትንሽ ሀገር
ትልቅ ችግር?'' (small country but big problem)
የኳታርን በተለይ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ ዘው ብላ መግባቷን ያዩ እና በ ሌሎች ሀገሮች ጉዳይ ላይ ደግሞ በዜና ማሰራቻዎቿ ማራገቧን የተመለከቱ የአካባቢው አጥኚዎች ''ትንሽ ሀገር ግን ትልቅ ችግር'' ብለው ይጠሯታል።የሀገሪቱ ያለፈ ታሪክ ላይ ትንሽ ስእል ለመስት:-
· እ.አ.አ ከ 1783 እስከ 1868 ባህራኒ አስተዳደር ስር፣
· እ.አ.አ ከ 1871 እስከ 1916 በ ኦቶማን ኢምፓየር ስር፣
· እ.አ.አ ከ 1916 እስከ 1971 በ እንግሊዝ ስር ተዳድራለች።
ከሁለተኛው አለም ጦርነት መጠናቀቅ ተከትሎ ሀገሪቱ የ እንግሊዝ ቅኝ የነበሩ ሃገራት ነፃነታ
ውን ሲያገኙ እንግሊዝም የ ፖለቲካ ስልጣን ለመስጠት የ ሶስት አመት ጊዜ አስቀምጣ ስለነበር ኳታርም በ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 1968ዓም ከ ባህሬን ጋር በ ፈድሬሽን እንድትዋሃድ አደረገቻት። በ መጨረሻ አሁንም በ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ መስከረም 3 ቀን 1971 ዓም ሙሉ ነፃነቷን አገኘች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በ አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የ ማደራደር አቅሟን ለማጎልበት ጥረት አድርግላች። በ ምዕራብ ሳሃራ ግጭት ፣ብ የመን ግጭት እና በ ፍልስተሞቹ ''ፋታህ'' እና ''ሐማስ'' ምካከል ለመሸምገል ሞክራለች።
የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ እና ኳታር
ኳታር በ አፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ መግባት የጀመረችው በ ደርግ ዘመነ መንግስት ነበር። ሻብያ በኢርትራ ሲዋጋ ስንቅ እና ትጥቅ አቀባይ ከሆኑት ሃገራት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ቀንደኛ የ ድርጅቱን አባላት በማስጠለል እና የ መንቀሳቀሻ ፓስፖርት በመስጠትም ትታወቅ ነበር። ይሄው ግንኙነት ከ ደርግ መውደቅ ጋር የተሻሻለ መልክ የያዘ ቢመስልም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተከትሎ የመሻከሩ ደረጃ ብሶበት በ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2008 ዓም ተመልሶ የ ኢትዮጵያ እና የ ኳታር ዲፕሎማሲ ግንኙነት መልሶ ተቋረጠ። በ ቅርቡ ከ አቶ መለስ እረፍት ተከትሎ ባለፈው ጥቅምት 2012 ዓም ነው ኳታር የ ዲፕሎማሲ ግንኙነቷን ከ ኢትዮጵያ ጋር ያደሰችው።
ኳታር በ ሱዳን እና በ ኤርትራ መሃከል ያለውን በጫፍ ያለ የሚባልለትን ግንኙነት በመያዝም ትታወቃለች። በሁለቱ መሬቶች መሃከል ያለውን የድንበር ችግር ለመግታት የድንበር ከተሞቹ ላይ የኢንዱስትሪ ማዕከል ልመስርትላችሁ ብሎ ከመጠየቅ ባለፈ በገንዘቧ የሁለቱን ሃገራት የሚያገናኝ የአስፋልት መንገድ ሰርታ ባለፈው አመት ጥቅምት ወር ላይ የኳታር መሪ ኤሚር ሼክ ሐመድ አል ታኒ፣የ ሱዳኑ አልበሺር እና የ ኤርትራው ኢሳያስ በተገኙበት አስመርቃለች። በምረቃውም ላይ የ ሱዳኑ አልበሺር ኤርትራ በ እሳቸው ላይ የ ዓለም አቀፉ ፍርድቤት የ ቆረጠውን የ መያዥያ ሰነድ ወደጎን በማለት ያስተናገደቻቸው ሀገር መሆኗን ጠቅሰው ወደፊትም ነፃ የ ድንበር ክልል እንዲኖር እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ይህን ይበሉ እንጂ የ ሁለቱን መሬቶች ግጭት በ ኳታር የ ገንዘብ ኃይል እንዲገታ መደረጉን እና የ ጊዜ ቦንብ መሆኑን ግን ለማውሳት አልበሺርም ሆኑ ኢሳያስ አልደፈሩም።
የኳታር ኢሚር ፣አልበሽር እና ኢሳያስ ኳታር ያሰራችውን መንገድ ሲመርቁ
የኳታር የ ድርድር ጥያቄ ቀደም ብሎ የጠየቀ የነበረ ቢሆንም በ አቶ ኢሳያስ የግል በጎ ፈቅድ ብቻ የሚመራው የኤርትራ አስተዳደር በ አንድ በኩል የመለስን መሞት ተከትሎ የሚመጣውን ለውጥ ስተባብቅ በ ሌላ በኩል ደግሞ በ ኢትዮጵያ በኩል ጫፍ የያዙ የ ህዋሀት አመራሮች ሲጎትቱት የቆየ ጉዳይ ነበር። አሁን ግን ሁለቱም ለድርድር የሚቀርቡ ከሆነ ስለ ሚከተሉት ምክንያቶች ብቻ እንጂ ለውጤት ሁለቱም እንደማይተጉ ግን ለመረዳት ሊቅ መሆን አያስፈልግም። ለድርድር እንዲቅርቡ ያደረጋቸው ምክንያት የመጀመርያው በ ኤርትራ በኩል እና በ ኢትዮጵያ በኩል ያለው የውስጥ ቅራኔ ከፍተኛ ደረጃ ስለደረሰ እና ለ ቅራኔው አቅጣጫ ማስቀየርያ ትልቁ የሀገር ውስጣቸውንም ሆነ አካባብያዊ ብሎም አለምአቀፍ ፖለቲካን የማብረጃ ስልት አድርገው ስላዩት ብቻ ነው። ኤርትራ የ ኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች ስልጠና ከምስጠት አልፎ አስከ ማስታጠቅ ድረስ እየሰራች እንደሆነ አቶ መለስ ብዙ ጊዜ ተናግረዋል። ኢትዮጵያም ከፍተኛ ባለስልጣናቷ ሳይቀሩ የተገኙበት የ አቶ ኢሳያስ ተቃዋሚዎችን አለማቀፍ ስብሰባ ከማስተናገድ አልፋ ''በ አረብ ሳተላይት'' በኩል ''ሓዳሽ ኤርትራ'' የተሰኘ የ ቴሌቭዥን ፕሮግራም ከ ምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ ዘወትር ማስተላለፍዋ እና የ ኤርትራ ቴሌቭዥን የደበቃቸውን የሃገር ውስጥ ክስተቶች ይፋ መሆናቸው በ እረጅም ጊዜ ተፅኖ መፍጠሩ አልቀረም። ከሁሉም
ግን ኤርትራ ከ ዓለም ሕብረተሰብ ከ ሚድያውም በመጥፋቷ ትንሽ ለ ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ አርስት መሆንም አስባ ይሆናል።የምሰመርበት
ግን ሁለቱም ሃገራት ውስጣዊ ችግሮቻቸውን ማስታገሻ እና ማስቀየሻ የምትመዘዘውን የ ተለመደች ካርድ መምዘዛቸው ብቻ ነው።
ከሁሉም ግን አሳዛኙ ክስተት የሁለቱ ሃገራት ጉዳይ በ አቶ ሃይለማርያም እና አቶ ኢሳያስ እጅ ላይሆን የመቻሉ ጉዳይ ነው። ጉዳዩ እጅግ ግሎ ውይይት የሚደረግበት እና የሚወሰነው በ ድብቅ በር በ ሁለቱ የ ጦር አለቆች ዘንድ ነው። በ ሁለቱም የ ጦር ሰራዊት አዛዦች ዘንድ ከ ብሔራዊ እና ስትራተጃው አስተሳሰብ ይልቅ ክልላዊ እና የ ትውልድ ቦታ ቅድምያ ስለሚሰጠው እልህ እና ተደፈርኩ ባይነት የጎላበት ስሜት ብዙውን ጊዜ የ ፕሬዝዳንቱንም ሆነ የ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሚና ያኮስሰዋል። በመሆኑም ይህን የሚያውቁት አቶ ኢሳያስ ባለፈው ለ አልጀዚራ ቴሌቪዥን አቶ ሃይለማርያም የሰጡት '' አስመራም ቢሆን ሄጄ እደራደራለሁ '' የሚለው ንግግር በ ህዋሀት የጦር አበጋዞች ዘንድ ምን ያህል ንዴት እንደፈጠረ እና ይህ ልዩነት ደግሞ ''ኳታርን አደራድርኝ ብላትማ የትየለሌ ይደርሳል'' አሉና አቶ ኢሳያስ ይሄው ''ያለቅድመ ሁኔታ እንደራደር'' አሉ ተባለ። ''እውነትና ንጋት እያደር'' እንደሚባለው በ ሺህ የሚቆጠረው የ ኤርትራ ወጣት በሺ ከሚቆጠረው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ እና አህቱ ጋር በ የመን በሱዳን በ እግሩ እየሄደ ይንከራተታል። ለህዝባቸውም ሆነ ለ እራሳቸውም ያልሆኑት መሪዎች ግን አንዴ ከ ኳታር አንዴ ከ ዱባይ እያሉ በ ህዝቡ ይነግዳሉ።
No comments:
Post a Comment