ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, December 17, 2012

''ቡሃዚ ዛሬ ላንተ እናለቅሳለን ነገ ግን አንተን የገደሉህን እናስለቅሳቸዋለን''የ ቡሃዚ ሰማዕትነት ዛሬ ሁለተኛ አመቱ

መሐመድ ቡሃዚ ሰፈር ስሙ ''ባስቡሳ'' ይባላል።እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር መጋቢት 291984 ''ሲዲ ቦስድ'' በተሰኘ ቦታ ቱንስያ ውስጥ ተወለደ።አባቱ ሊብያ ውስጥ ግንባታ ሥራ ተሰማርተው ይሰሩ ነበር። መሐመድ ቡሃዝ አባቱን በሞት ያጣው ገና ሶስት ዓመቱ ነበር።በልጅነቱ ያገኘውን ሥራ አየሰራ ቤተሰቡን መርዳት የጀመረው ግን  ገና አስር አመቱ ነበር። ነገር ግን ጥሮ ግሮ መስራቱ ሙስና ለተበከለች ሀገር ምኗም አይደል።ትምህርቱን አጠናቆም ሥራ ማግኘት አልቻለም። ጥቂቶች ስልጣን  ሚባልጉባት እና የተቀማጠለ ሕይወት በሚመሩባት ሃገሩ ውስጥ ያለው ፍትህ-ልባ ስርዓት ተስፋ ቢያስቆርጠውም ቡሃዚ እጅና እግሩን አጣጥፎ አልተቀመጠም በመንገድ ዳር አነስተኛ ንግድ ለመስራት ደፋ ቀና ማለት ጀመረ።ታህሳስ 162010 ሁለት መቶ ዶላር ተበድሮ የመንገድ ዳር ንግድ ለመነገድ ብድር ያገኘባት ቀን ነበረች
በቀጣዩ ቀን ታህሳስ 172010 ጧቱ ሁለት ሰዓት ላይ በተበደረው ገንዘብ የገዛቸውን ሸቀጦች ይዞ መንገድ ዳር መሸጥ ጀመረ። ስርዓቱ ግን አሁንም እረፍት አልሰጠውም ፖሊሶቹን ልኮ ቁም ስቅሉን አሳየው። ፖሊሶች የመስርያ ቦታውን እንዲያፈርስ ነገሩት። መንገር ብቻ አደለም ግፍ ዕቃዎቹን ወረወሩበት። ፖሊሶቹ ጉቦ ቢሰጣቸው እንደሚተዉት ቡሃዚ ይውቃል። ግን የሚሰጠው የለውም። አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ ወደከተማው አስተዳደር ሄዶ ''አቤት!'' አለ። ሰሚ አላገኘም። ፍትህ ካልሰጡት እራሱን እንደሚያቃጥል ነገራቸው። አልመሰላቸውም ሰማዕትነቱ እነርሱ አልፎ ቱንስያን ቤተመንግስት እንደሚያርገፈግፍ ብሎም መላ ሰሜን አፍሪካን አልፎም የመንና ሶርያ እንደሚደርስ ማንም አልገመተም። ልክ የዛሬ ሁለት አመት ታህሳስ 172010 አቆጣጠር ቡሃዚ ከተማው ምክርቤት ፊት ለፊት እራሱን አደባባይ አቃጠለ።

በቀብሩ ስነስርዓት ላይ ከአምስትሺህ በላይ ቱንስያውያን እያለቀሱ ቀበሩት ቀብሩ ላይ ግን ወጣቶቹ እንዲህ አሉ ''ቡሃዚዛሬ ላንተ እናለቅሳለን ነገ ግን አንተን የገደሉህን እናስለቅሳቸዋለን'' አሉ እንዳሉትም አልቀሩ ወጣቶቹ ተነሱ ፕሬዝዳንት ቤን አሊ ሀገር ጥለው እንዲሄዱ አደረጉ።ወላፈኑ ለልብያው ጋዳፊ፣ለግብፁ ሙባረክም ተረፈ።ዛሬ ቡሃዚ በመላው ዓለም ታስቧል።በተለይ በሰሜን አፍሪካ ''የሃገራትን ቅርፅ ''የቀየረ ተሰኝቷል። የ እኛው የኔ ሰው ገብሬም በተመሳሳይ መልክ በ ፍትህ እጦት እራሱን አቃጥሏል።''የኔ ሰው እንዲታሰብ እንደ ገርማሜ ንዋይ እና መንግስቱ ንዋይ አምታትን ይጠብቅ ይሆን?
 
መሐመድ ቡሃዚ
                                                              ወጣቶቹ ስለ ቱንስያው አብዮት ለ አልጀዚራ ሲናገሩ (ቪድዮ ) 







የኔ ሰው ገብሬ
መሃመድ ቡሃዚእራሱን ያቃጠለበት አደባባይ                                         
¨                                                                                                


  

3 comments:

Helen from Addis Ababa said...

Is our love to mother land Ethiopia is less than Tunisian young generation? who can give ma an answer. I can not reply even to my self.
KENAHUBACHEW TEQATELKU BE ERASE DEKAMANET AHUN GIN WESENKU!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

Weqtawi vidio.
THANK YOU

Anonymous said...

Ye enetsu mekera ke ene mekera aybeltm. Ere Ethiopiawian Ethiopian enadin.

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።