Tuesday, December 4, 2012

''እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ '' ሐዋርያት ሥራ 20፣28

በ ሀገር ውስጥ ያሉት እና በ ውጭ ያሉ የ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል በ እዚህ በያዝነው ወር ውስጥ የ እርቅ ውይይትበ ደቡባዊቷ የ አሜሪካ ግዛት በ ቴክሳስ ዳላስ  ይደረጋል። ምእመናን እጅግ በ ጉጉት እየጠበቁት ያለ ጉዳይ ነው። የ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የምትሄድበትን መንገድ የሚያመላክት ወሳኝ ውይይትም ነው። እኔም ከ አባቶቻችን ውይይት እንደ ቤተክርስቲያኒቱ ልጅነት ምን መጠበቅ አለብን? ብዬ ሳወጣ ሳወርድ ቆየሁ። እናም የ ውይይቱ ውጤት ከ እነኚህ ነጥቦች ባያንስብን ብዬ ተመኘሁ።

1ኛ / ''ከ ሁለት ሲኖዶስ'' ወደ አንድ ሲኖዶስ የሚያመጣ ፣

2ኛ / እውነተኛ የ ቤተክርስቲያንን አንድነት የሚያሳይ እና

3ኛ/ ሁሉም ያለፈውን እረስቶ ለነገዋ የ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት  የሚተጋበት እንዲሆን ።

አንድ ግን መርሳት የሌለብን ነገር አለ።የ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የ ሀገሪቱ አሻራ እንደመሆኗ ለ ሀገራችን የነገ ሁለንተናዊ እሷነቷ ትልቅ ተፅኖ ያለው መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ለ እዚህም ነው የ አባቶችን መጪ ውይይት የ ኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ በ በጎ ምኞት የሚጠብቁትን ያህል በ ኢትዮጵያ ላይ ካላቸው የጠላትነት ስሜት ይህን ውይይት በጎ ፍሬ እንዳያፈራ ተግተው የሚሰሩ መኖራቸውን መዘንጋት የሌለብን።

ምእመናንም የትኛውም አይነት ፖለቲካዊ፣ፍልስፍናዊ፣ወዘተ አስተያያት ቢኖረን በ እዚህ የ ውይይት መርሃግብር ላይ ግን አንዳች ልዩነት ሊታይ አይገባም። ሁሉም እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆኖ ሁሉንም አባቶች የ ቤተክርስቲያንቱን አንድነት ላይ እንዲተጉ፣ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆናቸውን በማስገንዘብ ሊያበረታቷቸው ይገባል።

''እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ ከ እኔ በኋላ ለመንጋይቱ የማይራሩ ነጣቂዎች ተኩላዎች እንደሚመጡ እኔ አውቃለሁ '' ሐዋርያት ሥራ 20፣28-30 የሚለው ቅዱስ ቃል ዛሬም ሕያው ነው እና።

ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያለው ታምሩ በ አንድ ወቅት ያስተማሩት ትምህርት ከ እዚህ በታች ያዳምጡ።

ቸር ወሬ ያሰማን
ጌታቸው
ኦስሎ


 

2 comments:

Anonymous said...

Anjet aris!

Anonymous said...

egziabher ytebkh berta endih yal lg lebetekrstiyn yasfelgatal dingl bemlgewa betecrstiyann ttebkln