ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, November 28, 2012

ዶክተር ጌታቸው እንዳሉት'' የሃውልቱ ተነስቶ መቅረትን ቅዠት ያድርግልን''


ሰሞኑን አዲስ አበባ ቀላል ባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ሳቢያ ሁለቱ ሃውልታት ማለትም ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ፕሮጀክቱ ሳቢያ ይነሳሉ የሚል ዜና አዲስ አበባ ተሰምቶ የነበረ መሆኑን እና ጉዳያችንም ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ፕሮጀክቱ ክለሳ ሃሳብ ጋር ፅሁፍ አቅርባ እንደነበር ይታወሳል።የ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ምላሽ ሰጥቷል።

ዶክተር ጌታቸው በትሩ ኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ ባለፈው ሰኞ ህዳር 17/2005 ዓም አሜሪካ ድምፅ ራድዮ አማርኛው ክፍል አገልግሎት በሰጡት መግለጫ የሚከተሉትን ተናግረዋል። 

  • ''የ አፄ ምኒልክ ሃውልት ፈፅሞ አይነካም ፣''
  • ''የ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ግን የ ባቡሩ መስመር በስር በኩል ሲያልፍ ሐውልቱን ሊያናጋው ስለሚችል ሐውልቱን አንስተን መልሰን ምናልባትም በተሻለ ሁኔታ  በክብር ለማስቀመጥ ከሁሉም የ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተነጋገርን ነው፣ ''
  • ''የ እሳቸው (የ አቡነ ጴጥሮስ ) ታሪክ የታወቀ ነው የ እዚህ አይነት የ ''ኬርለስ '' ሥራ ይሰራል ብሎ የሚያስብ ካለ እየቃዠ ነው ፣''
  • ''እናፈርሳለን ሳይሆን እንዲሰመርበት የምንፈልገው አንስተን መልሰን እናስቀምጣለን ነው፣''
ቪኦኤ ጥያቄ- '' ተመልሶ ለመተከሉ ዋስትናው ምንድነው ?''
  • ''ዋስትነው እኛ ነን ኃላፊነት አለብን። ወድያው ነው የሚመለሰው። ከ ኮንትራክተሩ ጋር ያለን ውል አድባባዩ እንዳለ አንዲመለስ ነው የተዋዋልነው።''
ቪኦኤ ጥያቄ; መቼ ይጠናቀቃል?( አሁን ያሉት ቦታ ለመድረስ )
  • ''መጪው ክረምት ከመምጣቱ በፊት ሰማንያ ከመቶ የሚሆነው ሥራ ይጠናቀቃል።''


አቶ ጌታቸው እንደቃልዎ ያድርግልን። ጉዳዩ ግን ''ቀን እባብ ያየ ማታ ልጥ ይፈራል'' ሆኖ ነው። ዋልድባ አባቶች በልማት ፕሮጀክት ስም አባቶች ሲንገላቱ፣ከ ሰሞኑ ደግሞ ትግራይ ተንቤን ታልቁ አርበኛ አሉላ አባ ነጋ የተሰየመው ትምህርት ቤት አርበኛው ውለታ ተረስቶ አቶ መለስ ተሰየመ ተብሎ አሻራ ሲጠፋ፣መቀሌ የተጀመረው አፄ ዮሐንስ ሃውልት ስራው እንዲቆም ተደረገ መባሉ ሁሉ ታሪክ አሻራን ለማጥፋት ዘመቻ አካል ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው።ደግሞም ብዙ ተጨባጭ ነጥቦችም ስላሉ ነው።ከ እዚህ በተረፈ ግን እገሌ የነካው ሁሉ ልማት አይደለም የሚል አስተሳሰብ ግን የመፍጠር ፍላጎት ቢያንስ እዚህ ትውልድ ውስጥ መስረፅ እንደሌለበት እስማማለሁ።

እስከዝያው ግን ይህ ትውልድ የሀገሩ ልማት የሚናፍቀውን ያህል ፖለቲካው አረማመድ ያሰጋዋል ብዬም አስባለሁ። ስጋቱ ግን እንደ ኢህአዲግ አገላለፅ '' ጨለምተኝነት'' አስተሳሰብ ሳይሆን ሌሎች ተሞክሮ እና ካለፈው ታሪካችን የሚነሳ ጭብጥ ስላለው ነው።ሲሰራ ደስ ይለዋል። ሲጠፋ ይከፋዋል።ለሁሉም ግን ዶክተር ጌታቸው ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ '' እዚህ አይነት ''ኬርለስ '' ሥራ ይሰራል ብሎ የሚያስብ ካለ እየቃ ነው ''እንዳሉት። ባቡር ዝርጋታውን እውን። የሃውልቱ ተነስቶ መቅረትን ቅዠት ያድርግልን።

ዶክተር ጌታቸውን ቃለ ምልልስ ያለበት አሜሪካ ድምፅ ራድዮ ሊንክ እና ባቡር ፕሮጀክቱ መስመር ካርታ እዚህ በታች ያገኛሉ።

ቪኦኤ ህዳር 17/2005 ፕሮግራም = http://amharic.voanews.com/audio/audio/234269.html
ከ ኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ድህረገፅ የተወሰደ በ ሰዓት ከ ሰማንያ ሺ ሰው በላይ የሚያንቀሳቅስ የ አዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሚያልፍባቸው ቦታዎች (http://www.erc.gov.et/index.php/projects.html?start=1)
 
ከ ኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ድህረ ገፅ የተወሰደ ( http://www.erc.gov.et/index.php/projects.html?start=1)
 
 
 

1 comment:

Anonymous said...

I think zis should be z main purpose of bloger. To tell z reders z fact on z ground. Enamrsgnalen. Thank u.

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።