- አስገራሚው ነገር ግን የ ሀውልቱ መንቀያ ወጪ ከ ዲዛይኑ ማስተካከያ (ባቡር መስመሩ ሐውልቱን ሳይነካ በ ጎን የሚያልፍበት) ወጪ መብለጡ ነው።
- በ አሁኑ አለም ቻይና የገባችበትን ፕሮጀክት ነቁጥ የሚፈልጉ እና ሃያ አራት ሰዓት የሚሰሩ 'ሚድያዎች' በ ምዕራቡ ዓለም መኖራቸውን የ ኢትዮጵያ መንግስት መዘንጋት የለበትም። ቻይና ከ 'አፕል ኮምፕዩተር¨ ምርት ጋር የገባችውን ውዝግብ መርሳት አይገባም።
- ባለንበት ዘመን ካምፓኒዎች በ ህብረተሰባዊ ኃላፊነት (Corporate Social Responsibility-CSR) በ መላው አለም በሚለኩበት ዘመን ቻይናዎች የነገ የ ሌላ የ አፍሪካ ሀገር ፕሮጀክት ዕድላቸውን የሚያበላሹ ላይሆኑ ይችላሉ ።
- ''የ ሕብረተሰብ ጉዳቶች በ ሁለት ደረጃዎች ከ ግንዛቤ ውስጥ ይገባሉ:- የመጀመርያው በ ፕሮጀክቱ የ ዲዛይን ደረጃ ሲሆን ሁለተኛው በ ልማት ዕቅዱ ትርጉም ላይ ነው።
- የ ሕብረተሰብ ጉዳት (social cost) ብዙውን ጊዜ በትክክል የሚታወቀው ፕሮጀክቱ ተያይዞ የሚያመጣቸው ጉዳቶች ከተከሰቱ በኋላ መሆኑ ችግሩን ያገዝፈዋል። ከ እዚህ አንፃር የ ሀውልቱ መነሳት የሚፈጥረው ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግር ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ ወጪው ላይ ለመደመር መዘጋጀት ይፈልጋል።
ዛሬ ከ አዲስ አበባ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት የ ሰማአቱ የ አቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ይነሳል ቢባልም 'መንግስት ከ ቦታው እመልሳለሁ' የሚል መልክት በ መንግስታዊ የመገናኛ ብዙሃንም ጭምር እየተነገረ ነው። እስኪ ጉዳዩን ከ ፕሮጀክት አስራር በኩል ያለውን አንደምታ አንድ ሁለት ልበል።
አንድ ሃውልት ሲተከል እንዲነሳ ተደርጎ አይደለም ። በጣም ጥብቅ ሆኖ እንደሚሰራ የታወቀ ነው።ሃውልቱን ለማንሳት ብሎን እንደመፍታት ቀላል አለመሆኑን ነገር ግን ከ ስር መገዝገዝ እና መቁረጥ እንደሚያስፈልግ ለማወቅ መሃንዲስ መሆንን አይጠይቅም።
ይህ ማለት ሃውልቱን ለመንቀል ወጪ ይፈልጋል ማለት ነው (በዶዘር እንደማይፈርስ ስለሚታሰብ )።አስገራሚው ነገር ግን የ ሀውልቱ መንቀያ
ወጪ ከ ደዛይኑ ማስተካከያ (ባቡር መስመሩ ሐውልቱን ሳይነካ በ ጎን የሚያልፍበት) ወጪ መብለጡ ነው።ምክንያቱም ለሀውልጡ ማንቀሳቀሻ
ብቻ ከ ስዊድን ሀገር በተቀጠረ አማካሪ ኩባንያ አማካኝነት እንደሚከናወን አቶ አበበ ምሕረቱ የ ኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን
የ ኮምኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ሲናገሩ ''ሥራው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሲደርስ ስዊድን አገር የሚገኘውና ከፍተኛ ልምድ ያለው
ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ሥራውን በበላይነት የሚቆጣጠረው ሲሆን በሚያስመጣቸው ባለሙያዎች አማካይነት ሐውልቱን ከ ቦታው ያስቀምጣል።''
ብለዋል። እዚህ ላይ ነው ነጥቡ።የአማካሪ ወጪ ሲደመር የ ዋስትና(insurance) ክፍያ ሲደመር ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ፕሮጀክቱን
በ ሀውልቱ ምክንያት ያንሩታል።
እዚህ ላይ
የ ፕሮጀክቱን
ወጪ ሂሳብ
በ ቀላል
አስተሳሰብ (logic) እንመዝነው ።
እርግጥ ነው
የ ፕሮጀክትን
ወጪ በ
ምሳሌ መገምገም
አይቻልም።ዝርዝር መረጃን
ስለሚፈልግ።
ከ እዝያ በፊት ግን ማንኛውም የ ልማት ፕሮጀክት ማሟላት የሚገባው ቢያንስ ሶስት አይነት ግምገማዎችን ማለፍ እንዳለበት ይታወቃል ። ይህ ማለት የ ባቡር ሐዲድ ዝርጋታው ፕሮጀክት ከ ሶስት ዋና የመለክያ ነጥቦች አንፃር ተገምግሞ እንደሚፀድቅ ይታወቃል።እነርሱም:-
ሀ/ የ ወጪ-ገቢ ትንተና (cost-benefit
Analysis):- ለ
ባቡር ግንባታ የሚወጣው ወጪ ከሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ጋር በማነፃፀር።
ለ/ የ አካባቢ ተፅኖ ዳሰሳ (Environmental Impact Assessment -EIA):- ፕሮጀክቱ በ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተፅኖ የሚለካበት እና
ሐ / የ ሕብረተሰቡ ጥቅምና ጉዳት ትንተና (Social cost-benefit Analysis):-ፕሮጀክቱ በ ማህበረሰቡ የ ጤና፣የ ገቢ ፣ባህላዊ ፣ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቱ ላይ የሚፈጥረው በጎ ያልሆነ ተፅኖ ሁሉ የመለካቱን ሂደት ያጠቃልላል።
ሐውልቱን መንቀል ዲዛይኑን ከማስተካከል የበለጠ ወጪ አለው።
ለ/ የ አካባቢ ተፅኖ ዳሰሳ (Environmental Impact Assessment -EIA):- ፕሮጀክቱ በ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተፅኖ የሚለካበት እና
ሐ / የ ሕብረተሰቡ ጥቅምና ጉዳት ትንተና (Social cost-benefit Analysis):-ፕሮጀክቱ በ ማህበረሰቡ የ ጤና፣የ ገቢ ፣ባህላዊ ፣ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቱ ላይ የሚፈጥረው በጎ ያልሆነ ተፅኖ ሁሉ የመለካቱን ሂደት ያጠቃልላል።
ሐውልቱን መንቀል ዲዛይኑን ከማስተካከል የበለጠ ወጪ አለው።
የሃውልቱ መነቀል ከላይ ከተጠቀሱት ወጪዎች አንፃር ሁሉም በ እዚህ ፕሮጀክት ላይ የሚወድቁ ወጪዎች መሆናቸውን ለመረዳት በጣም ቀላል ነው። ሃውልቱን ከመንቀል ይልቅ ዲዛይኑን ማስተካከል (በ ትንሽ እርቀት ባቡሩ እንዲያልፍ በማድረግ) አዋጪ መሆኑን ለመረዳት ሃውልቱን መንቀል ለ ሁለት አይነት ወጪ እንደሚዳርግ መረዳትን የግድ ይላል።እነርሱም:-
1/ የ ገንዘብ ወጪ(ቀጥተኛ ወጪ)
ለዲዛይን ማስተካከያ
ከመክፈል ለ
ሃውልት መንቀያ
የሚያወጣው ገንዘብ
ከፍተኛ እንደሚሆን
ይገመታል። ለምን?።ሀውልቱ እንዳይላላጥ እና
እንዳይሰበር ከ
አነቃቀል እስከ
ማንቀሳቀስ ድረስ
ኃላፊነት ሲወሰድ
የ መንቀል
፣የማንቀሳቀስ ሥራ
እራሱን የቻለ
ወጪ አለው።
ከላይ እንደተጠቀሰው
የመንቀሉ ሥራ
ላይ የ
ስዊድን አማካሪ
ድርጅት ክፍያ
ማለትም የአማካሪ
ወጪ፣ የ
ዋስትና(insurance) ክፍያ ፣
በሐውልቱ ማንሳት
እና ማንቀሳቀስ
ዙርያ ያሉ
ሌሎች ተያያዥ
ወጪዎች በሙሉ
እዚህ ላይ
ይካተታሉ።
2/ የ ሕብረተሰብ ጉዳት (Social-cost)-
ከላይ እንደጠቀሰው '' የ ሕብረተሰብ ጥቅምና ጉዳት ትንተና'' (Social
cost-benefit Analysis )፣ ቀጥተኛያልሆነ
ወጪ ነገር ግን ጉዳቱ ብዙ ጊዜ ከፍተኛ ችግር የመፍጠር አቅም ያለው ነው። ይሄውም ፕሮጀክቱ በ ማህበረሰቡ የ ጤና፣የ ገቢ ፣የ አካባቢ ብክለት ፣ባህላዊ ፣ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቱ ላይ የሚፈጥረው በጎ ያልሆነ ተፅኖ ሁሉ መኖር አለመኖሩ የሚለካበት የልማት ፕሮጀክት መለክያ መንገድ ነው። ይህም በማንኛውም የ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ፕሮጀክቱ ከመፅደቁ በፊት በሰፊው የሚተነተን መሆኑ ይታወቃል። አንድ የልማት ፕሮጀክት ከ ገንዘብ ወጪ-ገቢ (cost-benefit
analysis) አንፃርብቻ
የሚለካበት ጊዜ አልፏል።
በተለይ በአሁኑ አለም ማንኛውም ፕሮጀክት ጤናማ የሚያሰኘው ጥሩ የሆነ የ አካባቢ ተፅኖ ዳሰሳ እና የ ሕብረተሰብ ጥቅም-ጉዳት ትንተና (Social
cost-benefit Analysis) ጥሩ የሆነሲሆን
ብቻ ነው።በ ባቡር ፕሮጀክቱ ሳቢያ ያለው የህብረተሰብ ወጪ (Social cost) እጅግ ከፍተኛ እንደሚሆን ለማወቅ የ ሀውልቱ እጅግ ውድ የሆነ ታሪካዊ ፋይዳ ማወቅ ይጠይቃል። ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ በስማቸው ቤተክርስትያን የታነፀላቸው፣በ ኦርቶዶክሱ አለም ብቻ ሳይሆን ከ ኦርቶዶክስ ውጭ በሆኑት እንደ ስዊድን ቤተ ክርስቲያን ''የ ክፍለ ዘመኑ ሰማዕት'' የሚል ስያሜ ማግኘታቸውን እና ኢትዮጵያ በ ክፍለዘመኑ ከነበሩት ሰማአታት ደረጃ መሆናቸው በ እራሱ በ ሀውልቱ ላይ የሚደረገው የማንቀሳቀስም ሆነ ቦታ የመቀየር ተግባር ግዙፍ የ ሕብረተሰብ ጉዳት እንደሚኖረው ሊታወቅ ይገባል። የ ሕብረተሰብ ጉዳት (social cost) ብዙውን ጊዜ በትክክል የሚታወቀው ፕሮጀክቱ ተያይዞ የሚያመጣቸው ጉዳቶች ከተከሰቱ በኋላ መሆኑ ችግሩን ያገዝፈዋል። ከ እዚህ አንፃር የ ሀውልቱ መነሳት የሚፈጥረው ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግር ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ ወጪው ላይ ለመደመር መዘጋጀት ይፈልጋል። ለምሳሌ በ ተቃውሞ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች፣ መንግስትን ለ ዓለም አቀፍ ክስ የሚያቀርቡት ሂደቶች ሁሉ በ መጪ ወጭነት መመዝገብ ይገባል ማለት ነው። ለ እዚህም ነው ሐውልቱን ከማፍረስ ይልቅ ዲዛይኑን ማስተካከል ይቀላል ለማለት የሚያስደፍረው።
እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ከላይ የተጠቀሱት ትንተናዎች የሚደረጉት በቅድምያ ፕሮጀክቱ ሥራ ላይ ከመዋሉ በ ዲዛይን ደረጃ እና በ ፕሮጀክቱ ስራም ላይ የመከለስ ዕድል መኖሩን ነው።በ አውሮፓ የ ትራንስፖርት ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የ ትትራንስፖርትን የ ሕብረተሰብ ጉዳት ትንተና ፅሁፍ ላይ ማንጋውም የ ትራንስፖርት ግንባታ ፕሮጀክት ሁለት ጊዜ የመከለስ ዕድል ስለመኖሩ የ ኢኮኖሚ ልማት እና ትብብር (OECD) እትም እንዲህ ይገልፀዋል :-
''የ ሕብረተሰብ ጉዳቶች (ስለ መንገድ ፕሮጀክት ነው ከላይ ፅሁፉ የሚያብራራው) በ ሁለት ደረጃዎች ከ ግንዛቤ ውስጥ ይገባሉ:- የመጀመርያው በ ፕሮጀክቱ የ ዲዛይን ደረጃ ሲሆን ሁለተኛው በ ልማት ዕቅዱ ትርጉም ላይ ነው።''
''Social costs are
taken into account at two different levels:first, in the design of projects,
and then in the definition of development plans'' E Quinet - Internalising the
social costs of transport, European Conference of Minister of
Transport, OECD publication,1994,p.29
ዲዛይኑ ካልተስተካከለ አደጋው ለቻይናም ይተርፋል
ከ እዚህ በተረፈ ግን የ አለም አቀፍ ሕብረተሰብ ከቅርስ ጋር በተያያዘ የሚነሳ ጥያቄ በ ኢትዮጵያ መንግስት ላይ መቅረቡ አይቀርም።ዩነስኮን ጨምሮ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳዩን በጥብቅ እንዲያዩት መግፋት ከማንኛውም ዜጋ የሚጠበቅ ግዴታ ነው።
በ አሁኑ አለም ቻይና የገባችበትን ፕሮጀክት ነቁጥ የሚፈልጉ እና ሃያ አራት ሰዓት የሚሰሩ ሚድያዎች በ ምዕራቡ ዓለም መኖራቸውን የ ኢትዮጵያ መንግስት መዘንጋት የለበትም። ቻይና ከ አፕል ኮምፑተር ምርት ጋር የገባችውን ውዝግብ መርሳት አይገባም።(http://www.nytimes.com/2011/02/23/technology/23apple.html?pagewanted=all&_r=0)
የ ቻይና ፕሮጀክት ሲወቀስ አብሮ የ አፍሪካ መንግሥታት ጥሩ አርስት ተገኘላቸው ማለት ነው። እናም ምርጫው የ መንግስት ይመስለኛል። ዲዛይኑን አስተካክሎ የ ሰማአቱን ሃውልት አክብሮ ፕሮጀክቱን መጨረስ።
ከ እዚህ ባለፈ ግን ባለንበት ዘመን ካምፓኒዎች በ ህብረተሰባዊ ኃላፊነት (Corporate
Social Responsibility-CSR) በ መላውአለም በሚለኩበት ዘመን ቻይናዎች የነገ የ ሌላ የ አፍሪካ ሀገር ፕሮጀክት ዕድላቸውን የሚያበላሹ ላይሆኑ ይችላሉ። እና በ CSR ሕግ መሰረት ዲዛይኑ እንዲስተካከል እንደሚገፉ እገምታለሁ። በመሆኑም የ ግንባታውን ጨረታ
ያሸነፈውና ስራውን የሚያከናውነው የ ቻይናው የ ባቡር እሯን ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ( China
Railway Eryuan Engineering Group Co. Ltd. (CREEC)(http://www.capitalethiopia.com/index.php?option=com_content&view=article&id=226:addis-ababa-light-railway-project-starts-&catid=35:capital&Itemid=27
) ጉዳዩን እንዲረዳው ማለትም የሚደርስበትን ወቀሳ እንዲገነዘብ ማረግ ተገቢ ነው። የ ካምፓኒዎች ያለፈ የ ፕሮጀክት አፈፃፀም ወደፊት
ከሚሰሩት ሥራ ጋር በ እጅጉ ስለምቆራኝ ቻይናዎች ዝም ብለው ያልፉታል ብሎ ማሰብ አይቻል።
ለማጠቃለል
የ ባቡር ዝርጋታው ፕሮጀክት አንዱ እና ዋናው የ ትራንስፖርት ችግር መፍቻ መንገድ መሆኑ የታወቀ እና አስደሳች ሥራ ቢሆንም በ ሀገሪቱ አሻራዎች ላይ ያለው ጥቁር ነጥብ በደንብ ሊመዘን ይገባዋል። ነፃ ''ሚድያ'' ለሌላት ሀገር እና ህዝቡ ስለ ጉዳዩ ለመወያየት ዕድል በሌለው ሁኔታ በ ህዝቡ ዘንድ የሚፈጥረው ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ለመለካት በጣም ከባድ መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም።
አሁንም ያለው አማራጭ አንድ ይመስለኛል። ዲዛይኑን ማስተካከል እና ስራውን የ ሕዝብ ፕሮጀክት አርድርጎ መቀጠል። ይህ ሲደረግ ፕሮጀክቱ ቀረፃ፣ግምገማ እና የማረጋገጥ ደረጃ ሁሉ ሲያልፍ ገንዘብን እንጂ የ ሀገሪቱን አሻራ ያልታያቸው ባለሙያዎችም ሆኑ ባለስልጣናት ሊወቀሱ ይችላሉ። ይህ ተፈርቶ ግን ፕሮጀክቱ ልክ ነው ብሎ መቀጠል በ ወንጀሉ የሚጠየቁትን ሰዎች ከ ማብዛት በቀር ትርፍ የለውም።የ ባቡር ሐዲዱ ይዘርጋልን፣ ፕሮጀክቱም ይስተካከልልን።
አበቃሁ።
ጌታቸው
ኦስሎ
3 comments:
So perfect,informative and reasonable way of presentation.
YOU NEED TO WRITE IN ENGLISH. SO CHINES COULD READ AND CORRECT THE PROJECT DESIGN.
Yihn tsuhuf le babur project halafiwoch mesetet alebet. Berta tiru netb mizabawi aqerareb new geta yibarkih.
Post a Comment