ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, November 11, 2012

'ኢሳት 'በ ኢትዮጵያም ሆነ ከ ኢትዮጵያ ውጭ ቁጥር አንድ ተፅኖ ፈጣሪ 'ሚድያ' እየሆነ ነው:: ESAT TV and RADIO-NUMBER ONE INFLUENTIAL MEDIA ON ETHIOPIA ISSUES

'ኢሳት' (የ ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ) በ ዋሺግተን፣ለንደን ፣ አምስተርዳም እና በቅርቡ ደግሞ ቶሮንቶ ባሉት የማስተባበርያ ቢሮዎች እና ስቱድዮዎች በ ሚያቀርባቸው ፖለቲካዊ፣ምጣኔሃብታዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች የሚያተኩሩ ፕሮግራሞቹ በ ኢትዮጵያ ተፅኖ ፈጣሪ ከሆኑት ሚድያዎች ቁጥር አንድ እንደሆነ ከ ሀገርቤት ብዙዎች እየመሰከሩለት ነው። 'ጉዳያችን' ብሎግ  በ በጎም ሆነ በ ክፉ መልኩ  በ ሀገራችን ጉዳይ ላይ ተፅኖ ፈጣሪ የሆኑ ነገሮችን ማመላከት አስፈላጊነቱን ታምናለች።ቢያንስ ለ አዲሱ ትውልድ ከ ሃገሩ ፖለቲካዊ ኩነቶች የራቀ እንዳይሆን በ እዚህ በመረጃ ዘመን ትኩረት የሚሹትን ጉዳዮች ትኩረት የመስጠት ልምድ እንዲኖረው ማድረግ መልካም ነውና።

የ ኢሳት ''የ እርስዎ ለ እርስዎ'' የተሰኘው የ ሕዝብ አስተያየት የሚሰማበት መርሃ ግበር  የሚሰጠው መረጃ በቀላሉ የሚታለፉ ሳይሆን ልብ ላለው ነገን የሚያመላክት ነው።

የ ሕዝብ አስተያየት ያዳምጡ።

 

No comments:

መንግስት ከዲፕሎማሲያዊ መፋዘዝ ይውጣ! የአረብ ሊግ በአባይ ግድብ አንጻር የወሰነውን የጸብጫሪነት ተግባር በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የምላሽ መግለጫ ብቻ የሚበቃ ሊሆን አይገባም።መንግስት ያልሰራው ግዙፍ ስራ ኢትዮጵያን ለአደጋ እንዳያጋልጣት ያሰጋል።

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያቤት መንግስት በፍጥነት ሊሰራቸው የሚገቡት አምስት ወሳኝ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራት ========= ጉዳያችን አለርት ========= የአረብሊግ አንዱ የሚታወቅበት መለያው እንደባዶ ቆር...