ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, October 28, 2012

የካርቱሙ ቃጠሎ አንድምታ

ካርቱም የሚገኘው የ 'ያሞክ' የ ጦር መሳርያ ማምረቻ ፋብሪካ ማክሰኞ ለ ረቡዕ አጥቢያ ሌሊት( ጥቅምት 13 ለ 14 /2005 ዓ ም)  ባልታወቁ የ አየር ላይ ጥቃቶች የመቃጠል አደጋ ደርሶበታል። ሱዳን ''እስራኤል አቃጠለችኝ''  ብላለች። ከ ክስተቱ ቀጥሎ ከ አፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ጋር እና ከ ግብፅ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ድረስ ያሉትን ተያያዥነትያላቸው ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ጉዳዮች በ ስፋት እየተወሱበት ነው።''  ሱዳን ትሪብዩን '' ጋዜጣ ፋብሪካውን ከ ከተማ ለማራቅ መታቀዱን አርብ ኦክቶበር 26/2012 እ ኤ አቆጣጠር የ ካርቱምን አስተዳዳሪ አብደል ራህማን አልከሃድርን ጠቅሶ ዘግቧል። የሱዳን ትልቁ ተቃዋሚ ፓርቲ ''ኡማ ናሽናል ፓርቲ'' ጉዳዩን '' እናት ሀገር ተደፈረች'' ብሎታል።

 ሱዳን ኢራን ጋር ባላት ቅርብ ቁርኝት ምዕራባውያን ዘንድ አይነ ቁራኛ ምትታይ ሀገር ውስጥ መሆኗ አይዘነጋም። ሰሞኑ ክስተት ግን የሚከተሉትን ሶስት ጉዳዮች የሚያመላክት ይመስለኛል:-

የመጀመርያው   አንድ አይነት ሚድያው ያልተገለፀ ፍጥጫ መኖሩን ያመላክታል። ይሄውም ሱዳን ኢራን ጋር ባላት ትስስርም ሆነ ደቡብ ሱዳንን ሙሉ በሙሉ ከማጣቷ ጋር በተያያዘ ሊደርስባት የሚችለውን ከፍተኛ አለመረጋጋት ለማካካስ ረጅም ስትራቴጂ ሥራ ላይ የነበረች መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን  አዚህም ማስረጃው ጦር መሳርያው ማምረቻው ርቀት ተወንጫፊ ሚሳአሎችን ጭምር ማምረቻ ነበር መባሉን መጥቀስ ይቻላል። ይህ እቅድ የ ጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያን ከማጥቃት ጀምሮ እስከ የ አባይን ግድብ ማፍረስ የሚዘልቅ ዝግጅት መሆኑን መገመት ይቻላል።

  ሁለተኛው   በጦር መሳርያ ማምረቻው ቀጥሎ ሳብያ አረብ ሃገራት በተገቢ ሁኔታ አለመቃወማቸው ጉዳዩን ችላ ማለታቸውን ሳይሆን የሚያሳየው ሌሎች ከሱዳን ጋር ያሏቸውን ሚስጥራዊ ውሎች ለመደበቅ የፈለጉ ያስመስለዋል። እዚህ ላይ ተጠቃሿ ግብፅ ነች። ዛሬዋ ግብፅ ሙባረክ ግብፅ አይደለችም ዛሬ ስልጣን ላይ የሚገኘው '' እስላማዊ ወንድማማማቾች ህብረት'' አዲስ አበባ ላይ ቀድሞውን ግብፅ ፕሬዝዳንት ሁስነ ሙባረክን ለመግደል ሙከራ ካረገ በሁዋላ ግብፅ ውስጥ በተከሰተው ሕዝባዊ አብዮት ሳብያ ለስልጣን ይብቃ እንጂ በከፍተኛ ሁኔታ ስትደግፈው የነበረችው ሱዳንን ውለታ ፈፅሞ ይረሳዋል ተብሎ አይታሰብም። የዛሬውም እስራኤልን በተገቢው መንገድ አለመቃወም ካለጊዜው እንዳይወጡ የታሰቡትን ጉዳዮች ለመሸፈን እና ዋናውን ነገር እንዳንረሳ ' እየ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ማውጣቱ ምን ይጠቅማል? 'ያሉ አስመስሎባቸዋል-ግብፆችን። 

  የመጨረሻው ጉዳይ ኢትዮጵያ ጉዳይ ነው። ዊክሊክስ በለቀቀው ሚስጥራዊ መገናኛ መረብ መረጃ መሰረት የቀድሞው ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሺር ዳርፉር በስሩት ወንጀል ዓለም አቀፍ ፍርድቤት መያዥያ ትእዛዝ እንዲቆረጥ ውስጥ ውስጡን ሰርተዋል  ተብለው ታምተዋል።በመሆኑም ኢትዮጵያ እዚህም ሆነ አባይ ጉዳይ ሱዳን ግብፅ ጋር እንድትዶልት አያደርጋትም ማለት አይቻልም። ኢትዮ- ኤርትራው  1990ዎቹ የመጀመርያ አጋማሽ  ላይ በነበረው ጦርነት ግብፅ ጀነራሎቿን ልካ ኤርትራ ስለመርዳቷ አዲስ አበባ የሚገኝ አንድ የግል ጋዜጣ ወቅቱን ኢትዮጵያ ግብፅ አምባሳደር ሲጠይቃቸው ያሉት '' እኛ ጀነራሎቻችን ጡረታ ከወጡ በሁዋላ የት ሀገር እንደሄዱ የመከታተል ግዴታ የለብንም '' ሚል ነበር። ይህም አምባሳደሩ  ቢያንስ ጉዳዩን አለማስተባበላቸውን አመላክቷል።
በአጠቅላይ የ ሰሞኑ የ ካርቱም የ ጦር መሳርያ ማምረቻ ቦታ ቃጠሎ የ አፍሪካ ቀንድን ትኩሳት በ አዲስቷ በ እስላማዊ ወንድማማቾች ህብረት በምትመራው ግብፅ አይን ተገብቶ መመልከት ተገቢነት ይኖረዋል።በብዙ የ ሀገር ውስጥ ጉዳዮች እራሱን ወጥሮ የሚገኘው ኢህአዲግ የሀገር ውስጥ ውጥረቶችን ማርገብ ብቻ ሳይሆን መሰረታዊ የ ፖሊሲ እና የ ፈድራል አከላለል(ቋንቋን መሰረት ያላደረገ) ስልትን በመከተል እና መጭዋን ኢትዮጵያ ያገናዘበ ለውጥ ማድረግ፣ ውጥረቶችን ማርገብ እና የ ሕዝቡን አንድነት በተገቢው ሁኔታ መጠበቅ አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ መሆኑን ሊረዳበት የሚችልበት ወሳኝ ጊዜ ላይ መሆኑን ማወቅ  አለበት።ከ እዚህ በተለየ ግን ካለ አንዳች የ ፖሊሲ ለውጥ በሌለበት''የ አቶ መለስ ራእይ'' እየተባለ የ ወቅቱን ሁኔታ ያላገናዘበ ሥራ የሚሰራ ከሆነ በ ሀገራችን ላይ የሚጋረጠው  አደጋ ቀላል ሊሆን አይችልም። የውስጣዊ ጉዳዮች በ ብዙ ሁኔታ የ ሕዝቡን ህብረት እንዳይፈታተኑ አበክሮ መስራት ከ ፓርቲ ጥቅም ይልቅ የ ሃገርን ጥቅም ማስቀደም ለ እራሱ ለ ኢህአዲግም  ህልውና የሚበጅ ወሳኝ ቁልፍ ተግባር መሆኑን ማወቅ ያለበት ጊዜ ላይ ነው-ኢህአዲግ።
 
አልጀዚራ የ ካርቱሙን የ ጦር መሳርያ ቃጠሎ የዘገበበት ዘገባ 
 
            የ ሱዳን የ ማስታወቅያ ሚኒስትር አህመድ ጃላል ስለጉዳዩ መግለጫ ሲሰጡ።
 
  

2 comments:

Anonymous said...

... This is not contrary to fact. The problem is that weyane also need such attack from Egypt just to divert the peopl focus.

Anonymous said...

Eritrea, Sudan and Egypt are negotiating to creat some agreement of common military contract against the west. Iran is the one who is trying to creat the form

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...